>

ሰማያዊ ፓርቲ ፣ አንድነትና ፣ የግንቦት 7 ንቅናቄ ለቀጣዩ ስድስት ወራት ከዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ድጋፍ ያገኛሉ

ጋዜጠኛ ኣበበ ደመቀ  (ኖርዌይ ኦስሎ)

Norway Oslo june 30 2

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮዽያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ኖቨምበር 24/2013 ከተመረጠበትና ተግባራዊ እንቅስቃሴውን ከጀመረበት ዕለት ጀምሮ ያካሄዳቸውን እንቅስቃሴዎች ለመዳሰስና የመጀመሪያውን የግማሽ ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱን ለማቅረብ የጠራው ጠቅላላ ጉባኤ የተከፈተው ፤ በድጋፍ ድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነትና የፕሮግራሙ መሪ በሆኑት በአቶ አቢ አማረ ሲሆን እርሳቸውም በተለያየ የሀገራችን ክፍል በአምባገነኑ መንግሥት ውድ ህይውታቸውን ላጡ ንፁሃን የ1 ደቂቃ የሕሊና ፀሎት እንዲደረግ በመጠየቅ ሲሆን በመቀጠልም የድጋፍ ድርጅቱ ሊ/መንበር አቶ ዮሐንስ ዓለሙ የድርጅታቸውን የማይናወጥ ራዓይ የሆነውን  ፍቅር ፣ ሰላም ፣ መቻቻል ፣ እርቅ ፣ አንድነት ፣ ነፃነት ፣ ፍትሕ ፣ ግልፅነት ፣ በእውነት ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የፍቅርና የአንድነት ተምሳሌት ምድር ትሆን ዘንድ ከምኞት  ያለፈ ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም እነዚህን ሃገራዊና ህዝባዊ እሴቶች መሠረት በማድረግ በየጊዜው የምንደግፋቸው የወሰዷቸውንና የሚወስዷቸውን የፖለቲካ ውሳኔዎችን በማጤን እንደሚሆን አበክረው በመግለጽ ላሳለፉት ግማሽ ዓመት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ፣ የቅርንጫፍ ኮሚቴ አባላት ፣ የወጣቶችና የሴቶች ኮሚቴ አባላትንና እንዲሁም በአቶ ሳለህ አብርሃም የሚመራውን የድጋፍ ድርጅቱን ሬዲዮ አዘጋጆችንና አቅራቢዎችን አድናቆትና ምስጋና በማቅረብ ንጝግራቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን በመቀጠልም የድጋፍ ድርጅቱ ፀሐፊ የሆኑት አቶ ለገሰ ታፈሰ ባለፈው ግማሽ ዓመት የእያንዳንዱን የስራ ክፍል አጠቃላይ ክንውን በዝርዝር ከማቅረባቸውም በተጨማሪ ድርጅቱ ከተነሳበት ዓላማ አኳያ የሚደግፋቸውን የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ያለውንና የነበረውን ግንኙነት አስመልክቶ ለአባላት በስፋት አብራርተዋል ።

የድርጅት ጉዳይ ተጠሪ የሆኑት አቶ ልዑል አለማየሁ የድጋፍ ድርጅቱ የተቀላቀሉት አባላት ቁጥር ከመቸውም የበለጠ ከፍተኛ እንደሆነና በተለይም በተለያዩ አካባቢዎች ቀደም ብለው የነበሩትን በማጠናከርና አዳዲስ ቅርንጫፍ የድጋፍ ድርጅቶችን በመክፈትና ኮሚቴዎችን በማዋቀር በያሉበት አካባቢ ለዲሞክራሲና ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ያደረጉትን እንቅስቃሴ በምስል በማስደገፍ ያቀረቡ ሲሆን የቅርንጫፍ ተወካዮች ስለ ድርጅታቸውና ስለ አካባቢያቸው አጠር አጠር ያለ ገለፃ  በማድረግ የወጣቶችና የሴቶችም ክፍል እንቅስቃሴያቸውንና እቅዳቸውን ለአባላቶቻቸው የገለጹ ሲሆን ወ/ሮ ወርቄ አማረም ወቅታዊና ስሜት ቀስቃሽ ግጥም አቅርባለች ።በማያያዝም በወ/ሮ ፀሐይ ሹምየ የሒሳብ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በወ/ሪት ዙፋን አማረ የኦዲት ሪፖርት ቀረቧል ።

Norway Oslo June 30

በመቀጠልም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ዋነኛ ዓላማ ወደሆነው የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ ጥናት በማድረግ የሰማያዊ ፓርቲን ወጣት ኃየለየሱስ አዳሙ በስፋትና በጥልቀት ያቀረበ ሲሆን የግንቦት ሰባትን መሰረታዊ ዓላማና ራዕይ አቶ ዳባሱ  ድያቀረቡ ሲሆን የአንድነት ፓርቲን በተመለከ ደግሞ ወ/ሪት ሳራ ግርማ በስፋት ካቀረበች በኋላ የድጋፍ ድርጅቱ ሰባሳቢ አቶ ዮሃንስ ዓለሙ ከአባላቶቻቸው ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ አባላቱም ለቀጣዩ ስድስት ወራት ከአሁን በፊት ሲደግፋቸው የነበሩትን የፖለቲካ ድርጅቶች አሁንም ድጋፋችን ይገባቸዋል ብሎ በመወሰን በጭብጨባ አፅድቋል ።

በሌላ በኩል የድጋፍ ድርጅቱ ም/ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳንኤል አበበ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ በሃገራችን የፖለቲካ ጉዳይ ላይ እያደረገ ያለውን ሁለገብ አስተዋፅኦ በአብዛኛው በአንክሮ የሚከታተሉትና በምሳሌነት ተጠቃሽ እየሆነ መምጣቱን አውስተው ተሞክሮውም በተለያዩ ሃገሮች በዓይነቱ የመጀመሪያውና ለየት ብሎ የተዋቀረ ድርጅት ሲሆን ይኸው የድርጅታችን ተሞክሮ በተበታተነ መልኩ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች የሃሳብና የአመለካከት ለዩነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ መሰረታዊና ሃገራዊ አንድነታቸውን  ላይ በማተኮር ወደ አንድ ጥላ ስር እንዲመጡ ለማድረግ የሚያስችሉ ተሞክሮዎች ላይ በማተኮም የሚንቀሳቀስ በመሆኑ በምሳሌነት ተጠቃሽ እየሆነ መምጣቱንና ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት የሚለውን ሲያሜም በሲዊዲን ፣ በጀርመን ፣ በሲዊዘርላንድ እና በሌሎችም እየሰፋ መሄዱ የዚሁ አመላካች እንደሆነ በመጥቀስ ይህንን አርአያነት ያለው የተለያዩ አመለካከቶችን አቻችሎ በአንድነት ለአንድነት የመቆምና በጋራ የመስራት ባህሪን ይኖረን ዘንድ ፈር ቀዳጅ የሆነውን ስራ መሰረት ለጣሉልን ቀደምት አመራሮች በማመስገን ስብሰባው  የተዘጋ ሲሆን  በአጠቃላይ የድጋፍ ድርጅቱ የስራ አስፈፃሚ አካላት ከተመረጡበትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ አኳያ ሲታይ በኮሚቴ ደረጃ ተናቦ መስራትንና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ማተኮሩ ለውጤታማ እንቅስቃሴው በጎ ጅምር እያደረገ በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ ሆኖ ተመልክቸዋለሁ ።

 

Filed in: Amharic