>

አለም አቀፉ ማህበረሰብ ተስፋ የቆረጠባቸው ሳልቫ ኬርና  ዶ/ር ሪክ ማቻር  ትክክለኛውን የእርቅ ሰው አገኙ!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

አለም አቀፉ ማህበረሰብ ተስፋ የቆረጠባቸው ሳልቫ ኬርና  ዶ/ር ሪክ ማቻር  ትክክለኛውን የእርቅ ሰው አገኙ!!!

ቬሮኒካ መላኩ
እነዚህ ሰዎች ፕሬዚደንት ሳልቫ ኬርና  ዶ/ር ሪክ ማቻር ናቸው።  እነዚህን ሁለት ሰዎች የአፍሪካ ህብረት ፣ ኢጋድና  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማስተቃፍና ማስታረቅ አቅቷቸው ሰልችቷቸው ትተውት ነበር።
ፕሬዚደንት ሳልቫ ኬር ህውሃት የሚባለውን ድርጅት ከሚጠሉት የአፍሪካ ቀንድ መሪዎች ዋናው ነው። ፕሬዚደንቱ የኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማሪያም የልብ ወዳጅ እንደሆነ እስካሁንም ይነገራል። ጁባ ከተማ ላይ ለኮሌኔል መንግስቱ መኖሪያ ቪላ በስጦታ እንደሰጠው በአንድ ወቅት ቢቢሲ ዘግቧል።
እነዚህን ሁለት የቀጠናው ጥለኞች እንዲያስታርቅ በኢጋድ ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተመድ የተመደበው ስዩም መስፍን ነበር።
በምንም ጉዳይ ላይ ተስማምተው የማያውቁት ፕሬዚደንት ሳልቫ ኬርና ደ/ር  ሪክ ማቻር  በስዩም መስፍን የአደራዳሪነት እውቀት እጥረት ተስማምተው ቅሬታቸውን አቀረቡ።  ሁለቱም መሪዎች ስለስዩም መስፍን ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ከጠቀሷቸው ምክንያቶች ውስጥ:
1~ ስዩም መስፍን የእንግሊዚኛ ቋንቋ እጥረት አለበት ።
2ኛ~ ጆሮው በደንብ አይሰማም።
3ኛ~ ስዩም መስፍን በአደራዳሪነት ከተመደበ በኋላ ግጭታችን ጨመረ እንጅ አልቀነሰም የሚል ነበር።
በነገራችን ላይ:-
 አቶ ስዩም መስፍን የአልጀርሱ ስምምነት “የባድሜ መሬት ለኢትዮጵያ እንዲሰጥ ተወስኗል” ብሎ በኢትዮጵያ ቴሌቪን በኩራት የተናገረ
– እንግሊዝኛ የማይገባው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይና አሁን ድረስ የቻይና አንባሳደር ሆኖ የሚሰራ ወንጀለኛ ነው ።
– አቶ ስዩም መስፍን በኢትዮጵያ ብሄር ብሄረስቦች ውስጥ ግጭት በመፍጠር ህዝብን ከህዝብ በማጫርስ ልምድ ያለው አማሳኝ በመሆኑ ደቡብ ሱዳንንም ለማበጣበጥ የተላከ እንጂ ለማስታረቅ የሄደ አልነበርም ።
– አሁንም የትግራይን ህዝብ ከቀሪው ኢትዮጵያውያን ጋራ ለማጋደል ተነስ ታጠቅ በማለት ላይ ይገኛል።
ወደ ቀደመ ነገራችን ስንመለስ – ዛሬ ይሄው እነዚህ አለም አቀፉ ማህበረሰብ ተስፋ የቆረጠባቸው የፖለቲካ ጉሩዎች ትክክለኛውን ሰው አግኝተው የታረቁ ይመስላሉ።
Filed in: Amharic