>
5:13 pm - Wednesday April 18, 4192

የነውረኛው ስዩም  መሥፍን አይን ያወጣ ያደባባይ ውሸት!  (አቻምየለህ ታምሩ)

የፋሽስት ወያኔ መስራች የሆነው  ስዩም መስፍን ባደባባይ በሕዝብ ፊት አይን ያወጣ ውሸት መቅጠፍ ልማዱ ስለሆነና  መቀሌ ላይ  ወያኔ ሻዕብያን ተከትሎ አዲስ አበባ የገባበትን 27ኛ ዓመት ሲያከብሩ ካቀረበው ንግግርም  ውስጥ አንድም  እውነት ፈልጌ በማጣቴ ነውረኛው እንጂ ውሸታሙ ስዩም መስፍን በማለት ልጠራው እንዳልችል አድርጎኛል።
ውሸት ልማዱ የሆነው ስዩም መስፍን «የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባድመን  ለኢትዮጵያ ሰጠ» ብሎ አገር በሙሉ  አደባባይ ወጥቶ ደስታውን እንዲገልጽ በቴሌቭዥን መስኮት ጥሪ አቅርቦ ነበር። ተጠያቂነትን ያሰፈኑ አገሮች እንደ ስዩም መስፍን በሕዝብ ፊት አይን ያወጣ ቅጥፈትና ውሸት የሚናገሩ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሕዝብ ይቅርታ ጠይቀው ከሥልጣናቸው ይለቁ  ነበር። ነውረኛው ስዩም ግን  «የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባድመን  ለኢትዮጵያ ሰጠ» ብሎ ሕዝብን ዋሽቶ ከሥልጣኑ መልቀቅ ይቅርና ይቅርታ እንኳ ሳይጠይቅ እስከዛሬ ድረስ ተጎልቶ የሚኖር ጉድ ነው።
ነውረኛው ስዩም ከሰሞኑ ደግሞ መቀሌ ላይ  «ጉንበት» 20ን  አስመልክቶ ባደረገው  ንግግር «ጀኔራ ሳሞራ ጠቅላይ ኢታማጆር በመሆኑ ብቻ ነው የአገር መከላከያ ሰራዊት የወያኔ ሰራዊት ወይንም የሕወሓት ሰራዊት ተብሎ እየተጠራ ያለው» ሲል ለታዳሚዎቹ ያስረዳል።
ጤና ይስጥልኝ ኣይተ ስዩም መሥፍን! ከዘጠና ሰባት በመቶ በላይ የሰራዊታችሁ የአዛዥነት ቦታ በማነው የተያዘው? ከሥዩም ውሸት የበለጠ በጣም የሚያሳዝነው ነገር በመድረኩም ይሁን ከመድረኩ ውጭ ባሉ ፕላትፎርሞች ስዩም  መሥፍን  «ጀኔራ ሳሞራ ጠቅላይ ኢታማጆር በመሆኑ ብቻ ነው የአገር መከላከያ ሰራዊት የወያኔ ሰራዊት ወይንም የሕወሓት ሰራዊት ተብሎ እየተጠራ ያለው» ሲል ባቀረበው ንግግር  የትግራይን  ሕዝብ  እየዋሸና እያሳሳተ መሆኑን ለትግራይ ሕዝብ ከትግራይ አካባቢ የሚናገር  አንድም ሰው አለመኖሩ ነው።
እውነት ስዩም መሥፍን እንዳለው ጀኔራ ሳሞራ ጠቅላይ ኢታማጆር በመሆኑ ብቻ ነው የአገር መከላከያ ሰራዊት የወያኔ ሰራዊት ወይንም የሕወሓት ሰራዊት ተብሎ እየተጠራ መሆን አለመሆኑን ከታች ያለውን በሰራዊቱ ውስጥ እስከቅርቡ ጊዜ ድረስ የነበረው የአዛዥነት ቦታ በነማን እንደተያዘ ተመልካች አይቶ ይፍረድና ሰራዊቱ የማን እንደሆነ የራሱን ድምዳሜ ይድረስ! እነሆ ማስረጃው!
በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ  ከላይ እስከ ታች ያሉ  የአዛዥነት ቦታዎችና አዛዦች የሚከተሉት ናቸው፤
1. የመከላከያ ኢታማጆር ሹም — ሜ/ጀ ሳሞራ የኑስ (ትግሬ)
2. የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር — ብ/ጀ ገ/ኪዳን ገ /ማሪያም(ትግሬ)
3. የመከላከያ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር —ኮ/ል ፍፁም ገ/እግዚአብሄር (ትግሬ)
4. የመከላከያ በጀትና ፕሮገራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር — ኮ/ል ምቡዝ አብርሃ(ትግሬ)
5. የመከላከያ የኪነ-ጥበባት ስራወች ኃላፊ —ኮ/ል ክብሮም ገ/ እግዚአብሄር (ትግሬ)
6. የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን የግንኙነት መምሪያ ኃላፊ—ኮ/ል ነጋሲ ትኩ (ትግሬ)
7. የመከላከያ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር —ኮ/ል ገ/ትንሳይ ሓጎስ (ትግሬ)
8. የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ዋና አዛዥ — ሌ/ጀ ሳህረ መኮንን (ትግሬ)
9. የመከላከያ ሎጅስቲክ መምሪያ ዋና አዛዥ —ሜ/ጀ ኢብራሂም አብደል ጀሊድ (ትግሬ)
10. የመከላከያ ኢንዱስትሪ ኃላፊ —ሜ/ጀ ክንፈ ዳኛዉ(ትግሬ)
11. የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኮማንደንት —ብ/ጀ ሃለፎም እጅጉ (ትግሬ)
12. የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ኃላፊ— ኮ/ል ሃጎስ ብርሃነ (ትግሬ)
13. የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት ዋና አዛዥ — ብ/ጀ ገ/እግዚአብሄር በየነ (ትግሬ)
14. የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የስልጠና ኃላፊ —ኮ/ል ግርማይ ገ/ጨርቆስ (ትግሬ)
15. የብር ሸለቆ መሰረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ት/ቤት የኢንዱክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ —ኮ/ል ጌታሁን ካህሳይ (ትግሬ)
16. የብላቴ ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ — ኮ/ል ዮሃንስ ካህሳይ (ትግሬ)
17. በልዩ ሀይል ማሰልጠኛ ማእከል የልዩ ኃይልና ጸረ ሽብር ማሰልጠኛ ት/ቤት አዛዥ —ሻለቃ ተክላይ ወ/ገብርኤል (ትግሬ)
18. የሜ/ጀ ሀየሎም አርአያ ወታደራዊ አካዳሚ ዋና አዛዥ— ኮ/ል ጎይቶም ፋሮስ (ትግሬ)
19. የጦር ላይ የበታች ሹም ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ — ኮ/ል አደም ምትኩ (ትግሬ)
20. የሜ/ጀ ሙሉጌታ ቡሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና አዛዥ — ኮ/ል ብርሃነ ተክሌ (ትግሬ)
21. የሆሚት አሙኒሽን ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ ዋና ኃላፊ —ኮ/ል ሃድጉ ገ/ጊዮርጊስ (ትግሬ)
22. የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ዋና ስራ አስኪያጅ — ሻለቃ አሰፋ ዮሃንስ (ትግሬ)
23. የመከላከያ ኮንስትራክሽንና ኢንጅነሪንግ ማሽነሪ ኢንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ— ሻለቃ ካህሳይ ክህሸን (ትግሬ)
24. የመከላከያ መሰረታዊ ልማትና ግንባታ ዘርፍ የኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ— አቶ ወልዳይ በርሄ (ትግሬ)
25. የታጠቅ ትራንስፎርመር ማምረቻ ኢንዱስትሪ ም/ስራ አስኪያጅ —ሻለቃ አማኑኤል አብርሃ (ትግሬ)
26. የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ ፋይናንስ ኃላፊ — ሌ/ኮ ለተብርሃን ደመወዝ (ትግሬ)
27. የመከላከያ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር — ኮ/ል ሃጎስ አስመላሽ (ትግሬ)
28. የመከላከያ ሚዲያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር —ኮ/ል ጸጋዬ ግርማይ (ትግሬ)
29. የመከላከያ መገናኛና ኢንፎርሜሽን ዋና መምሪያ የግኑኝነትና ስርአት ደህንነት መምሪያ ኃላፊ — ኮ/ል በርሄ አረጋይ (ትግሬ)
30. የመከላከያ ፋዉንዴሽን ኃላፊ — ብ/ጀ ያይኔ ስዩም (ትግሬ)
31. የሽሬ ከተማ ኮሪደር ሜንተናንስ ኃላፊ — ኮ/ል አብርሀ ገ/ መድህን (ትግሬ)
32. የብሔራዊ ተጠባባቂ የሃይል ዋና አዛዥ —ሜ/ጀ ማሞ ግርማይ (ትግሬ)
33. የኢንሳ ዳይሬክተር —ሜ/ጀ ተክለብርሃን/ካህሳይ (ትግሬ)
34. የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተርና የጅኦስፓሻል ደህንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር —ኮ/ል ታዚር ገ/እግዚአብሄር (ትግሬ)
35. የሰሜን እዝ አዛዥ —ጄ/ል ገብራት አየለ (ትግሬ)
36. የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥና የሎጂስቲክ ኃላፊ — ብ/ጄ አብርሃ አረጋዊ (ትግሬ)
37. የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ምክትል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ — ብ/ጀ ማዕሾ በየነ (ትግሬ)
38. የሰሜን ዕዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ኮ/ል ነጋሲ ተስፋዬ (ትግሬ)
39. የሰሜን እዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር የኢንዶክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ — ሌ/ኮ ሙሉ አብርሃ (ትግሬ)
40. የሰሜን እዝ 4ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ምክትል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ — ኮ/ል ገ/ስላሴ በላይ (ትግሬ)
41. የሰሜን እዝ የሰሜን ዕዝ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር — ኮ/ል ላዕከ አረጋዊ (ትግሬ)
42. የሰሜን እዝ መሃንዲስ አዛዥ —ኮ/ል ተሰስፋየ ብርሃኔ (ትግሬ)
43. የሰሜን እዝ ዋና አዛዥ ጽ/ቤት ኃላፊ — ኮ/ል ገ/ዮሃንስ ተክሌ (ትግሬ)
44. የሰሜን እዝ አጠቃላይ የትምህርት አገልግሎት ኃላፊ —ኮ/ል ግደይ ሃይሌ (ትግሬ)
45. የሰሜን እዝ የመድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት ሀላፊ ኮ/ል ሰገደ/ ገ/መስቀል (ትግሬ)
46. የሰሜን እዝ የኢንዶክትሪኔሽንና ኮምዩኒኬሽን ኃላፊ —ኪሮስ ወ/ስላሴ (ትግሬ)
47. የሰሜን እዝ ዘመቻ ኃላፊ — ኮ/ል ታደለ ገ/ህይወት (ትግሬ)
48. የሰሜን እዝ የሰዉ ኃይል አመራር መምሪያ ኃላፊ — ኮ/ል መሃሪ አሰፋ (ትግሬ)
49. የሰሜን እዝ የብ/ጀ በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ዋና አዛዥ — ኮ/ል ጀማል መሃመድ (ትግሬ)
50. የሰሜን እዝ የብ/ጀ በርሄ ወ/ጊዮርጊስ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ሆስፒታል ጤና ኃላፊ — ሌ/ኮ ተክላይ ገ/መድህን (ትግሬ)
51. የሰሜን እዝ የጤና ሙያተኞች ማሰልጠኛ ማዕከል ዳይሬክተር — ሻለቃ ነጋሲ ሃጎስ (ትግሬ)
52. የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ — ሜ/ጀ ዮሃንስ ወ/ዮሃንስ (ትግሬ)
53. የማዕከላዊ ዕዝ ምክትል አዛዥና የኦፕሬሽን ኃላፊ — ብ/ጀ አብርሀ ተስፋይ (ትግሬ)
54. የማዕከላዊ ዕዝ የትምህርት ክትትል ኃላፊ —ሌ/ኮ ሀጎስ ሀይሌ (ትግሬ)
55. የማዕከላዊ ዕዝ የዘመቻ መምሪያ አዛዥ ኮ/ል ገ/ሚካኤል ኪ/ማርያም (ትግሬ)
56. በማዕከላዊ ዕዝ የፋና ማሰልጠኛ ምክትል አዛዝና የኦፕሬሽን ኃላፊ — ኮ/ል ገ/እግዚአብሄር ገ/ሰላማ (ትግሬ)
57. በማዕከላዊ ዕዝ የፋና ማሰልጠኛ የወታደራዊ ተሽከርካሪና ማመላለሻ ዲፓርትምንት ኃላፊ — ሻለቃ ተክላይ ካህሳይ (ትግሬ)
58. የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ —ሜ/ጀ ፍስሀ ኪዳኑ(ትግሬ)
59. የምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥና የሎጅስቲክ ኃላፊ —ብ/ጀ አብድራሃማን ኢስማኤል (ትግሬ)
60. የምዕራብ ዕዝ ኢንሰፔክሽን ኃላፊ — ኮ/ል ዮሃንስ ገ/ሊባኖስ (ትግሬ)
61. የምዕራብ ዕዝ ሲግናል ሬጅመንት አዛዥ — ኮ/ል ተክላይ ገ/ጻድቃን (ትግሬ)
62. የምዕራብ ዕዝ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር — ኮ/ል ገ/ኪዳን ቸኮል (ትግሬ)
63. የምዕራብ ዕዝ የስልጠና ኃላፊ — ኮ/ል በርሄ ኪዳነ (ትግሬ)
64. የምዕራብ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል አዛዥና የስልጠና ኃላፊ — ኮ/ል ንጉሴ ሐይሌ (ትግሬ)
65. የደቡብ ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ — ሌ/ጀ አብርሀ ወ/ማሪያም (ትግሬ)
66. የደ/ምስራቅ ዕዝ ም/አዛዥ እና የሎጅስቲክ ኃላፊ — ብ/ጀ የማነ ሙሉ (ትግሬ)
67. የደ/ምስራቅ ዕዝ የትራንስፖርት ኃላፊ —ኮ/ል ቀለህ ገ/ስላሴ (ትግሬ)
68. የደ/ምስራቅ ዕዝ የህግ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር — ኮ/ል ገ/ሚካኤል ገብራት (ትግሬ)
69. የደ/ምስራቅ ዕዝ ጤና ት/ቤት ዳሬክተር — ሻ/ል ሀፍቱ ሰብለዉ (ትግሬ)
70. የ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ኮ/ል ሃጎስ [ህቁት] (ትግሬ)
71. የ5ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ምክትል አዛዥና የአስተዳደር ፋይናንስ ኃላፊ — ኮ/ል ተ/ብርሃን አለማየሁ (ትግሬ)
72. የ7ኛ ሜካናይዝድ ከ/ጦር የወንጀል ምርመራ ኃላፊ — አምሳ አለቃ ሀይለአብ ፍስሀ (ትግሬ)
73. የ8ኛ ሜካናይዝድ ከ/ጦር ዋና አዛዥ — ኮ/ል ገ/እግዚአብሄር ዘሚካኤል (ትግሬ)
74. የ8ኛ ሜካናይዝድ ክ/ጦር ኢንዶክትሬሽንና ኮሚኒኬሽን ኃላፊ —ሌ/ኮሎኔል ሓጎስ ታረቀኝ (ትግሬ)
75. የ12ኛ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ እና የሎጅስቲክ ኃላፊ — ኮ/ል ምሳሁ ገ/ተክሌ (ትግሬ)
76. የ20ኛ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ — ኮ/ል ሰመረ ተክሉ (ትግሬ)
77. የ22ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ኮ/ል ወ/ጊዮርጊስ ተክላይ (ትግሬ)
78. የ23ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ብ/ጀ በላይ ስዩም (ትግሬ)
79. የ24ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ብ/ጀ ፍስሀ ወርቅነህ (ትግሬ)
80. የ24ኛ ክ/ጦር የጤና ኃላፊ — ሎ/ኮ ዘሚካኤል ብርሀኔ (ትግሬ)
81. የ25ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ብ/ጀ አሰፋ ቸኮል (ትግሬ)
82. የ25ኛ ክ/ጦርምክትል አዛዥ እና የሎጅስቲክ ኃላፊ — ኮ/ል ገ/ሊባኖስ ገ/ጊዮርጊስ (ትግሬ)
83. የ32ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ብ/ጀ ገ/መስቀል ገ/እግዚአብሄር (ትግሬ)
84. የ32ኛ ክ/ጦር ምክትል አዛዥ እና የፋይናንስ ኃላፊ — ኮ/ል መሃሪ በየነ (ትግሬ)
85. የ32ኛ ክ/ጦር የጤና ኃላፊ — ሌ/ኮ ተክሊት ገ/ህይወት (ትግሬ)
86. የ33ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ብ/ጀ ጋይም መሸሻይ (ትግሬ)
87. የ33ኛ ክ/ጦር የኢንዶክትሪኔሽን ኃላፊ — ሻ/ል መብርሀቶም አብርሀ (ትግሬ)
88. የተዋጊ መሀንዲስ ክ/ጦር ዋና አዛዥ — ብ/ጀ ሙሉ ግርማይ (ትግሬ)
89. የተዋጊ መሀንዲስ ምክትል አዛዥ — ኮ/ል ሰመረ ገ/እግዚአብሄር (ትግሬ)
90. የተዋጊ መሀንዲስ ክ/ጦር ማሰልጠኛ ዋና አዛዥ — ኮ/ል አደም ትኩ (ትግሬ)
የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሚባለውንና የሰላም አስከባሪ ኃይል የሚባለውንም እንደሚከተለው በትግሬዎች ብቻ የተያዘ ነው፤
91. የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ —ብ/ጀ መአሾ ሀጎስ (ትግሬ)
92. የአየር ኃይል የዘመቻ እቅድ መምሪያ ኃላፊ—ኮ/ል ደሳለኝ አበበ (ትግሬ)
93. የማዕከላዊ የአየር ምድብ ዋና አዛዥ — (ኮ/ል ሰለዎን ገ/ስላሴ ትግሬ)
94. የማዕከላዊ የአየር ምድብ ዘመቻ ኃላፊ — ኮ/ል ጸጋየ አረፈአይኔ (ትግሬ)
95. የምዕራብ አየር ምድብ 3ኛሚሳይል ክንፍ አዛዥ — ሻ/ል ገ/እግሂአብሄር ኅ/ስላሴ (ትግሬ)
96. የምዕራብ አየር ምድብ የ301ኛ አየር መቃወሚያ አዛዥ— ሻ/ል ዝናቡ አብራሃ (ትግሬ)
97. የምዕራብ አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የኦፕሬሽን ኃላፊ—ኮ/ል ኪዱ አሰፋ (ትግሬ)
98. የምዕራብ አየር ምድብ አዛዥ እና የኦሎጅስቲክ ኃላፊ — ሌ/ኮ ክብሮም መሀመድ (ትግሬ)
99. የሰሜን አየር ምድብ ዋና አዛዥ — ኮ/ል ኃይሌ ለምልም (ትግሬ)
100. የሰሜን አየር ምድብ ምክትል አዛዥ እና የአስተዳደርና ፈይናንስ ኃላፊ—ኮ/ል ጸጋየ ካህሳይ (ትግሬ)
101. የምስራቅ አየር ምድብ ዋና አዛዥ—ኮ/ል አበበ ተካ (ትግሬ)
102. የምስራቅ አየር ምድብ ዘመቻ ኃላፊ — ኮ/ል ሙሉ ገብሌ (ትግሬ)
103. ካሳ የምስራቅ አየር ምድብ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ክንፍ አዛዥ — ሻ/ቃ ጸጋ ዘአብ (ትግሬ)
104. የምስራቅ አየር ምድብ ዘመቻ ምክትል ኃላፊ — ሻ/ቃ ሀፍቶም ዘነበ (ትግሬ)
105. በደቡብ ሱዳን አብየ ሰላም ማስከበር የ8ኛ ታንከኛ ሻምበል አዛዥ— ሻ/ቃ ወልደ ገሪማ (ትግሬ)
106. በደቡብ ሱዳን አብየ ሰላም ማስከበር ምክትል የሃይል አዛዥ —ብ/ጀ ህንጻ ወ/ጊዮርጊስ (ትግሬ)
107. በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር 9ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ —ኮ/ል ጽጋቡ ተወልደ (ትግሬ)
108. በደቡብ ሱዳን አብየ ሰላም ማስከበር 10ኛ ሻለቃ አዛዥ — ኮ/ል ገ/ህይወት አደራ (ትግሬ)
109. በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር 17ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ አዛዥ — ኮ/ል መለሰ ብርሀን (ትግሬ)
110. በዳርፉር ሰላም ማስከበር ድጋፍ ሰጭ ቡድን አስተባባሪ — ኮ/ል ዮሴፍ አሮን (ትግሬ)
111. በዳርፉር የ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም ማስከበር ሻለቃ አዛዥ — ኮ/ል ተክላይ ወ/ጊዮርጊስ (ትግሬ)
112. በዳርፉር የ13ኛ ሞተራይዝድ ሰላም ማስከበር ሻለቃ የዘመቻ አዛዥ —ሻ/ቃ ሀጎስ ነጋሽ (ትግሬ)
እንግዲህ! ከፍ ሲል ከቀረበው ዝርዝር ማስረጃ ማየት እንደሚቻለው በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት፣ በአየር ኃይል፣ በአጋዚ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስና የፌዴራል ፖሊስ በሚባለው ውስጥ በየ ንዑስ ክፍሉ ካሉ አስር የአዛዥነት መደቦች መካከል ቢያንስ ዘጠኙ በትግሬዎች የተያዙ ናቸው። ያፈጠጠው እውነታ ይህ ሆኖ ነው እንግዲህ ነውረኛው ስዩም መሥፍ «ጀኔራ ሳሞራ ጠቅላይ ኢታማጆር በመሆኑ ብቻ ነው የአገር መከላከያ ሰራዊት የወያኔ ሰራዊት ወይንም የሕወሓት ሰራዊት ተብሎ እየተጠራ ያለው» ሲል  ሁሉ ደንቆሮ መስሎት ባደባባይ ሕዝብ  የሚዋሸውና የሚያታልለው!
Filed in: Amharic