>
5:13 pm - Friday April 20, 3787

ዶ/ር ዐቢይ በ11ኛው የግንባሩ ጉባኤ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች!!!

ዶ/ር ዐቢይ በ11ኛው የግንባሩ ጉባኤ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች!!!
 ኢ.ቢ.ሲ
• 11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ በለውጥ ምሁዋር ውስጥ በገቡበት ወቅት መካሄዱ ታሪካዊ ያደርገዋል፡፡
• ኢህአዴግ ከዚህ ቀደም የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች እያሸነፈ እንደመጣው ሁሉ የሚገጥሙትን ችግሮች እየፈታ የለውጡ ሞተር ሁኖ አገር መምራቱን ይቀጥላል፡፡
• ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ነገዋን በመፈለግ ላይ ያለች፣ በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገች አገር ናት፡፡
• የሽግግር ሂደቱን የአገራችን አርሶአደር “የበሬውን ብልሃት እና የወይፈኑን ጉልበት አቀናጅቶ” …እንደሚለው ሁሉ በእኛም ዘንድ ተተኪዎችን በጎ ልምድ ካላቸው በማስተሳሰር አገራዊ ለውጡን ለማሳካት ኢህአዴግ ይታትራል፡፡
• አገር የምታድገው በቅብብሎሽ ነው፡፡
• ያለትላንት ዛሬ ምንም አልተገኘምና የትናቱን ትውልድ ማመስገን ያስፈልጋል፡፡እኛም በተራችን በተተኪ ትውልድ መተካታችን አይዘነጋምና፡፡
• መተካካት የታቀደ ሂደት እንጂ ድንገተኛ ሆሆ እልቂት እንዳያመጣ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
• ይህ ትውልድ ስልጣንን በእጁ አስገብቶ ቀድሞ የነበረውን ነገር በማስፍረስ የተጠመደ መሆን አይገባውም፡፡
• ትላንት እና ዛሬን ያጣጣመች ኢትዮጵያን ለመገንባት ተግቶ መስራት ያስፈልጋል፡፡
• ኢትዮጵያ በላቀ ተግበራቸው ያገነኗት መሪዎች እንደነበሯት ሁሉ ፣ለውድቀት የዳረጓትም ነበሩ፡፡ለጠላቶቿ የሰጧት መሪዎችም ነበሩ፡፡
• ያለመተማማን በማስፋት ፣ በጠብና በጦርነት ሊተላለቁ የነበሩ ልጆቿን አስታርቀው ወደ ልዩ ምዕራፍ ያስገቧት ነበሩ፡፡
• ጥያቄው በአሁኑ ጊዜ ያለው አመራርስ የትኛውን ታሪክ ይደግማል የሚለው ጥያቄ ለእኛ ቀርቧል፡፡
• የአገራችን እጣ ፈንታ አሁን እድሉን ባገኙት ፖለቲከኞች ፣ እንዲሁም በህዝቧ እጅ ነው፡፡
• ዘመናዊና ስልጡን አገር ለመፍጠር ህዝብን የስልጣን ልዕልና መገለጫ አድርጎ የሚቀበል ስርዓት መፍጥር ሲሳካልን ነው፡፡
• ህዝብ የሚያምናቸውና የሚከተላቸው ልዩ ልዩ የማህበረሰብ መሪዎችን ካገኘን በእምነት ፣ በባህል፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በፖለቲካ፣ በጦር አመራር ፣ በምህንድስና ፣ በስፖርትና ኪነጥበብብ፣በሌሎች ዘርፎችም ጭምር ከተዋጣልን አገር የተሳካ ጉዞ አድርጋ በከፍታ ጉዞ ላይ ትደርሳለች፡፡
• የምንፈልጋትን አገር መምሰልና መሆን የሚገባን እኛው ራሳችን ነው፡፡
• የበለፀገች የጋራ ቤታችንን ለጋራ ልጆቻችን ማድረስ የምንፈልግ ከሆነ ዝርፊያውን ፣መጠላለፉን ትተን በጋራ መስራት አለብን፡፡
• ዘርና ሀይማኖትን መሰረት አድርገን ሌሎችን ከመቆስቆስ ይልቅ ለጋራ ጥቅምና ድል እንስራ፡፡
• ከመካከላችን ማንም እስከተጎዳ ድረስ ሁላችንም እንጎዳለን፤ስለዚህ ለሁናችንም የምትሆን አገር በመደመር መገንባት ግድ ይለናል፡፡
• ኢትዮጵያ በሁላችንም ላብና ደም የተሰራች አገር በመሆኗ ባለቤቶቿ ሁላችንም ነን ፡፡አዲሲቷንም ኢትዮጵያ በጋራ ልንገነባ ይገባል፡፡
• ኢህአዴግ ከዳር እሰከዳር የሚሳተፉበት ድርጅት እንዲሆን መስራት ያስፈለጋል፡፡
• ኢህአዴግ አጋር ፓርቲዎችን ወደ ግንባሩ ለማስገባት አቅዶ ቢንቀሳቀስም በአገራዊ ሁኔታው በጥናት እንዲመለስ የቀረበውን ጥናት ማድረስ ባመቻሉ፣ ይህን ምላሽ እንዲያገኝ የሚያስችል ውሳኔ ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
• የተጀመረውን የፖለቲካ ምህዳር የማስፋቱ ሂደት የይስሙላ ባለመሆኑ በሁሉም መስክ ተጠናክሮ ይግፋበታል፡፡
• የተፎካካሪዎቻችን ሀሳብ ላይሳማማን ይችላል፣ነገር ግን የነሱን ሀሳብ በመገደብ ሳይሆን የነሱን ሀሳብ የሚያሸነፍ ሀሳብ ይዘን በመቅረብ ብቻ እንዲሆን እንሰራለን፡፡
• ዛሬ ላይ ሁነን የትላንትናውን ሁነታችንን መቀየር አንችልም፣ ይሁን እንጂ የነገዋን ኢትዮጵያ ተስማምተን መገንባት እንችላለን፡፡
• አዲስ ታሪክ ለመፃፍና ለመስራት በሚያስችል የዘመን አካፋይ አንጓ ላይ እንገኛለን፡፡
• ክልላዊ አስተዳደርን ከብሄር ማንነት ጋር ሳናምታታ ፌደራሊዝሙን ከተገበርነው ለአኛ አውድ ተመራጭነቱ አያጠያይቅም፡፡
• ሰዎች በየትኛው የአገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሰው የመስራት መብታቸው ተረጋግጦ ኢትዮጵያ ህብረ ብሄራዊ የምትሆንበት ገፅታም ሊረጋገጥ ይገባል፡፡
• እስካሁን የብሄር ማንነት እና ኢትዮጵያዊ ማንነት ሚዛን ጠብቀው የመጡ ባለመሆናቸው የህዝብ ለህዝብ መድረኮች፣ የባህል መድረኮችና ሌሎች መድረኮችን በማዘጋጀት ከፍ ከፍ የሚያርገንን ስራ መስራት ያስፈልገናል፡፡
• መደመር ሁሉም የየራሱን ጥንካሬ ይዞ ከሆነ እምቅና አዲስ ታሪክ መፃፍ ያስችለናል፡፡
• አገራችን የገጠማት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያው ቀውስ መስኤው ከግብርገብነት ቀውስ የሚመነጭ ነው፡፡
• በሞራልና ግብረገብ የወደቀ ማህበረሰብ ውስጥ ሆነን ሰላም፣ ፍትህ፣ ብልፅግናን ማረጋገጥ ከባድ ነው፡፡
• በሞራል ልዕልና፣ በስነ ምግባር ምሳሌ በመሆን የሀይማኖት ፣ የጎሳና ማህበረሰብ መሪዎች መሪ በመሆን አርዓያነትን በማሳየት ከችግራችን እንዲንወጣ ያስፈልጋል፡፡
• ዜጎች የሚገጥማቻውን መሰረታዊ አገልግሎት የመልካም አስተዳደር ችግር ብሎ መግለፅ አይመጥነውም፡፡
• ስራ አጥነት መቀነስ፣ የዜች የኑሮ ደረጃን ማሳደግ ፣ የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ላይ ትኩረት የሰጠ ጉባኤ ሆኖ እንደሚቀጥል እምነቴ ነው፡፡
Filed in: Amharic