>

አዲስ አበባ ኩርፊያ ላይ ናት!!! (የሺሀሳብ አበራ) 

አዲስ አበባ ኩርፊያ ላይ ናት!!!
የሺሀሳብ አበራ 
* “ኢትዮጵያ” የሚለው ስም የሚያስደነግጣቸው ሁሉ የኢትዮጵያ  የቀደመ ቀለም እንዲደበዝዝ ሩጫ ላይ ናቸው፡፡
 
* የሰው እጅ ቆርጦ በተቆረጠው እጅ ተጨፍሮበታል፡፡
*  መነኩሲቴች ተደፍረዋል፡፡
 በዝቅተኝነት ስሜት ተቦክቶ የተጋገረው የነ ጃዋር ፖለቲካ  ከደጉ ከኦሮም ህዝብ አብራክ የወጣን ወጣት አይደለም ኦሮሞነቱን ሰውነቱን እያሳጣው ነው፡፡ ጡት ለመቁረጥም ሙከራ ተደርጓል፡፡
 ..
የነ ጃዋር  እና ኦነግ ስብከት እጅግ አደገኛ እና በዝቅተኝነት መንፈስ የተሞላ በመሆኑ ሰውን ከመስቀል እጅ እስከ መቁረጥ  አድርሷል፡፡ እንደ አኖሌ አይነት ሃውልት ስልጤ ወይም ጉራጌ ማስቀመጡ አይቀርም፡፡በነጃዋር ስብከት ምክንያት እጅ እና ጡት እየተቆረጠ ነው፡፡ ኦሮሚያ ክልልም የኦሮሞን ህዝብ አቃፊነት በሚቃረን መንገድ ስልጤን፣ጉራጌን፣ተጋሩውን እያፈናቀለ ነው፡፡በማፈናቀል ኦሮሚያ ክልል ቀዳሚው እየሆነ ነው፡፡  ኦሮመኛን ሁለተኛ ቋንቋ ለማድረግ ሲንቀሳቀስ የነበረው የኢትዮጵያ  ህዝብ በነጃዋር ክፍኛ ተሸማቆ አዲስ አበቤ ሰላማዊ ሰልፍ እያደረገ ነው፡፡ ሌላውም መቀጠሉ አይቀርም፡፡
አዲስ አበቤዎች ለወገናቸው እየጮኹ ነው!!
…….።።
የአዲስ አበባን ኩርፊያ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ይጋሩታል፡፡ ከዓርብ እስከ ዛሬ እሁድ አዲስ አበባ ሙሉ አገልግሎት  እየሰጠች አይደለም፡፡አዲስ አበባ አገልግሎት  ካልሰጠች ኢትዮጵያም ትቆማለች፡፡በአዲስ አበባ እና በዙሪያው ያለው ጉዳይ  ካልቆመ ሃገሪቱ ለመፍረስ ትገደዳለች፡፡ የነጃዋር ቅስቀሳ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ አዲስ አበባን እና ድሬድዋን በቄሮ ፈቃድ ብቻ የሞትኖር ከተማ በማስመሰል፣ከፈለግን በሁለት ቀን የኦሮሚያ  እናደርጋታለን የሚል ለከት የለሽ ቅስቀሳ እየተስተጋባ ነው፡፡ የነጃዋርን ቅስቀሳ ኳታር ወይም አልጀዚራ  ይቀበላል፡፡ያስተጋባል፡፡(ይህ ብዙ ጉዳይ ነው፡፡ትርጉሙን ላቆየው::)
 …
በ2008 ዓም  ጀርመን ላይ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ” ኩሽቲክ” ተብሎ እንዲቀየር የነጃዋር ክንፍ ወትውቶ ነበር፡፡ በኦነጎች  ኩሽቲክ የሚለው ስም ፀንቷል፡፡ጀርመንም ለሃይማኖቷ ስትል ሙሉ ድጋፏን ሰጥታለች፡፡
 …
የሴሜቴክ ወይም የአብሲኒያ መንግስት ኢትዮጵያ በሚል ኦሮሚያን ወሯል  የሚሉት እነጃዋር የኩሽቲክ መንግስት ማቋቋም የሚል አጀንዳም እያነሱ ነው፡፡ የሲዳማ እንቅስቃሴ በነ ጃዋር ድጋፍ አለው፡፡ሲዳመኛ ኩሽቲክ ቋንቋ ነው፡፡ኦሮመኛ፣ሶማሌኛም እንዲሁ፡፡ ሲዳማ ክልል እንዲሆን ኦኤምኤን እየተጋ ነው፡፡ ሶማሊያም የኩሻዊ ትስስሩ አካል አድርጎ ለማቅረብ ተጥሯል፡፡
አማራ ክልል ገብተው  አማራ እና አገው እያሉ አገው የኩሽቲክ መደብ ብለው ከአግዴፓ ጋር ለመገናኘትም ጥረት አድርገዋል፡፡ አዲስ አበባ የኩሽቲክ ኦሮሞ ናት የሚለውን ኩሻዊ የቋንቋ ቤተሰብ ያላቸው ሁሉ እንዲደግፉ ለመስራት ሞክረዋል፡፡
 …
በእርግጥ ኢትዮጲያዊነት በብሄር ማንነት  ተደፍቋል፡፡ኢትዮጲያዊነት በመንፈስ ካልሆነ በተግባር የለም፡፡የኢትዮጲያዊነት መገለጫ አንድም ነገር የለም፡፡ኢትዮጵያ ዋና ከተማ እንኳን የላትም፡፡የሚያስማማ ሰንደቅዓላማ የላትም፡፡የተቃርኖ ሃገር ናት፡፡”Ethiopia  is if country” ያላት የዶክተር ስዮም መስፍን ንግግር ገዥ ናት፡፡  ኢትዮጵያ በቅድመ ሁኔታ ያለች ሃገር ናት፡፡ብሄር ከዜግነት ይበልጣል፡፡
……
 ስለበጠለም አዲስ አበባን፣ድሬድዋን የብሄር ማንነት ለመስጠት ሩጫው ተጀምሯል፡፡ ሩጫው ፈፅሞ በሰላም አይጠናቀቅም፡፡
 አዲስ አበባ የኢትዮጵያ  ናት፡፡አዲስ አበባ ያሉ ኢትዮጵያዊን ተደራጅተው መብታቸውን ሊያስከብሩ ይገባል፡፡  ከውጭ ሆኖ በዕድላቸው የሚወስን ማንም ጣልቃ ገብ ሊኖር አይገባም፡፡የአዲስ አበባ አራዳ የፖለቲካ አራዳነት ይልመድ፡፡መፍትሄው ይሄ ብቻ ነው፡፡አዲስአበቤ ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ኢትዮጵያዊነቱ ይከበርለት፡፡
 ..
ይህ ሳይሆን ኢትዮጲያዊነቷ  ቀርቶ አዲስ አበባን የሆነ ብሄር ብቻ ለማድረግ ሩጫ ከተጀመረ ሰንብቷል።
Filed in: Amharic