>

ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለማደናቀፍ የሞከሩና የስራ ማቆም አድማን ሲመሩ የነበሩ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

 ሙለታ መንገሻ

ፋና ብሮድካስቲንግ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለማደናቀፍ የሞከሩና የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎችን የስራ ማቆም አድማን ሲያስተባብሩ እና ሲመሩ ነበር ተብለው የተጠረጠሩ 9 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ተኮላ አይፎክሩ ለፋና ብሮድካስቲነግ ኮርፖሬት እንዳስታወቁት፥ ግለሰቦቹ የበረራ ሂደቱን ለማስተጓጎል በተለይም ከውጭ ሀገራት የሚመጡ አውሮፕላኖች እንዳያርፉ ጥረት ሲያደርጉ ነበር።

እንዲሁም በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ሰራተኞቹ ዘንድ ሲደረግ የቆየውን የስራ ማቆም አድማ አስተባብረዋል እንዲሁም መርተዋል ተብለው ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል ተኮላ፥ ግለሰቦቹ በፍርድ ቤት መያዣ ወጥቶባቸው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅትም ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል ብለዋል።

በታሪክ አዱኛ

 

 

Filed in: Amharic