
እነ ንግስት የታሰሩት በቅርቡ ከእስር የተፈታውን አጋዬ አድማሱን ጎንደር አየር ማረፊያ በመቀበል ላይ እያሉ ነው። አጋዬ አድማሱን ለመቀበል የወጣውን ሕዝብ ያሰረው መከላከያ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አዘዞ መከላከያ ካምፕ ይገኛሉ።
የጎቤ መልኬ ምክትል የሆነውን አጋየ አድማሱን ሲቀበሉ ንፁሁን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ይዘው እንደነበር የገለፁ ሲሆን መከላከያ ሰራዊቱም “ይህን ሰንደቅ አላማ የያዘውን እንጠይቃለን” ማለቱ ታውቋል።