>
5:13 pm - Thursday April 19, 4581

ዶ/ር አብይ ስልጣንን በጎሳ እየመዘነ የሚያድል የወያኔ ወራሴ መንግሥት መሆኑን አረጋግጧል!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ዶ/ር አብይ ስልጣንን በጎሳ እየመዘነ የሚያድል የወያኔ ወራሴ መንግሥት መሆኑን አረጋግጧል!!!
አቻምየለህ ታምሩ
 
* አንዳቸውም ከተሾሙበት ሚንስትር መስሪያ ቤት ስራ ጋር የሚገናኝ የትምህርት ዝግጅት፣ እውቀትና  የሞያ ልምድ የላቸውም። ስለዚህ ዐቢይ በየቦታው ባደረጋቸው ንግግሮች ሁሉ  ስለብቃትና እውቀት ሲሰብክ የነበረው የማያምንበትን፣ የማይተገብረውንና ከወያኔ የማይለይበትን ሽንገላ  ነበር ማለት ነው!
 
ዐቢይ አሕመድ ካቢኔውን በፈለገው መልኩ የማዋቀርና ያሻሙን ሰው የመሾም ሙሉ መብት አለው።  መጠየቅና መወቀስ ያለበት የዛሬውንም ሆነ እስካሁን ድረስ  ሲሾማቸው የነበሩ ሰዎችን ለሹመት በሚያጭበት ወቅት እየተከተለው ባለው  መርህ ነው። ዐቢይ በጠቅላይ ሚንስትርነት ከተሾመ ጊዜ ጀመሮ በየቦታው ሲሰብክ የነበረው  የመንግሥት ስልጣን በሞያና በእውቀት ብቻ  የሚገኝ  አገልጋይነት እንደሆነና  እርሱም ለዚህ እንደሚሰራ አድርጎ ነበር። ትናንትናም ሆነ ዛሬ  በሰጠው  የካቢኔ ሹመት  ያደረገው ግን  በየአደባባዩ ባደረጋቸው ንግግሮች ሕዝብ እንዲቀበለው   የቀሰቀሰበትን  መርህ ተከትሎ  አይደለም።
ኢሕአዴግ የሚባለው ድርጅት አባልና እህት ፓርቲዎች የጎሳ ስብስቦች ናቸው። ጎሳ የግዕዝ ቃል ነው። ትርጉሙ ቋንቋ ማለት  ነው። ዐቢይ ሚንስትር አድርጎ የመረጣቸው ሰዎች ሁሉ የነዚህ የጎሳ ድርጅቶች ማኅበተኛ  ናቸው። በሌላ አነጋገር ዐቢይ ሚንስትሮቹን  የመረጠበት ብቸኛ መስፈርት ጎሳና የጎሳ  ድርጅት ማኅበርተኛነትን ብቻ ነው። መቀሌ ዩኒቨርሲቲ የኛ ተማሪ የነበረውን  ሳሙኤል ኡርካቶን ጨምሮ  ዛሬ የተሾሙት ሚንስትሮች ሁሉ አንዳቸውም ከተሾሙበት ሚንስትር መስሪያ ቤት ስራ ጋር የሚገናኝ የትምህርት ዝግጅት፣ እውቀትና  የሞያ ልምድ የላቸውም። ስለዚህ ዐቢይ በየቦታው ባደረጋቸው ንግግሮች ሁሉ  ስለብቃትና እውቀት ሲሰብክ የነበረው የማያምንበትን፣ የማይተገብረውንና ከወያኔ የማይለይበትን ሽንገላ  ነበር ማለት ነው። በዚህም  ለሕዝብ የገባውን ቃል በልቶ፣ ስልጣንን  በጎሳ እየመዘነ የሚያድል የወያኔ ወራሴ መንግሥት ሆኗል፤ ሕዝብን አታሏል፤ ከዚህ በፊት እንዳልሁት አጭበርባሪና  አስመሳይ [con artist] መሆኑ እስካሁን ላልታያቸው በእውነተኛ  ባሕሪው ተገልጧል!  ይሄው ነው!
Filed in: Amharic