>
5:13 pm - Monday April 19, 1515

ለአምባገነኖች ጉልበትና ምሽግ መሆናችንን እናቁም ይብቃን!! (ኤፍሬም ለገሰ - ካብ መቋለ)

ለአምባገነኖች ጉልበትና ምሽግ መሆናችንን እናቁም ይብቃን!!
ኤፍሬም ለገሰ – ካብ መቋለ
1–መከላከያንና ፖሊስን በተመለከተ  ከኤታማዮር ጀምሮ እስከ ሻምበል ያሉት መኮንኖች ጥናት ተደርጎባቸው ያላቸው ማዕረግና እውቀት ተመጣጣኝ መሆኑን መመርመርና በአገርም ውስጥ ሆነ በውጭም የሚገኙትን የቀድሞዎችን የኢትዮጲያ ሰራዊት መኮንኖችን ያካተተ  አለም አቀፍ ወታደራዊ ስታዳርን የተከተለ በገለልተኛ አካላት ፈተና እንዲደረግና  ካልመጠኑ ዝቅ እንዲሉ ይገባል ይህንንም የምለው በአሁኑ ሰአት ያሉት አብዛኛው “መኮንኖች” የአንድን ቡድን ጥቅምና አላማ ለማሳካት ተብለው  የተሾሙና  ያስቀመጧቸው በመሆኑ ነው በዚህ መልኩ የህወሃትም ትምክት እየከሰመ ይሄዳል ማለት ነው።
2–ከጎንደርና ከወሎ በጉልበት የተወሰዱት መሬቶችና ህዝባቸው በህገ ወጥ መንገድ በ”ትግራይ ክልል” ውስጥ የተካተቱ በመሆኑ ወደ ቀድሞው ግዛት እንዲመለሱ። የማንነቱ ጥያቄ “ህገ መንግስቱን’ አልተከተለም ሲባል ከመጀመሪያዉኑ ማን አማክሯቸው ነው ወደ ትግራይ ሲያካትቷቸው? “ህገ መንግስት” የሚባለውንስ ማን አስተያየት እንዲሰጡ እድል ሰጣቸው?
ስለዚህ አንድን ህዝብ በጉልበት አንድን ማንነት እንዲይዝ ማድረግ የቅኝ ኣገዛዝ ባህሪ ነው።
3–የደህንነት የመከላከያ በተለይ አየር ሃይል  የቴሌኮምንኬሽን ሴንተር ሁሉም በአስቸኳይ ወደ ፌደራል መንግስቱ መናኸሪያና ቀድሞ ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲመለሱ።
4–የቀድሞው የጌታቸው አሰፋ የደህንነት መረቦች (ከመቀሌ እስከ ቀበሌዎች)  እንዳሉ እንዲፈርሱና ሌላ ከፖለቲካ ነፃ የሆነ ተቋም እንዲቋቋም።
5– የህወሃትና ግብረአበሮቻቸው  ዘራፌዎች በሚስታቸው፡ በውሽማቸው፡ በልጆቻቸው፡ በወንድም፡ በእህት፡  በስጋ ዘመድ እንዲሁም በአንዳንድ ሆድ አደሮች ስም በአገርም በውጭም  ያከማቹት ሃብት እንዲወረስና ለህዝብ አገልግሎት እንዲውል።
6– በህዝብ ላይ ሞትንና አሰቃቂ በደሎችን (ለምሳሌ ጥፍር መንቀል ማኮላሸት አካለ ጎዶሎ ማድረግ ወዘተ) ስደተን ጭምር ያስከተሉ ግለሰቦችና አሸባሪ ቡድኖች በኢንተርፖል ተፈልገው ለህዝባዊ ፍርድ እንዲቀርቡ። እኛ ደግሞ እንደ ህዝብ ከኛ የሚደበቅ ዘላለማዊ ሚስጥር ባለመኖሩ  በጥቆማ መተባበርና ሰላማችንና የአገራችን አንድነት እንደረጋገጥ መስራት ይገባናል።
አመሰግናለሁ።
Filed in: Amharic