>
5:13 pm - Tuesday April 19, 9774

"እኛ የጃራ አባገዳ ልጆች ነን!" (ጀዋር በሚሊኒየም አዳራሽ የተናገረው፡) - በያሬድ ይልማ

“እኛ የጃራ አባገዳ ልጆች ነን!”
(ጀዋር በሚሊኒየም አዳራሽ የተናገረው፡ )
ያሬድ ይልማ
* …የአዲስ አበባ ከንቲባ እንዲሆን ህግ ከመሬት ተፈንቅሎ ተዘጋጅቶለት ፣ ወደ ስልጣል የመጣው ታከለ ኡማ ፣ በአዲስ አበባ የሚገኙትን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሬቶች በግማሹ እንዲወርሱም ጥሪውን አስተላልፏል!
በሐረርጌ ውስጥ በብዙ ስፍራዎች ፣ የኦነግ አስተሳሰብ ጠንሳሽ እና የክርስቲያን ዘር ኢትዮጵያ ውስጥ ለደቂቃ አይቶ መታገስ የማይችለው ነብሰ በላው ጃራ ፣ ስንት ክርስቲያን ኦሮሞዎችን ፣ ቄሶችን ፣ እንዲሁም የምኒሊክ ሰፋሪ የተባሉ ምስኪን ኢትዮጵያዊያንን ከዚሁ ከሐረርጌ ከተውጣጡ ፣ ሙስሊም የኦሮሞ ተወላጆችን ይዞ አሰቃቂ እልቂት እንደፈፀመ በሐረርጌ የኖረ ሰው በሙሉ የማይረሳው ነው፡፡ ብዙው ሰው የበደኖንና ፣ የአርባጉጉውን እልቂት ብቻ ነው የሚያስታውሰው፡፡
ታዲያ በውጪ ሐገር ሳለ አቶ ጀዋር መሐመድም ፣ የጥላቻ አባቱን ፣ የጃራን ፈለግ ተከትሎ ፣ ለክርስቲያኖች ያለውን ጥላቻ ፣ በአጠቃላይም ኢትዮጵያ የምትባለውን ሐገር ፣ በዚሁ የክርስትና እና የእስልምና እምነት አብሮ ፣ ተደባልቆ ፣ እንደ አንድ ሆኖ መኖርን ፣ “ሽርክ-ሀጥያት” አድርጎ እንደሚያየው ፣ አርኣያው ፣ ነብሰበላው ጃራ ፣ በተደጋጋሚ እንዴት እንደሚጠላ ፣ እንዴት በሜንጫ ፣ ክርስቲያኖችን አንገታቸው ላይ እንደሚል ፣ በገሃድ ሲናገር የኖረ በመሆኑ ፣ ዛሬ ድምፁን በዚህ ጉዳይ ላይ ሲቀንስ ሰዎች ፣ ቢረሱት አይፈረድባቸውም፡፡
እውነቱን ለመናገር ጀዋር ግን ለደቂቃ ያልተቀየረ ፣ የኢትዮጵያ የክርስቲያኑ ክፍል ፣ ለኦሮሞ የነፃነት ትግል ዋነኛ ችግር ነው ብሎ የሚያምን ፣ (ይህ ክርስቲያን ኦሮሞውንም ይጨምራል) ስለዚህም ከሁሉ አስቀድሞ በሚወደው እና በሚከተለው የነብሰበላው ጃራ አርኣያነት መሰረት ፣ ኦርቶዶክስ ከርስትናን ፣ መጀመሪያ ከኦሮምያ ፣ ከዚያም ከአጎራባች ስፍራዎች ማጥፋት ፣ የነብሱ ውጥን ናት፡፡ ለዚህም ነው ፣ ከአሜሪካ አቀባበል ተደርጎለት በሚሊኒየም አዳራሽ ፣ የማይረሳውን ነብሰበላ አባቱን በመፈክር “ እኛ የጃራ አባገዳ ልጆች ነን!” ብሎ ዛሬ ድረስ እሱንም የሚገፋውን ፣ ደም አፍሳሽ አረመኔ ሰው ስም የጠራው፡፡
ጀዋር መሐመድ ኢትዮጵያን መጥላት ብቻ ሳይሆን ክርስቲያን የሆነውን ክፍሏን ለማጥፋት ወስኖ ኢትዮጵያ የገባ መሆኑን ፣ ብዙ ሰዎች ከመጀመሪያው ጀምረን ስንናገር አልተቀበሉንም ነበር፡፡ ይህ ግልብ አይምሮ እና አስነዋሪነት ባንድ አጣምሮ ፣ ጃራን የሚያፈቅር ግለሰብ ፣ ዛሬ ደግሞ ሌላ እቅዱን በገሃድ አዲስ አበባ መሐል ቁጭ ብሎ ተናገረ፤ “ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አዲስአበባ የያዘችው መሬት ሰፊ ስለሆነ መነጠቅ አለባት ” ብሎ ተናገረ፡፡
እምነትአልባ የነበረው ኮሚኒስቱ ደርግ ፣ ካልጠፉ ቀናት እሮብ እና አርብ ላይ ህዝብ ስጋ እንዲበላ ሲያስገድድ የነበረው ደርግ እንኳ እጁን ያላነሳባትን እምነት እንዲሁም ህውሃት እንኳን ያልደፈሩትን አይነኬ የሆነውን የሀይማኖት ጉዳይ ውስጥ ዘሎ ገብቶ የጃራን የጦርነት አዋጅ አውጆ ጦርነቱን ለማስጀመር እየተዘጋጀ ነው።
ይህንን ሃሳቡንም እንዲያስፈፅሙለት ፣ የአዲስ አበባ ከንቲባ እንዲሆን ህግ ከመሬት ተፈንቅሎ ተዘጋጅቶለት ፣ ወደ ስልጣል የመጣው ታከለ ኡማ ፣ በአዲስ አበባ የሚገኙትን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሬቶች በግማሹ እንዲወርሱም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡ በነብሰ በላው ጃራ መንፈስ የሚነዳው ፣ ጀዋር ይህ በኢትዮጵያ ምድር ገብቶ በሐይማኖት ጉዳይ ላይ ፣ የፖለቲካ ጦርነት ያወጀበት የመጀመሪያው አዋጅ ነው ልብ በሉ፤ ይህ እንግዲህ የት እንደሚያደርሰው አብረን የምናየው ይሆናል፡፡
Filed in: Amharic