>

ነገረ ባድመ:- የህወሃት ፕላን A አና ፕላን B [የሰሜኑ ቋያ -  የብአዴን አመራር]

ነገረ ባድመ
            (የ ህውሀት Plan A ና Plan B
            የሰሜኑ ቋያ  የ ብአዴን አመራር
ህወሃት  ውስጥ  የመሽገውና ከእኔ  በላይ ብልጣብልጥ  የለም የሚለው  ተስፋፊው  ቡድን  በእነ  ስዬና  ፃድቃን ፕላን  አርቃቂነት  በኤርትራ  ጉዳይ  ፕላን  A  እና  ፕላን B አዘጋጅቶ  እንቅስቃሴ  ላይ  መክረሙ  ይታወቃል
 ፕላን A – በአልጀርሱ  ስምምነት መስረት  የድንበር ኮሚሽኑን  ውሳኔ ተቀብሎ  አሁን  በተለያዩ  የኢትዮጵያ አካባቢዎች  ያለውን  በተለይም የኢኮኖሚ  መገለል  በዚህ  በኩል  ከሻዕቢያ  ጋር  ስምምነት  በመድረስ  ከህዝባችን  የሚነሱትን  ጥያቄዎች ማስተንፈስ  የሚል ሲሆን ለዚህም  ፕላኑ  ተግባር ላይ  ይውል  ዘንድና በኢህአዴግ  ስራ  አስፈፃሚ  ይወስን  ዘንድ  ከተናጠል ቅስቀሳ  እስከ  በህዝብ መድረኮች  አጃንዳ እንድሆን ህወሃት  ያልፈነቀለው  ድንጋይ ያልወጣው ተራራና  ያልወረደው  ቁልቁለት  የለም :: ባደረገውም  ጥረት  መስረት  የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ  ያለምንም ልዩነት  ተቀባይነት አገኘ ህወሃትም  ደስ አላት::
ነገር  ግን  ገና ከመጀመሪያውም  ከእኔ በላይ  ብልጥ  የለም በሚል  የሞኝ ሃሳብ የተጀመረው ውጥን ካልታስበውና  በደስታ ብዛት  ይፈነጥዛል  ከተባለው ከትግራይ ህዝብ እስከ እራሱ  የህወሃት  አባላት ድረስ ትልቅ ተቃውሞ  ሲገጥመው  በአንድ ጀንበር ውስጥ  ሃሳቡን ቀይሮና በእራሱ በህወሃት አርቃቂነት ያለምንም ልዩነት  የተወስነን  ሃሳብ ያላየና ያልስማ  በመምስል ሽምጥጥ  አድርጎ ክዶ  ከትግራይ ክልል የምትስጥ ስንዝር መሬት አትኖርም በሚል  መግለጫ ነው  መላገጫ  ነገር  አወጣ ::  እኛም  እኛስ  እንተዋወቃለን  ይህንን ባህሪ  ለማያውቁት ስዎች ግን ይህንን ያህል  ለትዝብት ሙውደቃችሁ  እናንተ ባታፍሩም እኛ አፈርንላችሁ እናንተው  አመጣችሁት  እናተው አስወሰናችሁ  እናንተው ተቃወማችሁ  ይገርማል  ብለን ዝም እንዳልን ይሄው ሞኝና  ብልጣብልጥ ነኝ  ባዩ  ቡድን አሁን ደግሞ ሌላ አድስ ፕላን Bን  ይዞ  የኢህአዴግ  አመራርን  ውስጥ ለውስጥ ለማሳመን ቅስቀሳ ጀምሯል::
ፕላን B > የኢትዮጵያ ህዝብ ስንዝር መሬት ከምትስጥበት ህይወቱን ቢያጣ  ይሻለዋል ስለዚህ  ከኤርትራ መንግስት ጋር  እኛ ባልነው መስረት  የማይስማማ ከሆነ  የህዝቡም  የስራዊቱንም ስሜት ስናጠናው ለሉዓላዊነቱ  መስዋዕትነት መከፈል የሚችል ስለሆነ  በድፕሎማሲው በኩል ስፊ ስራ እንስራና  ምክንያት በመፍጠር  ለአንደየና ለመጨረሻ ጊዜ  ጦርነት አድርገን የሻዕቢያን መንግስት በማስወገድ ለእኛም ለቀጠናውም ተስማሚ የሆነ ስርዓት እንድፈጠር እናድርግ ይህንንም የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ውሳኔ  ይስጥበትና  ከወድሁ ዝግጅቶች  ይደረግ የሚል ነው
    ሃሃሃሃሃሃ………ይህ ሃይል በፍፁም ከባለፉት ተሞክሮዎቹ  የማይማር ስለሆነ ከእራሱ በስተቀር  የሌላውን ስሜትና ስነ ልቦና ማወቅና  መገምገም አይችልም  አይወድምም በመሆኑም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ  ፕላን Bን እፈፅማለሁ ማለት ለእኔ ከዕቃቃ ጫወታ ለይቸ አላየውም ምክንያቱም በእነዚህ ስግብግብ ዘረኛ ሙስኛ   ተስፋፊዎች ችግር ፈጣሪነት በተፈጠረው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መሻከር ምክንያት::
 ስለሆነም አሁን ላይ ይህንን ቅዥታችሁን አቁሙና  እስኪመጀመሪያ የቤት ስራችሁን ጨርሱ  ከአጎራባች አገር ጋር ይቅርና ከጎረቤት ወንድም ክልልና ህዝብ  ጋር የገባችሁትን የመሬት ወረራና  በአገር አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆናችሁበትን የሙስናና  የአድሎ ችግሮችን  በይቅርታና  በህግ አግባብ  መፍትሄ እንድስጡ አድርጉ  በተለይ በተለይ  በእናንተ ብቻም ሳይሆን በተከታዯቻችሁም  እየታዬ ያለውን ትልቁን ቫይረሳችሁን  ለጎረቤት ክልልም ሆነ ለጎረቤት አገር  ያስቸገረውን በሽታችሁን “ከእኔ  በላይ ብልጥ የለም ”  የሚለውን ደዌ  ወይ ታከሙት ወይም ተፀበሉ
  ካልሆነ በተለይ ከእናንተ በእጅጉ  የሚበልጠውንና የምንሳሳለትን የትግራይን ስፊ ወንድም ህዝብና መላውን የኢትዮጵያን ህዝብ ልክ  እንዳለፉት ጊዜያት በአገር  ተወረረ የሞኝ ቅስቀሳ እሳት ውስጥ  መክተት የሚቻልበት ሁኔታ ያለ አይመስልኝም  ደግሞም እርግጠኛ  ነኝ  አይሳካም አይደለም  ኢህአዴግ ሌላ  ምድራዊ ሃይል ቢያጅባችሁም  አይሆንም:;
   ዛሬን በዛሬ  መነፀር እንጅ በትናንት መነፀር ማየት የመነፀሩ ችግር ሳይሆን የተጠቃሚውን የሁኔታ ግምገማ  ችግርና ቁሞ ቀርነት ብቻ  ነው የሚያሳየው::
    አስር ጊዜ  ለካ አንድ ጊዜ ቁረጥ ይላል  ደጉ  የአገሬ ስው!!
          መልካም ቀን!!
Filed in: Amharic