>
11:06 pm - Wednesday February 1, 2023

ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ ''ሞት ሊበየንበት ይችላል'' -በሽብርተኝነት ክስ ሞት ተፈርዶባቸው ሞታቸውን የሚጠባበቁ 127 ሰዎች ኣሉ

EthioReference.com: በኖርዌይ ሃገር ውስጥ በኖርዌጂያንኛ የሚታተመው ዳግብላደት የተባለው ጋዜጣና ድረ-ገጽ ”ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን” ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ በሚቀጥለው ሳምንት ሞት ሊበየንበት ይችላል” ሲል ኣውጥቶኣል።
”ባለፈው ሳምንት ለማወቅ እንደተቻለው ዕድሜው 52  የሆነና  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ  የተባለ ኖርዌጂያን ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት ተከሶ በእስር ላይ ይገኛል።” tiltalt for terror በማለት የጀመረው የኖርዌዩ ዳግብላደት ሲቀጥልም…”የኢትዮጵያ መንግስት ቃለ ኣቀባይ እንደሚለው ገንዘብ ኣሰባስቦና ኣጥቂ ቡድን መልምሎ ኣደጋ ለማድረስ ሲሞክር ያዝነው በማለት መከሰሱን ያትትና በበኩላቸው የኖርዌዩ የሰብኣዊ መብት ጥበቃም ሆኑ የዓለም ኣቀፉ ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን በጥብቅ ያወገዙት ሲሆን፣ ኣያይዘውም ለዚሁ ድረ-ገጽ ታሳሪው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ከወትሮው የከፋ እንደሆነም ስጋታቸውን እንደገለጹለት ያወሳል።
Okello Akway (foto priviat form Dagbladet )
 ኢትዮጵያንም ሆነ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት፣ በኣሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ውስጥ የሚገኙትን  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ ”በሚገባ ያውቃሉ” ያሉዋቸውን የሰብኣዊ መብት ተሟጋችና ኖርዌጂያን ፈሊክስ ሆርነ ን  ኣነጋግሮ ድረ-ገጹ ያገኘው መልስ ”ኖርዌጂያኑን ኦኬሎ በሚቀጥለው ሳምንት የሚሰየመው ችሎት ሞት ሊበይንበት ይችላል” በማለት የገለጹ ሲሆን ኣክለውም፣
”በሃገሪቷ ውስጥ በሽብር ወንጀል የሚከሰሱት ዜጎች የሚገጥማቸው የሞት ፍርድ ነው። ነገር ግን እነዚህ ሞት የሚፈረድባቸው ዜጎች ምንም ማስረጃ ያልቀረበባቸው ናቸው። በሽብር ክስ ስለተከሰሱ ብቻ ዕድላቸው ይሄው ነው። በሞት ቀጠና የሚገኙትን ዜጎች የሚዘግበው ዓለም ኣቀፉ ድርጅት በኢትዮጵያ በእስር ቤት ውስጥ በሞት ቀጠና (ሴል) የሚሰቀሉበትን ወይም የሚገደሉበትን ጊዜ የሚጠባበቁ 127  ዜጎች  ይገኛሉ ሲል ፈሊክስ ሆርነ ለድረ- ገጹ ገልጸዋል።
 ሌላው ኣምነስቲ ኢንተርናሽናል ውስጥ የሚሰሩት ጌራልድ ካዶርድ ”የኢትዮጵያ መንግስት ኦኬሎን እንደከሰሰው በሽብር ወንጀል ጦር ሲመለምልና ሲያደራጅ ኣግኝቶት ከሆነ፣ የሞት ቅጣት ይበይኑበታል የሚለው ስጋቴ ነው።የፍርድ ሂደቱን እንደምናየው የሞት ቅጣቱ በፍርድ ቤቱ ይለወጣል የሚል ዋስትና የለንም።” ኣያይዘውም ባለፈው ዓመት 8 ጋምቤላ ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ድርጅት ኣባላቶች በሽብርተኝነት ከሰዋቸውና የሞት ፍርድ በይነውባቸው ሞታቸውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው።”
 ጭፍጨፋ
ኦቻላ ከሽብርተኛ ጋር ግንኙነት እንዳለው ኣላውቅም። ነገር ግን በጋምቤላ ውስጥ መንግስትን የሚቃወም ጠንካራ ተቃዋሚ ድርጅት የለም። መንግስትን ለመቃወም የሚነሱትንም ሽብርተኛ የሚል ስም በክልሉ መንግስት ይለጠፍባቸዋል።
 ኦቻላ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበረ ጊዜ፣ massakre 13. desember 2003. የ 1000 በላይ  የኣባወራዎች መኖሪያ ቤቶች በገዥው ስርዓት ወታደሮች ሲቃጠልና ከ400 የኣኙዋክ ንጹሃን ተወላጆች በጥይትና በስለት ሲታረዱ በስፍራው  ነበር። ይሄንንም ተከትሎ ወደ ደቡብ ሱዳን ስልጣኑን በመተው መሰደዱንና ከዚያም ከቤተሰቡ ጋር  በኖርዌይ ”ትሮንዳሄም” በተባለ ቦታ  በስደተኝነት በመግባትና ፈቃድ ጠይቆ በ2009 ዓ.ም የኖርዌጂያን ዜግነት ተሰጥቶት ነበር።
  ቢሆንም  ከ 2012 ጀምሮ በጋምቤላ ውስጥ በሚከናወነው ሁኔታዎች ይረበሽ ነበር። በዚህም የተነሳ ወደዚያው ኣቅንቶኣል።ማድረግ ግን ኣልነበረበትም።በኣንድ ወቅት በክረምት ወራት የሱዳን የመረጃና ደህንነት ሰራተኞች በሱዳን ጁባ ውስጥ ያለን ኣንድ ሆቴል በድንገት ከበቡት። ከዚያም በውስጡ የነበሩትን የሱን ጓደኞች  ኣስረዋቸው ወደ ኢትዮጵያ  ልከዋቸዋል በማለት ድረ- ገጹ ኣትቶኣል።
ቶርቸር 
በኣሁኑ ሰዓት ኦኬሎ በእስር ቤት ውስጥ ባልተረጋገጠ መረጃ ውስጥ ይገኛል። ይህ ኖርዌጂያን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማወቅ ኣይቻልም።በኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ  የእናትነት እንክብካቤን ማግኘት ህልም ነው።እስረኞች ለቶርቸርና ስቃይ የተጋለጡ  መሆናቸውን ፈሊክስ ሆርነ  ለድረ-ገጹ ኣስረድተዋል።
የኦኬሎን የፍርድ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ሪፖርተር የተሰኘው  ጋዜጣ ችሎቱ  ጁላይ 1 ይውላል ብሎ ቢገልጽም፣ የእኛ Dagbaldet በሲዊድን ያለውን የኢትዮጵያ ኣምባሳደር ለማግኘት ሞክረን ያልተሳካልን ሲሆን፤ ዓለም ኣቀፉን የሰብ ኣዊ መብት ተሟጋች ድርጅትንም ሆነ በኣዲስ ኣበባ ካለውም የኖርዌይ ኤምባሲ ትክክለኛ የችሎት ጊዜውን ማረጋገጥ ኣልተቻለም።
የኖርዌይ የውጭ ጉዳይም ለኣንድ ኣዲስ ኖርዌጂያን በኣደጋ ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ፣ ወይም ኣደጋ በገጠመው ወቅት እንዴት መከላከል  እንዳለበት ከድረ- ገጹ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ መስጠት ኣልፈለጉም።ድረ- ገጹ   ምላሽ በማጣቱም ይመስላል በኮንጎ ውስጥ ኖርዌጂያዊው Joshua French  በሞት ሲቀጣና፣  Shahid Azim  በኣስገድዶ መድፈር ወንጀል ፖኪስታን ውስጥ ተይዞ ሞት ሲፈረድበትም ኣላስጣሉትም በሚል ኣጣቅሰው ያለፉት። ቢሆንም ይላሉ የውጭ ጉዳይ ቃል ኣቀባይ ፍሮደ ኣንደርሰን፥ እስከኣሁን ከተከሳሹ ስለ ፍርድ ውሳኔውንም  ሆነ  ስለ ችሎቱ ቀን የምናውቀው የለም በማለት ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ያለው የኖርዌይ ኣምባሳደር  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላን በተመለከተ ተደጋጋሚ  ጥያቄዎችን ለኢትዮጵያ መንግስት ኣቅርቦኣል። ኦኬሎ ያለበትን ሁኔታ፣ የፍርድ ሂደቱን ለመከታተልና በእስር ቤት ለመጎብኘት፣ ቢሆንም  ከኢትዮጵያ መንግስት ምንም  ምላሽ  ኣልተገኘም። የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሁኔታውን በኣደገኛነት እንደሚያዩትም ሳይገልጹ ኣላለፉም።
ባለፈው ሳምንት Okello Akway with wife የኦኬሎ ባለቤት ኦባ ኦድዋ ኦመት kona Obo Adwo Omot fram i Dagbladet  ”… ባለቤቴ ሽብርተኛ ሳይሆን የፖለቲካ እስረኛ ነው” በማለት ገልጻ ነበር። ይህችው የ ኣራት ልጆች እናት የሆነችው ባለቤቱ ባለፈው ሳምንት እንደገለጸችው፣ ”…በኣሁኑ ሰዓት በዚህ ጠባብ ክፍል ከኣራት ልጆቼ ጋር እገኛለሁ። ምንም የማውቀው ነገር የለም። ባለቤቴም የሚያውቀው ነገር የለም። የኖርዌይ መንግስት የተቻለውን ሁሉ ኣድርጎ ባለቤቴን ከእስር እንዲያስወጡልኝ እማጸናለሁ በማለት ነበር የገለጸችው።

 

Filed in: Amharic