>

ትህነግ/ህወሓት መልካም አጋጣሚ አገኘ! (ጌታቸው ሽፈራው)

ትህነግ/ህወሓት መልካም አጋጣሚ አገኘ!
ጌታቸው ሽፈራው
~ትናንት አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ቀለም ሲለቀለቅባቸው ሲውል ከዳውድ ደጋፊዎች በላይ የትህነግ/ህወሓት ደጋፊዎች ስለ ኦነግና ስለ አርማው ሲያወሩ ዋሉ። “በለው፣ ግፋ” እያሉ አበረታቱ!
~የኦነግ አቀባበል አባላት  “እኛ ቀለም እንዲቀባ አልፈለግንም” ብለዋል። ወጣቶች ግን አዲስ አበባን በሙሉ ለመቅባት ተዘጋጅተው የመጡ ይመስል፣ ከዳር ጀምረው፣ የቆሻሻ ማጠራቀሚያና ሌላም ቅራቅንቦ ሳይቀር እየቀቡ ነው የገቡት።  ይህም ወጣቶቹ ገንዘብ አሰባስበው ብቻ የሚያደርጉት አይደለም ለማለት መነሻ ነው።  በሁለቱም ወገን “የሕዝብ ሰላም የማይፈልጉ” እየተባሉ የተገለፁ አሉ። “ሕዝብ፣ ድርጅት፣ አይወክሉም” የተባሉ አሉ
~የአዲኃን እና የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት አባላት የገቡት በሁመራ ነው። የኦነግን ጨምሮ የታጣቂዎቹ ፅ/ቤት ሁመራ ማዶ ይገኛል ነበር። በዚህም ነው በሁመራ በኩል የመጡት።  የኦነግ ሰራዊት ግን  ዛላምበሳ በኩል ሊገባ ነው። በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱትን እነ በቀለ ገርባን ለምን ይፈታሉ እያለ ሲከራከር የነበረው ትህነግ፣ በሽብር የፈረጁ ድርጅቶች ስማቸው ከፀረ ሽብር አዋጁ መነሳት የለበትም ሲል የነበረው ትህነግ/ህወሓት  የትግራዩን ተቃዋሚ ትህዴን አልቀበልም እያለ የዳውድ ኢብሳን ሰራዊት በዛላንበሳ በኩል ተቀብሎ፣ ምሳና ራት ጋብዞ የሚልክበት ምክንያት ምን ይሆን? የዳውድ ኢብሳው ኦነግ እና የደብረፅዮን ትህነግ/ህወሓት ቃል ኪዳናቸውን መልሰው አሰሩት ማለት ነው።
~ትናንት አዲስ አበባ ላይ ያ ግርግር ሲፈጠር፣ሀውልት ይፍረስ ሲባል፣  መተከል ላይ የትህነግ/ህወሓት ባለሀብቶች ቁጥጥር ስር በወደቀው መተከል አማራዎች ሲታረዱ ውለዋል። ያኔ አርባ ጉጉና በደኖ ላይ አብረው ተባብረው እንደጨፈጨፉት አሁንም አዲስ አበባን ብቻ ሳይሆን ሀገር ለማናጋት ከሆነ ትህነግ/ህወሓት ወደኋላ እንደማይል ግልፅ ነው!  ጊዜው ለትህነግ/ህወሓት ምቹ ነው! የቀን ጅብ የተባለበት ጊዜ ሳይርቅ አውሬ ሆኖ ለመምጣት እድል እያገኘ ነው! ተባባሪ ፅንፈኛም አያጣም!
~ መሞት አልበቃ ያለበት ዘመን እየመጣብን ይመስለኛል። የአማራ ህዝብ እንደፍዬል መታረዱን ቀጥሎበታል። በቤኒሽልንጉል ጉምዝ ክልል ጉባ ወረዳ አልመሃል ከተማ በአማራዎች ላይ ዘግናኝ ግድያ ተፈጽሟል።
~ አልመሃል ከተማ ላይ ሆቴል ያለው ገብረ ፃድቃን የተባለ ትግሬ ሁለት ሽጉጥ አንድ ታጣፊ ክላሽ በመታጠቅ በአማራ ተወላጆች  ላይ ጥይት በመተኮስ ሶስት ወጣቶችን አቁስሏል፡፡  የፀጥታ ሃይል በቦታው በመድረስ ከነመሳሪያው  በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
 ~ በሪሁን የሚባል የአቢሲኒያ ሆቴል ባለቤት ቁጥሩ ያልታወቀ መሳሪያ እንደተገኘበት የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ ፊድራል ፓሊስ አና መከላከያ ፀጥታውን ለማረጋጋት ቢሞኩሩም ማቆም አልተቻለም ።
 አልመሀል 90 በመቶ የሚሆኑት የትግሬ ባለሀብቶች የሚኖሩባት ቀበሌ ስትሆን ቀን ሰራተኞቻቸው ደግሞ ሳሉግ የሚባሉ የአማራ ወጣቶች ናቸው።
ከሁለት ወር በፊት  2 መቶ የሚሆኑ የጉምዝ ወጣቶችን ለቀን ሰራተኝነት በሚል የትግሬ ኢንቨስተሮች ወታደራዊ ስልጠና ሲሰጧቸው ነበር።
 ይሄው ዛሬ ስልጠናው ፍሬ አፍርቶ 10 የአማራ ወጣቶችን በጭካኔ አርደው በየጫካው ወድቀው የአውሬ እራት እንዲሆኑ ተፈርዶባቸዋል።
የታረደው አማራ ቁጥሩ እንደሚጨምር ቢንጎ ከምትባል ጎጥ ሸሽቶ አልመሀል ከተማ የመጣው አንድ ወጣት  የአይን እማኝ ገልጿል።
Filed in: Amharic