>
5:13 pm - Thursday April 19, 7534

ለሀውልት ድንጋይ መወርወር ምንኛ ቂልነት ነው?? (ሔቨን ዮሐንስ)

ለሀውልት ድንጋይ መወርወር ምንኛ ቂልነት ነው??
ሔቨን ዮሐንስ
አባቶቻቸው ያልሆኑትን ልጆቹ የእንሁን አባዜን ተጠናውታቸው አልበላ አልጠጣ አላቸው። አባቶቻቸው ጀግኖች ነበሩ ጣሊያንን ሽምቅ የተዋጉ ። ልጆቹ ግን አባቶቻቸውን መሆን ተስኖአቸው ጣሊያንን መሆን ወደዱ ። አባቶቻቸው ባርነትን ተፀይፈው ተዋግተው ያባረሩትን ጣሊያን ተመልሶ ነፍስ አንሰራርቶ መጣና ለንጉሱ የቆመውን ሀውልት በንደት አፈርሳለሁ አለ ።አያይ አታፈርስም አሉና የኢትዮጵያ ህዝቦች ሞገቱ በድቅድቅ ጨለማ ማንም ሳያይ አፍርሰውት አደሩ ። በአድስ አበባ ሀዘን እልህ ቁጭት ቤቷን ሰራች ። የፈረሰው ሀውል ጊዜውን ጠብቆ ተሰራ ።
ባርነትን የተፀየፋ አባቶቻቸው ተዋግተው ነፃነትን አውርሰዋቸው ዛሬ የጣሊያን ጠላት ሚኒሊክን የእኔ ጠላት ነው ብሎ መነሳት ጣሊያን ደቅሎኛል ከማለት አይተናነስም ።
ከባርነት ቀንበር ያወጣውን ደክሞ ያስከበረውን በአለም ላይ እንኳን ኢትዮጵያ አፍሪካን ያስከበረው የጥቁር ህዝቦች ኩራት ምንም ሳይሰሩ በማንኪያ ቀርቶ በጉጠት የምትወጣ ስራ ሳያስቀምጡ ሚኒሊክ ጋር መንጠራራቱ ለእኛው ብቻ ሳይሆን በአለም ህዝቦች ፊት አለማወቃችንን በፊርማ ሳይሆን በስራ እያስመሰከርን ነው ። ጣሊያን ነይልን አባቶቻችን ሳያውቁ አስቀየሙሽ እንደማለት ባርነትን እንደመናፈቅ ነው።
የሆነው ሆኖ ዛሬ 6፡00 እስከ 8፡00 ድረስ በአዲስ አበባ  ፒያሳ አካባቢ ብዙ ደስ ማይሉ ነገሮች ተፈጥረዋል ።
ገጀራ ቆንጨራና ዱላ ከኦነግ ባንዲራ ጋር የያዙ ወጣቶች ወደ አፄ ሚኒሊክ ሃውልት ድንጋይ መወርወር ሲጀምሩ ከፀጥታ ሀይሎች አስለቃሽ ጭስ ተተኩሱዋል። ትንሽ የመሳርያ የተኩስ ድምጦች እንደነበሩ ከአካባቢው የመረጃ ምንጭ አድርሶኛል ። አንቡላንሶችና የህክምና ባለሙያዎችም በፍጥነት ወደ ቦታ መጥተዋል ።አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ አላማ የያዙ ወጣቶች የተለያዩ መፎክሮችን እያሰሙ ከዶሮ ማነቂያ ከሰባራ ባበቡር በአቡነ ጴጥሮስ በኩል እንዲሁም ከፒያሳ በአራዳ ህንጻ በኩል ወደ ንጉሱ ሃውልት ጉዞ ሲያደርጉ በፀጥታ ሃይሎች ተመልሰዋል።
 የአዲስ አበባ የፌደራልና ፖሊስና የመከላከያ አባላት ሰልፉን ለመበተን ጥረት ሲያደርጉ ተስተውለዋል። 8፡00 አካባቢ የጣለው ከባድ ዝናብ ለወጣቶች መበተን የራሱን ሚና ተጫውቷል ። ተፈጥሮ ክፍዎችን ሞገተች ። ድንጋይ መወርወር ለሀውልት ምንኛ ሞኝነት ነው ። ለጋራ ሀገር የጋራ ስራ እንስራ እንጂ የጋራ ጥፋት አንስራ ። በእኛ ዘመን አስነዋሪ ስራ ያየሁት ታሪክ የሰሩ ሰዎች ታሪክ ያልሰሩ ሰዎች ሲያብጠለጥሉ ነው ። እጅጉን ያስገረሙኝ ደግሞ ከማንበብና ከማወቅ ይልቅ ምንም ሳያውቅ ለሚለፍፍ ለፍላፊ ጆሮ ሰጥቶ አሜን ብሎ የተቀበለ ዱኩማንን ማየት ነው ። አንብቡ ጠይቁ ተመራመሩ ትልልቆችን ጠይቁ ። ከእናንተው ወገን መተኪያ የሌለው ፀጋየ ገብረ መድህንን ስራዎች ብቻ ብትፈትሹ ኢትዮጵያ ፍንትው ብላ ትገለፅላችሁ ነበር ። ሌላ እነ አብዲሳን ታሪክ ብታዩ፣ እንደ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳን ፣ ጄነራል ጃግማ ኬሎን አይነት ልሂቃኖቻሁን ብትጠቀሙባቸው የት በደረሳችሁ ። እግዚአብሔር አስተዋይ ልቦናን ያድለን ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
Filed in: Amharic