ዘመድኩን በቀለ
~ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከኤርትራ ጋር ኃይለኛ ፍቅር ይዟቸው ሃኒ ሙን ላይ ናቸው።
~ ” የዓመቱ በጎሰው” ተሸላሚ ኦቦ ለማ መገርሳ የት እንዳሉም አልታወቀም።
~ ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል በዜጎች ላይ ያላግጣሉ። አዲስ አበባ ከአስኮና ከቡራዩ በተፈናቀሉ ዜጎች ተጨናንቃለች።
ጉራጌን አሳደህ በለው፤ የሚንሊክ ሰፋሪ ዐማራውን ከኦሮሚያ ምድር አጽዳው፣ በለው ውገረው እያሉ የኦሮሞን ወጣት በወገኑ ላይ አውሬ እንዲሆን ያደረጉትን አካላት መንግስት ተብዬውም ህዝቡም ጠንቅቆ ያውቃል። ለፍርድ ይቅረቡልንም እየተባለ ነው ሰሚ ከተገኘ ።
★ የፖሊስ ኮሚሽነሩ አቶ ዘይኑ እንቅልፋቸውን ሲተኙ አድረው ጠዋት አርፍደው ወደ ሥራ መግባታቸው ሳያንስ በሚሰጡት ንቀት የተመላበት መግለጫ ህዝቡ ብስጭቱ ከጣሪያ በላይ ደርሷልና ግለሰቡ በአስቸኳይ ስልጣናቸውን ይልቀቁም እየተባለ ነው።
~ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማም ችግር ከደረሰ በኋላ እየዞሩ እጅበደረት እያጣመሩ ያዘኑ መምሰሉን ይተውትና አዲስአበባ በአስቸኳይ በአዲስአበባ ልጆች ትተዳደር፣ ትመራም። አስቸኳይ የከተማዋ የሽግግር አስተዳደር ይመስረት የሚሉ ድምጾችም በርክተዋል።
ህዝቡ ፖሊስም ሆኖ እየሠራ ነው፣ የእርዳታ ሰጪ ድርጅቱም ህዝቡ ነው። መንግሥት ተብየው ድራሽ አባቱ ጠፍቶ ጮጋ ብሏል።
በመጨረሽታም | ~ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ከሽርሽር መልስ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ወይም በቤተመንግሥታቸው ይከሰቱና እንደተለመደው ” መግደል መሸነፍ ነው ” ይሉልሃል። አከተመ ይኸው ነው።