>

ጃዋር አልባግዳዲ  (መስቀሉ አየለ)

ጃዋር አልባግዳዲ 
መስቀሉ አየለ
የኢትዮጵያ ታሪክ የሚቀዳው ከጥንታዊቷ ኦርቶዶክስ ቤተከርስቲያን መሆኑን ሰይጣንም፣ አህመድ ግራኝም አይክዱትም። አገሪቱ ኢትዮጵያዊ ማንነትን ከመቅረጽ ባሻገር ታቦት ጭምር እየተሸከመች ባህር ተሻግሮ ከመጣው ከቱርኩ፣ ከድርቡሹ ከፋሽስቱ ሁሉ ጋር እየተፋለመች ተሸክማ እዚህ ባደረሰችው አገር ላይ መቀመጣችንን መጠርጠር አይቻልም።
ክብረ-ነገስት የዚህች አገር ህገ-መንግስት ሆኖ በኖረበት ወደ አንድ ሽህ አመት ያህል ቤተክርስቲያን ከአገሪቱ የቆዳ ስፋት ባለ ሲሶ እርስት እና ነገስታቱን እንቆጳዚዮን ቀብታ የምታነግስ የክብር ዘውዳችን እንደነበረች አለመቀበል የታሪክ ለምጻምነት ነው። ሳይንስ ህይወታቸው ሆኖላቸው በስጋዊ ጥበብ ጣራ የደረሱት ምእራባውያን ሳይቀሩ የሰውልጅ( ሆሞሳፒያንስ) እውነተኛ ምንነት ፈልፍለው ለማውጣት የሚደክሙባት፣ በወርቃማ ታሪኳ የሚደመሙባት አገራችን ዋነኛው አሻራዋ ቤተክርስቲያን መሆኗ የጸደይ ንጋት ነው።
ጃዋር አልባግዳዲ ዛሬ ተነስቶ “ቤተክርስቲያን ካላት  መሬት እየተቀነሰ ይሰጠን” የሚል አቤቱታ ሲያቀርብ ማን ተዋግቶ እዚህ ባደረሰው መሬት ላይ ማነኝ ብሎና ማንንስ ወክሎ እንደሚናገር አጠያያቂ ነው።
ጃዋር ሜንጫው ሽህ አላሙዲንና ከቀን ጅቡ የተጣቡ ተውሳካሞች በድፍን የአገሪቱ ግዛት ሁሉ በልማት ስም አጥረው ከያዙት ስፍር ቁጥር የሌላቸው መሬቶች በተጨማሪ እንግሊዝ አገርን የሚበልጥ መሬት የያዘውና ሾላ የሚገኘው የእንግሊዝ ኤምባሲን ጨምሮ፣ ፈረንሳይ፣ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ አሜሪካ፣ ናይጀሪያ ኤምባሲ ወዘተ ስለያዙት ስንት ጋሻ መሬት አንዲት ነገር ሳይተነፍስ ዘሎ ቤተክርስቲያን ላይ መውጣቱ ትናንት የመርዙን ክኒን ወግቶ ወደ አሜሪካ የላከውን የጆነዲን ሳዶ ፕሮጀክት ዳር ለማድረስ አንግቦ የተነሳበት የቁም ቅዠት እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን።
ደግሞም ለመሞት የእውነት ሞት የማያስፈልጋቸውን ያንተ ብጤ የቁም ሙታንን አትይ። ነገር ግን ኖረው የደመቁባትም ሁሉ መጨረሻም በክብር የሚያርፉት በዚህችው ቤተክርስቲያን ጓሮ መሆኑ፣ ከአገር ለወጡትም ቢሆን ዛሬ ላገራቸው ባይበቁ ነገ ለመቀበሪያ ታስፈልገናለች ሲሉ ማረፊያቸውን እዚህችው መሆኑን አስበው እንደሆነ ለማወቅ የሚያስፈልገው እንዳንተ እብድ ሆኖ አለመፈጠር ብቻ ነው።
ሜንጫው ሆይ! እንዳንተ ከረባት በማሰር ሳይሆን  በጨለማው ዘመን ጌሎቲን ሰይፍ ታጥቆ ድፍን ኢትዮጵያን የወረረው አህመድ ግራኝን የቀበረች አገር ባለቤት መሆናችንን ልብ ለማለት ሞክር።
Filed in: Amharic