>

ድንበር ተሻጋሪው ዘረኝነት በእስራኤል!!! (እሸቴ ካሳ ዘውዱ)

ድንበር ተሻጋሪው ዘረኝነት በእስራኤል!!!
እሸቴ ካሳ ዘውዱ
האם אתם  נתקלתם בבעיות כאל בארץ  תשתפו אותנו  יכול להיות בעבודה או זוגיות.
ገዳዩ ጸጋዬ በርሄ:-
– በጎንደር የተፈፀመውን ግድያና ማፈናቀል  የመሩ ፋሽስት ናቸው
–  በዋልድባ  ገዳም   መናንያን የሀይማኖት አባቶች ግድያ ግርፊያ ተፈፅሞባቸዋል
–  መነኩሲቶቹ ደናግልም በሕወሓት ታጣቂ  ተደፍረዋል  ።
–  የተቀሩት አካለ ጎደሎ ተደርገው ተባረዋል
   ጸጋዬ ከዓመታት በፊት በኤየሩሳሌም
:— የበደኖውን ፣ የአርባ ጉጉን  የአማራ ዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የናንተ ፈጠራ  ነውም ይለዋል ።
በቪዲዮው ተመልከቱት  ኢየሩሳሌም  ላይ ነበር  በኢትዮጵያውያኖች መካከል ቁሞ አላፈረም  ።
ውድ ትውለደ ኢትዮጵያዊ  በእስራኤል ሀገር የምንኖር  ሁሉ ሀቁን እንወቅ ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር  ምን እየሠሩባት እንደሆን ።
ዕትብታችን እና ዘመድ አዝማዶቻችን  አፅም   የተቀበረ  በጎንደር  ነው ።
 ምንም በሌላ ዓለም ሁነን ዜግነታችንም በዕምነትም  ብንለይም ።
ሁለንትናችን  እስራዔላዊ ብንሆንም  ለወደፊቱ ኢትዮጵያ የሚለው  ቃል ከኛ ጋር  እስከትውልድ መለያችን ይሆናል ።
    ልብ በሉት  በዚህ በምስል የምናያቸው ሰዎች  የትግራይ ተወላጆች ናቸው ።
 በኢትዮጵያ የጥቁር አፓርታይዱን ሥራዓት የመሰረቱት የአገዛዙ አባላት ናቸው ።
  እኒህ ሰዎች ደንበር ተሻግረው የመለያየቱን ሥራ ለዓመታት  ቀጥለውበታል ።
  እነዚህ በባለቤትነት የሚመሩት የኢትዮጵያው ገዥ ሕወሓት ለ27 ዓመታት የንፁኃንን ደም እያፈሰሰ ያለው  በተለይ በዚህ ሰዓት በየቀኑ ደረቱንና ግንባሩን በጥይት  እየተቦደሰ የሚገኘው  ዓግዓዚ በተሰኘው  ቅለብ ነፍሰገዳ  መሆኑ ሁላችንም የምናውቀው ነው ።
  በመሀል ተቀምጠው የምናያቸው ጸጋዬ ብርሄ የዘረኛው ሕወሓት ወይም የትግራይ ነፃ አውጭ  ሕወሓት መሥራች ከመሆናቸው በተጨማሪ በሰሜን ጎንደር  ለተፈፀመው ሰብዓዊ ወንጀል ሙሉ በሙሉ እጃቸው ያለበት  በደም የተለወሰ ነው ።
  እኒህ ሰው  በትጥቅ ትግሉ ወቅት መነኩሴ ሁነው በሰሜን ጎንደር  በታላቁ ገዳም በመግባት ከፍተኛ ጥፋት ያደረሱ በዛ በኩል የስለላና የቅድመ ዝግጅት ያደርጉ የነበረ መሆኑ ይነገራል ።
ዋልድባ ላይ የጣልያን ፋሽሽት የሱዳን ድርቡሽ በጎንደር ከፈጸሙት በላይ የተፈፀመውን ግድያና ማፈናቀል  የመሩ ፋሽስት ናቸው ።
በዋልድባ  ገዳም  በወረራ ወደትግሬ መከለሉ ብቻ አይደለም በዛ የሚኖሩት መናንያን የሀይማኖት አባቶ ግድያ ግርፊያ ተፈፅሞባቸው የተቀሩት አካለ ጎደሎ ተደርገው ተባረዋል  ደናግል መናንያን አለም ይቅርብን  ያሉት ጎንደሬ በመሆናቸው ድንግልናቸው በሕወሓት ታጣቂ ረክሷል ተደፍረዋል  ።
 መነኳስት ቆባቸውን እንዲያወልቁ  እና በማዕከላዊ በሚባለው በመሀል አዲስ አበባ  ምድራዊ ገሀነም ስቃይ መከራ ን እያሳለፉ አሁንም በጨለማ ክፍል ላይ የገኛሉ ።
ደርግ ከወደቀም በኋላ የትግራይ የበላይ አስተዳዳሪ ሁነው የሰሜን ጎንደርን መሬት በወረራ  ወደትግራይ ከማስገባታቸውም በተጨማሪ  በሰሜን ጎንደር  በሰሜን አውራጃ እና በወገራ አውራጃ በርካታ ሰዎች መገደልና  መሰወር የርሳቸው ኃላፊነት ነበር ።
 በወልቃይት በጠገዴ አማራ ነኝ ያሉትን ሁሉ የዘር ማፅዳት ያካሄዱት የትግራይ መስተዳድር የነበሩት  እኒሁ ሰውዬ  ናቸው ።
 እኒህ ሰው  ከትግራይ መስተዳድር ከለቀቁ በኋላም  ወደ አዲስ አበባ በሚኒሊክ ቤተ መንግሥት መሽገው የጠቅላይ ሚ/ ር አማካሪ ተብለው ካባ ይደርቡ እንጅ ዋና ሥራቸው የሰሜን ጎንደርን  ሕዝብ የሚታፈንበትን  ባካበቱት ልምድ መነሻ አድርገው ከጎጃም ጀምሮ እስከ ተከዜ ማ  ትግራይ ደንበር  ድረስ ያለውን አፈና በበላይ የሚመሩ  ደንበር ተሻጋሪ ሱዳንም ድረስ የጎንደሬዎችን  ታፍኖ መሰወር የርሳቸው ድርሻ ነበር   ።
በጎጃም ውስጥ በአመለካከታቸው ለሚገደሉ እንደ እነ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ያሉት በትውልድ ቦታቸው እንደ ዕባብ ተቀጥቅጠ  መገደል እኒሁ ሰውዬ የሚመሩት የገዳዩ ቡድን ነው ።
  በዚህ ወቅት  ሕላዌ ዮሴፍን ተክተው የወደዚህ አገር ምጣት አንደምታው ምንድን ነው?
  በሰሜን ጎንደር አፈናውን ግድያውን የዘር መድልኦው  ያስመረራቸው ወደ አደባባይ ወጥተው ሕወሓት አይገዛነም ካሉ በኋላ ነው ።
በዚህ ሀገርም ያ እየተሰማ  ነገሩ በማሕበረ ሰቡ ጥያቄ ሲብላላ  በእስራኤል በብሔረ አማራ   ብአዴን በሚበሰለው  ሰዎችን አስተባብረው በየከተማው ይንቀሳቀስ የነበረው  ተበተነ ሕላዌም  ወደ ሀገር እንዲመለስ ተደረገ  ።
በዚህ አገር ከምንኖረው ትውልደ ኢትዮጵያዊ 95% የመጣነው ከጎንደር ነው ።
እኒህ ሰዎች አብሮ መብላት አብሮ መጠጣት  መዋለድ ምናቸውም አይደል ጎንደሬ የሆነው ሁሉ ለነሱ  ማደር ካልቻለ ጠላት ነው ።
አማረኛ ቋንቋው የሆነ በሙሉ ጠላት ነው  በጥቅም ከተሳሰረው ውጭ ።
 የኒህ ሰውዬ ወደ ዚህ ሀገር መምጣት  ታላቁ ዓላማ  ስለ ጎንደሬዎች ለኔ ተውት ልክ ማስገባት አውቃለሁ ብለው ነው።
 ወደዚህ አገር እንደገቡ ለቃለ መጠይቅ የሰጡት መልስ በርግጥም ኢትዮጵያን የወከሉ አይመስልም የትግራይ ተወካይ እንጅ ስለኢትዮጵያ አንድ አልወጣቸውም ስለ አክሱምና ንግሥተ ሳባ ብቻ ነበር የጠነጠኑት  ።
  ልብ ያለ ልብ ይበል ደንበር ተሻግረውም አብረ እየኖር ያለነው እየመረዙን ነው ።
Filed in: Amharic