>
5:30 pm - Sunday November 2, 6206

ለቅማንት ህዝብ ዘመኑ የመደመር ነዉ እንደመር!!! (ሚኪ አምሃራ)

ለቅማንት ህዝብ ዘመኑ የመደመር ነዉ እንደመር!!!
(ሚኪ አምሃራ)
የቅማንት ብሄረሰብ የራሱ አስተዳደር እንዲኖረዉ ተፈቅዷል፡፡ ጥሩ እራስን በራስ ማስተዳደር ምንም ችግር የለዉም የህዝብ ፍላጎት እስከሆነ ድረስ፡፡ አሁን የምንፈልገዉ የቅማንት ማህበረሰብ በትምህርት፤ በጤና፤ በምርት፤ እንዲሁም በማንኛዉም አይነት የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ኑሮዉ ተሻሽሎ ነዉ ማየት የምንፈልገዉ፡፡ ከአማራ ወንድም እህቶቹ ጋር ባካባቢዉ ያለዉን ዉስን ሪሶርስ አብሮ በመጠቀም የተሻለ ህብረተሰብ እንዲኖር ነዉ የምንፈልገዉ፡፡
ምእራብ ጎንደር ተብሎ በተከፈለዉ አዲስ ዞን ዉስጥ በመተማ ወረዳ ይመስለኛል 2 ጎጦች ወይም ቀበሌወች የቅማንት ማህበረሰብ በዛ ብሎ የሚኖሩበት አለ እና እነሱ ቀበሌወች ይጨመሩልን ነዉ ጥያቄዉ እስከገባኝ ድረስ፡፡ እኒህ ቀበሌዎች ግን ሌላ ዞን ዉስጥ ያሉ ከቅማንት አስተዳደር ጋር በጆግራፊ የማይገናኙ ናቸዉ፡፡
ዞሮ ዞሮ መተማ ዉስጥም ሆነዉ የሚኖሩት ከአማራ ወንድም እህቶቻቸዉ ጋር ነዉ፡፡ የቅማንት ልዩ አስተዳደር ዉስጥም እኮ አማራ የሚበዛበት ጎጥ አለ ግን በጆግራፊ ከሌላኛዉ ዞን ጋር ካልተገናኘ እዛዉ ባሉበት በቅማንት አስተዳደር ይተዳደራሉ፡፡ የቅማንት ህዝብ በልቶ የሚያድረዉን በልተዉ ያድራሉ፡፡ የቅማንት ማህበረሰቦችም ምእራብ ጎንደር ዞን ዉስጥ አማራዉ እንደሆነዉ ይሆናሉ፡፡ አልፎ ሄዶ ሌላ ዞን ዉስጥ እኔ ላስተዳድር ማለት ግን ግራ የገባዉ እና ሁለቱን ህዝቦች ለማቆራረጥ የሚደረግ ነገር ነዉ፡፡
በተለይ ይህ ኮሚቴ የሚባለዉ ቡድን የሁለቱን ህዝቦች ጠብ ለምን አጥብቆ እንደሚፈልገዉ ግራ ይገባል፡፡ ይህ በባህል፤ቋንቋ እና ስነልቦና ለመለየት የሚከብድ ህዝብን ዛሬ ይሄን ጎጥ ያን ጎጥ እያሉ ህዝብን ለማናከስ የሚደረግ
ተራ ሴራ ህዝቡ መገንዘብ አለበት፡፡ መጠቀሚያ ከመሆን እናቁም፡፡ ዞሮ ዞሮ ሁለቱም ህዝቦች ህልዉናቸዉ ወደድንም ጠላንም አንድ ነዉ፡፡ ዛሬ ቢከፋፍሉንም በክፉ ቀን አብረን መቆማችን አይቀርም፡፡ ምክንያቱም ለሁለቱም ማህበረሰብ መቀሌወች እንደማይሆኗቸዉ ይታወቃል፡፡ ሁሉም ፖለቲካ ነዉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ይሄ ኮሚቴ የሚባል ሲጀምር እርስ በእርሱ እንኳን የማይስማማ አስተዳደር መስርቱ በተባለ ማግስት ኮሚቴዉ በስልጣን ተጣልቶ አሁን አንዱ አንዱን እስከ መገዳደል ድረስ እየተፈላለጉ ነዉ፡፡ እንግዲህ እኒህ ናቸዉ ለህዝቡ የሚያስቡት፡፡
ስለዚህም ወንድማዊ ምክሬ ምንድን ነዉ ይህ ኮሚቴ የሚባል መልክት ከየትም እየተቀበለ አካባቢዉን ዘላለም አለሙን የጦር ቀጠና ለማድረግ መሞከር ለሁለቱም ህዝቦች አይጠቅምም፡፡ አሁን ሁለቱም ህዝቦች ተያይዘዉ የሚያድጉበትን መንገድ እንጅ በአንድ ክልል ዉስጥ ለዛዉም በአንድ ዞን ዉስጥ ተሰባጥረዉ የሚኖሩ ሰወች ይህ ጎጥ የኔ ያ ጎጥ ያንተ እየተባባሉ መኖሩ ጥሩ አይደለም፡፡ ዛሬ ደቡብ ላይ የምናየዉ ዘግናኝ ነገር በዚህ የተጀመረ ነዉ፡፡
ብአዴንና ህወሃት ከህዝቦች አንድነት ይልቅ ይህን ኮሚቴ ማሽሞንሞን፤ማባበል እና ማገዝ ብታቆሙ ይሻላል፡፡

Filed in: Amharic