>

"ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአማርኛ ስነ ጽሁፍ" (ተባባሪ ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ገብሬ)

ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ሀገር ግንባታ

ተባባሪ ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ገብሬ
“ለአዳም፤ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በጊዜ ውስጥ አይደለም የተፈጠሩት። ከጊዜ ጋር አብረው ነው የተፈጠሩት”
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ “ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በአማርኛ ስነ ጽሁፍ” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው መድረክ ላይ የጸጋዬ ገብረመድህንና የአዳም ረታን ስራዎችን ዋቢ በማድረግ ስለ ብሔርተኝነትና ሀገር ግንባታ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቧል። የዝግጅቱ ሙሉ የቪዲዮ ፋይልና በዚህ ገጽ ላይ ለንባብ እንዲመች ተደርጎ የተዘጋጀ ጨመቅ (summary) ከዚህ በታች ቀርቧል።
***
* Nationalism የሀሳብ፣ የእምነትና የ principle ጣጣ ነው። እነዚህ ሶስት ጉዳዮች ረቂቅ ናቸው። Metaphysical ናቸው፡ ስለዚህ representation ይፈልጋሉ። Representation በኪነት ወይንም በስነ ጽሁፍ ውስጥ ሁለት መልክ አለው። አንደኛው ውክልና ነው። መወከል። የተጠራ አለ፡ ያልተጠራ አለ። ሁልጊዜም nation building የሚያከራክረውና national myth የሚያስፈልገው represent ያልተደረገ ወገን ወይንም ሰብዓዊ እሴት ስለሚኖር ነው። ጠንቅቀን አደረግን ብንል እንኳን አዲስ ትውልድ ሲመጣ አዲስ እሴትና አዲስ interest ይዞ ስለሚመጣ ማደስ ያስፈልጋል። ይሄን ለመስራት ስነ ጽሁፍ ጥሩ አውድ ይሰጣል። ሁለተኛው representation አስተማስሎ የሚባለው ነው። አስተማስሎ ማለት abstract እና complex የሆኑ ሃሳቦችን በምስል ማቅረብ ማለት ነው።
* ከሃምሳዎቹና ስድሳዎቹ ጀምሮ የ Ethiopian Nationalism ታውኳል። እስካሁንም እንደታወከ ነው። ብዙ ጥያቄዎች ተነስተውበታል። ብዙ እሴቶች አጥፍቷል። ባጠፋቸው እሴቶች ምትክ አዲስ እሴት አልገነባም። ትውልድ ተለዋውጧል። ነባሩ ትውልድ በነቀለው እሴት ምትክ አዲስ ስላልገነባ አዲሱ ትውልድ ያለ እሴት ነው የተቀመጠው። ነባር እሴቶች romanticize ይደረጋሉ። እነዛ እሴቶች ላይ ነው nationalism የተመሰረተው። ሮማንሱ ሲፈርስ አብሮ ናሽናሊዝሙም ፈርሷል። አዲሱ ትውልድ አዲስ nationalism ያስፈልገዋል። ይሄን nationalism የሚሰሩለት ደግሞ ከያንያን ናቸው።
* የሌላ ሀገራት ልምድ ብናይ ከያንያን successful ናቸው። እኛ ጋር ግን አይደሉም። ለምን? የቋንቋ መብዛት እርግማን ሆኖብን ይሆን? እንደዛም እንዳይባል Papua New Guinea የምትባል ሃገር 3 ሚሊየን ሕዝብና 700 ገደማ ቋንቋ አላት። ነገር ግን In harmony ነው የምትኖረው። ሕንድ ከአንድ ሺህ በላይ ቋንቋና ከአራት በላይ እዛው የበቀሉ ሃይማኖቶች አሏት። እምነት ላይ የተመሰረት የ caste system አላት። ሕንድም በግጭትና በመከፋፈል የታወቀችበት ጊዜ ነበር። Tagore የሚባል ሰው ነው የዋጃት። Inian soul የሚባለውን የሰራው Tagore ነው። Tagore በስነ ጽሁፉ አማካይነት transpersonal እና transhistorical ሆኗል። successful ነው። እነሱ ጋር የተፈወሰው የቋንቋ በሽታ እኛ ጋር ለምን አልተፈወሰም?
የዛሬ 80 አመት ሕንድ በግጭት የታወቀች ነበረች። አሁን ሕንድ የአለምን economy እና euro centric የሚባለው የሚጫነውንና global south south የሚባለውን movement የምትመራ ሀገር ነች። እዚህ ውስጥ የ Tagore እጅ ትልቅ ነው። እኛ ሀገር የ Tagore አይነት ሰው ጠፋ ወይ?
* የኢትዮጵያ የስነ ጽሁፍ ቀኖና (literary canon) ብንሰራ ከላይ ከሚቀመጡት ሰዎች ውስጥ እንደ ስብሃት፣ ጸጋዬ፣ በዓሉና ሰለሞን አፋቸውን የፈቱት በአማርኛ አይደለም። ግን ለምን በአማርኛ መጻፍ መረጡ? የ cultural dominance ጣጣ ሆኖባቸው አይደለም። ወይንም ሰፊ የሆነ audience ፍለጋ አይደለም። እነዚህ ከያኒያን በእንግሊዝኛ እና በፈረንሳይኛ ጥሩ አድርገው ይጽፋሉ። በነዚያ ቋንቋዎች ቢጽፉ ሰፊ የሆነ audience ማግኘት ይችሉ ነበር። ግን አላደረጉትም። በነዚህ ሰዎች አማካኝነት የአማርኛ literature የ ኢትዮጵያ literature መሆን አይችልም ወይ?
* የnationalism ጉዳይ የቋንቋ ጉዳይ ነው ካልን እዛ ውስጥ የ nation building project የለም ወይ? እሱን ሳናነብ nation building መስራት እንችላለን? Ethiopian nationalismን ለመገንባት pop culture, literary art እና ሌላውም art መስራት አለበት። በፖለቲካ ዲስኩር መስራት አይቻልም። Politics ሊሰራ የሚችለው ሀሳብን በሃሳብ ማስረዳት ነው። Art ግን ሃሳብን ፈርክሶ concretely ቀለም እና ቅርጽ ኖሮት ሰው እንዲኖርበት አድርጎ ነው የሚሰራው።
በሀገር ግንባታ ውስጥ ጸጋዬና አዳም በንጽጽር 
* ሁለቱም ጥልቅ የሆነ ጊዜና mythical thinking አላቸው።
* ሁለቱም የተቃራኒዎች መቃለጥ (fusion of opposites) ላይ ይመሰረታሉ።
ልዩነታቸው
* ጸጋዬ ተሰርቶ ያለቀ symbol ይፈልጋል። የጸጋዬ narrative ወይንም national myth ሙከራ በግዙፋን እሴቶች ላይ ለምሳሌ በአባይ፣ በአዋሽ፣ በምኒልክ፣ በዓድዋ፣ በቴዎድሮስና በዘርዓይ ታሪክ ላይ ይመሰረታል። እዛ ላይ ተመስርቶ seriously የሚፈልገውን ይሰራል።
አዳም ያን ይሽርና በጥቃቅን ነገሮች ላይ ይመሰረታል። ጸጋዬ ሕሩያንን እና ጉልሃንን ነው የሚፈልገው። አዳም ምድር ነው የሚመጣው። ጥቃቅን ሲባል በማሕበራዊ ሕይወታችን ውስጥ ስፍራ የማንሰጣቸውን values ነው ወደ center የሚያመጣው። ለምሳሌ hero መፍጠር ሲሞክር heroውን ቴዎድሮስ ወይንም ምኒልክ ሳይሆን ሁሌ ከምንሰማው ተረት ወይንም ተንኮለኛ ከሆነ character ስንዝሮን ይመለምላል። እና ያራግፋል ይህን ባህሪውን። ስም ይቀይርለትና mythic figure ያደርገዋል። ከማይረባ የተረት figure ወደ mythic figure ይቀይረዋል። ስንዝሮ ረዥም ታሪክ አለው። ወደኋላ አምስት ሺህ አመት አለው ወደፊትም ብዙ ዘመን ይገፋል። የነባሩ የ solomonic ሳባ myth immemorial past እንጂ future አልነበረውም። ጸጋዬም አዳምም ሲሰሩ ይሄንን future ያስባሉ። Guaranteed ነው።
* ጸጋዬን ጨምሮ ነባር ከያኒያን hero ሲሰሩ የሚመርጧት እናት በተለመደው የ feminine value የተሟላች መሆን አለባት። ንጹህ ቦታ የተገኘች፣ ከማሕጸን ጀምሮ የተጠበቀች መሆን አለባት። የአዳም character ግን ጉልት ላይ የምትውል፡ እግሯ ንቃቃት የተሞላ፡ ከነባሮቹ ባሮች የከፋ ድህነት ያላት ይሆንና እሷም ግን እንደነባሮቹ በድንግልና ትወልዳለች።
* ጸጋዬ አባይንን ይጠልፍና ከአባይ የ Ethiopian identity ያሰግራል። አባይ ትልቅ ነው፣ አባይ ጠንካራ ነው። አዳም ደግሞ ጤፍን ይወስዳል። ጤፍ ማለት ከሰብሎች ሁሉ ትንሿ ነች። ከዚህች አንድ ፍሬ ጤፍ አብራክ (ልብ በሉ ጤፍ አብራክ ሲኖረው) እንጀራ እንደሚከፈለው ሁሉ አዳም ኢትዮጵያዊነትን ከዛ ሊከፍል ይሞክራል።
* ጸጋዬ consistent ነው። በሃምሳዎቹና ስድሳዎቹ ሃገር በታመሰ ጊዜ ጸጋዬ ከሮማንሱ አልወጣም። የጸጋዬ ኢትዮጵያ ከምድር በላይ ነች። አትለወጥም።
አዳም እስከ 1983 ድረስ በ universal humanism የሚያምን ሰው ነው። የሰው ልጅነትና የሰው ልጅ ዕጣ ፈንታ ነው የሚያሳስበው። Human condition ነው ጉዳዩ። ከ 83-85 ለውጥ በኋላ ቻርተር ሲጸድቅ፣ ሌሎች የምናውቃቸው ነገሮች ሲፈጠሩ በአስተሳሰብና በአካሄድ shift አደረገ። በፊት ሲሰራ myth ይሰራል። የሚገለገልበት myth ግን universal humanismን ሊወክል የሚችል myth ነው። ለምሳሌ እንቁላል። Cosmic egg ከሚባለው myth የሰው ልጅን ዕጣ ፈንታ ይነድፋል። እሱን ነው ትቶ የመጣው። ይሄን symbol መተዉ መዓት ነገር ይለውጣል። አንደኛ ለትችት ይዳረጋል። አፍሪካውያን የምዕራባውያኑን ሃሳብ መተው ሲፈልጉ የዚያን ነገር አቻ እዚህ ማግኘት አለባቸው። እዚህ ካላገኙት ያንሳሉ። እና በባዶ አርበኝነት (superficial nativism) ይተቻሉ። አዳም እዚያ ውስጥ ላለመውደቅ ማጥናት ነበረበት። አዳም popular ከመሆኑ በፊት ሰላሳ ምናምን አመት ሰርቷል። ሲያጠና ያገኘው በእንቁላል ፈንታ ጤፍን ነው። ጤፍ በብዙ መንገድ ለ Ethiopian nationalism ጥሩ የሆነ symbol ነው።
አንደኛ ጤፍ racially complex ነው።
ሁለተኛ ጤፍ sexually hermaphrodite ነው።
ሶስተኛ ጤፍ በዕድሜ ሩቅ ነው።
አራተኛ ጤፍ ስሙ የመጣው ‘ጠፋ’ ከሚለው ነው። ነገሯ ራሷ ትንሽ ነች። ጠፋ ማለት absence ነው። Philosophically ቢታይ ጤፍ የምትባለው ነገር ራሷ represent የምታደገው absenceን ነው። The presence of absence. Absence ደግሞ metaphysical ነው። በኛ case ግን ጤፍ የምትወክለው መኖርን ሳይሆን አለመኖርን ነው። ገበሬው አለመኖርን ይዘራል ያጭዳል። ሴቶች ደግሞ ከዚህ ያለመኖር እንጀራን ያህል ነገር ይጋግራሉ። እና እኛም ስንመጣ ካለመኖር ነው። ይሄ mythological መሰረት አለው። ምክኒያቱም ሁሉም mythology the beginning of all beginnings መሆን ይፈልጋል። መነሻ መሆን ካለበት ደግሞ ከእመ አልቦ (ex nihilo) መምጣት አለበት። አዳም Ex nihiloን በጤፍ አማካይነት ሰራ። ጤፍ ብዙ ነገር ነው። 70% ኢትዮጵያዊ ጤፍ እንደሚበላ ጥናቶች ያሳያሉ። በስፍራም፣ በጊዜም፣ በውክልናም አስቡት። በየትኛውም መንገድ ጤፍ ጥሩ symbol ነው።
* ጸጋዬ national mythology ሊሰራ ሲፈልግ የጋራ ጠላት ይመለምላል። Common enemy በብዙ national myth እና national literature ውስጥ መሰረታዊ ጉዳይ ነው። ምክኒያቱም የውጪ ጠላት ሲመጣ ወደ አንድ ይሰበስበናል። ስለዚህ ለ national identity ጥሩ ነገር ነው። ቴዎድሮስ፣ ምኒልክ፣ ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት ወዘተ በዚያ መንፈስ ነው የተሰሩት።
አዳም ከዚህ ተቃራኒ ነው። የኛ ጠላት ራሳችን ነን። እንደ ማሕበረሰብም እንደ ግለሰብ አንድ entity የሁለቱም ማደሪያ ነው። ስለዚህ ራሳችንን እንድናሸንፍ ነው የሚያደርገው።
የNationalism ጉዳይ time depth ይፈልጋል። ጸጋዬና አዳም time depth ሰርተዋል። Time depth ካለው እዛ ላይ የሚተከል nationalism የሚነቃነቅ አይደለም። National identityውም ጽኑ ነው። የሰሩበት material ደግሞ local ነው። ከየትም ቦታ የመጣ ሳይሆን indiginous ነው።
ለአዳም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት በጊዜ ውስጥ አይደለም የተፈጠሩት። ከጊዜ ጋር አብረው ነው የተፈጠሩት።
ከጊዜ ጋር ከተፈጠሩ አንደኛ በ Anderson ቋንቋ immemorial past አላቸው። በጣም ሩቅ የሆነ። ሁለተኛ የማይገመት future አላቸው። unpredictable የሆነ። የጊዜውን ጽንፍ perfectly ይዘውታል።
ይሄ ለ ሀገር ግንባታ fertile የሆነ አፈር ነው።
***
ሙሉ የቪዲዮ ፋይሉን ከስር ባለው ሊንክ መመልከት ይቻላል።
Filed in: Amharic