>

ለአማራ ቅማንትና..ለአዴፖ የተመዘዙ ቀይ ካርዶች (መንገሻ ዘውዱ ተፈራ)

የአማራና ቅማንት በወራሪ የተያዙ የአማራ ክልል መሬቶች ለአዴፓ የተመዘዙ ቀይ ካርድ
መንገሻ ዘውዱ ተፈራ
በመሰረቱ ከአዴፓ ብዙም የሚጠበቅ ባይኖርም ከደ/ር አብይ አህመድ መከሰት ጋር ተያይዞ እኔም ተለውጫለሁ። ተቆጥሮ ማለቂያ ከሌሌቸው ብዙዎቹ ችግሮቸ በተለይ በወራሪ የተያዙ የአማራ ክልል መሬቶች የወልቃይት ጉዳይ ብሸሸው ብሸሸው የማይለቀኝ ሆኖ፤ይኸው ልይዘው ነው ባለነ መሰረት ትንሽ ተስፋ ጥለን ነበር።
ታዲያ የአማራ ክልል መሬቶችን በወረራ መያዝማ የእነሱ ጓዶችም የህወሀት ህልም የጀመረው ከ1967ዓ/ም ጀምሮ አንደሆነ ይህንም እውን ለማድረግ በተለይ በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ጠንካራና ሰፊ የዘር ማጥፋት መፈፀማቸውን። ለዚህ ደግሞ ህወሃት አይደለም የአማራን ህዝብ የራሳቸውን ህዝብ ሳይቀር ሃውዜን ላይ አቅደው ያስጨረሱ። ከስልጣንና ጊዚያዊ ደስታ ውጭ ሰለ ሰው ያማያስቡ አረመኔዎች ስለመሆናቸው ሰምታችሁ አረጋገጣችሁል ምን ትጠብቃላችሁ? ታዲያ አሁንም የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የመጨረሻዎቹ ትውልዶች ሊጨርሱ ሲሉ አምልጠው ወደ ጎንደር ተሰደው ሲመጡ ምን አይነት እርምጃ ለመውሰድ ተንቀሳቀቀሳችሁ? ለምን በምን ምክንያት ነው ዝምታን የመረጣቸሁ? እኛ እኮ የምታነገሩት ከምተተገብሩት የማይገኛኝ እጅግ አሳዛኝ አስደንጋጭ ሆነብን። በተቃራኒው ህወሀት በምርኮና ሀገር ሲቆጣጠሩ በተጠጋችሁአቸው የነሱ ቢጤ አእምሮ የለሽ ሆድ አደሮችን በመጠቀም እኮ ነው ዓላማቸውን ለማስፈፀም አሰከ አሁኗ ደቂቃ የእኛን ሰላም ነስተው እየሰሩ ያሉት። ለዚህ ደግሞ ከደ/ር አብይ አህመድ ወረዶ መስራት አይጠበቅበትም።
ስለዚህ እናንት የድሮው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ ከቀዩ ካርድ ለመዳን የሚጠበቅባችሁ፦ 
1. የወልቃይት ጠገዴ ጠለምት ራያ ቆቦና ራያ ዘቦ መሬት ወረራ ዓለምንም ጭምር በሚያምታቱበት በተለይ የአማራ ክልል ምናልባትም የመላው ኢትዮጵያን ህዝብ የማይወክለው ህግ መንግሥስት ተብየው ከፀደቀበት 1987 ዓ/ም በፊት በ1984 ዓ/ም መሆኑን ታወቃላችሁ። ይህን ባታውቁ በየጊዜው አያሳወቅናችሁ የአማራ ክልልን ህዝብ በመወከላችሁ እርግጠኞች ከሆናችሁ ይህንን በሰነድ የተደገፈ ፀሀይ የሞቀው ውሽት መታገል ሲገባችሁ የህወሀት ነው ብላችሁ ልታሳምኑን መታገል ምን ማለት ነው? ይህ ወድቀት ነው። የአማራ ክልል ህዝብ ድንገት ባላወቅነው ዘዴ እያስፋራሩአችሁ ከሆነ በሚል መላ ምት ፍራሃታችሁን ለመታደግ ከመሬታችን የገባ ወራሪ ሌባን አናስወጣለን ብሎ ዳር አስከ ዳር እንቅስቃሴ ጀመሮአል። ህወሀትም ይህን በመረዳት በወኪላቸው ወ/ሮ ኬሬያ አህመድ በተለመደው የማጭበርበሪያ ስልት የጥቅም ተገዥ ሰዎችን ሰብስበው ድራማ ለመስራት እየተሯሯጡ መሆኑን በደንብ ታወቃላችሁ። ታዲያ የእኛዎቹ እናንተ አዴፓዎች ትንሽ ተቃውሞ ስለ ተሳትፎአችሁ እንኳ ለማሰማት ስትጥሩ አይታዩም። ህዝብ ግን ይህን የእናንተን ጀሮ ዳባ ልበስ ዝም በሎ እያየ በነበረበት ለማስቀጠል ፈቃደኛ ስላልሆነ በአንዳንድ አከባቢዎች ወደ ትግራይ በሚጓጓዙ አቅርቦቶች ላይ አቅባ በማድረግ ትግሉን በእራሱ ጀምሮአል። ይህንስ አልሰማንም ነው። ሰሙና ይህ እርምጃ መቆም ካለበት አዴፓ እራሱን ሸሽጎ በበራፍ ሰንጥቅ በማየት ሳይሆን ወደ ህዝብ ቀርቦ ጉዳዩን በባለቤትነት መያዝ። አለበለዚያ ግን የቀይ ካርዱ ምዝዣ አንድ ብሎ መቁጠር ነው።
2. የአማራና ቅማንት ጉዳይ ህወሀት ወደ ጎንደር ከገባበት 1983ዓ/ም በነበረከት ይፋ ካወጁበት ቀን በፊት ተወልደን አሁን አስከምንገኝበት ድረስ ምንም መለያ ምልክት የለለን በደስታ ችግርና መከራ ተረዳድተን ተደጋግፈን የምንኖር የተዋለድን አንዳችን ካለ አንዳችን መቆም የማንችል ጎንደሬዎች ነን። ነገር ግን ህወሀት በበረከት ጠቅላይ አዛዥነት ይዘውረው በነበረው ምናልባት አሁንም በግልፅ አለማየታችን አንጅ እየተዘወረ ባለው የድሮው ብአዴን አሁኑ አዴፓ አሰፈፃሚነት የቅማነት ማንነት በሚል፤በእናንተው ቀመር ነገ ደግሞ ከሁለታችን የተወለዱትን ልጆቻችን ከአማራና ቅማንት የተወለዱ የማንነት ጠያቂ በሚል በአማራና ቅማንት መሀል ሆድ የሚያሻክር መርዝ በመርጨት ማዋጋት ነበር። የዚህም ዓላማ እኛን ጎንደሬዎች አማራና ቅማንት በማለት አቅማችን በማሳሳት የልባቸውን ለመስራት የፈጠሩት የአማራ ክልል ህዝብን የማጥፋት ዘመቻ ነው።
ይኸው እኛም ጎንደራዎች የሐምሌ 5 2008 ዓ/ም የጎንደር ጦርነት እና የእነ ሲሳይ ታከለ፤ሰጠኝ ባያብል መስዋዕትነትና አደራ እረስተን ዛሬ አነ በረከት ሰፈረው በሰጡን የማን አባቱ ገደል ጋባ ወንድማማቾች ማጣላት ተቀብለን ነፍጥ አዘጋጅተናል። በአንዳንድ ቦታዎችም ተሰክቶላቸው ተኩሱ ተጀምሮአል። አባካችሁ ውድ ወገኖቻችን የአነዚህ ወንድሞቻችን አፅም እሾህ ሆኖ እንዳይወጋን ጎንደርንም ተተኪ ትውልድ እንዳያሳጣትና የህወሀት መፈንጫ እናዳናደርጋት ደጋግመን እናስብ።  እንደምናስታውሰው በ2008 ዓ/ም ህዝብ አንድ ሆኖ በእኛ መሐል ልዩነት የለም ዘውር በሉ አንሰማችሁም ሲላቸው ከሌላ አካባቢ የማይታወቁ ሰዎችን አታለው በማስገባት በሽንፋ አካባቢ የሰው ደም አፋሰዋል። አሁንም የዛሬው የዚያ ቅጥያ ነው። አዴፓም ይህንን በዚች ሁለት ቀን ውስጥ ወደ ህዝብ ወርዳችሁ ከህዝብ ጋር በመሆን ካልሰራችሁ የቀይ ካርዱ ምዝዣ ሁለት በሉ።
በአጠቃላይ ይህ ጉዳይ ያሳሰበው በጎንደር ከተማ ኑዋሪዎች ሙሉ እውቅና የተቋቋመው የጎንደር ሰላምና ልማት ሸንጎ ምንም አንኳን ለዚህ ችግር በአስፈፃሚነትም ሆነ በተጠያቂነት ከአማራ በኩል በአደባባይ የተቋቋመ ኮሚቴ ባይኖርም ከቅማንት በኩል የተቋቋሙትን የቅማንት ማንነት አስፈፃሚ ኮሚቴዎች በፖሊስ ጣቢያ በነበሩበት ጊዜ በአካል በመገኘት ጠይቆ ቀርቦ አነጋገሮአል። ከዚህም መረጃ በመነሳት ለችግሩ መፍቻ መንገድ ሆኖ ያገኘው ከአማራና ቅማነት ገለልተኛ የሆኑ አባላት ያሉበት አንድ ኮሚቴ በማቋቋም ከህዝብ ጋር በቀጥታ በመነጋገርና ከግጭት የሚገኘው ህይወት መጥፋትና ንብረት ወድመት መሆኑን ማስተማር። ይህ ሳይታያቸው ወደ ስህተት የገቡም ካሉ ስህተቱን በማረም በነበረው አንድ ሆኖ መለያየትና ሁለት መሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ በልዩነት ያለመጎዳዳት አብሮ መኖር መቻሉን በመረዳት ወደ ሰላም ለመመለስ ነበር።
ሆኖም ግን ከአንዳንድ መረጃዎች መከታተል አንደተሞከረው በዚህ ኮሚቴ ውስጥም ተልዕኮ ያዘሉ ሰርጎ ገቦች አንዳሉበትና የተፈለገው ውጤት ስለመምጣቱ አጠራጣሪነት ጭምጭምታ ይሰማል። በዚህ ጉዳይ አዴፓም ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ከዚህ ኮሚቴ ጎን በመሆን ሰላምን ያረጋግጣል ብለን ስንጠብቅ ሰምቶ አንዳልሰማ ድምፁን አጥፍቶ ይታያል። ለዚህ ግምት ማረጋገጫው ህፃናት፤ ወላዶች፤አዛውንቶች ከቋራ፤መተማና ሌሎች አካባቢዎች ተሰደው በኬንዳ ውስጥ በየቦታው መገኘታቸው ነው።
ሰለዚህ አዴፓ ይህን ለሰላም መታወክ ከፊቱ ተደቅኖ ያለ የአማራና ቅማንት እንዲሁም በወራሪ የተያዙ የአማራ ክልል መሬቶች ጉዳይ ነገ ዛሬ የማይባል ዛሬውኑ መጀመር ያለበት ተግባር ነው። አለበለዚያአዴፓ( የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት) ነኝ የሚል እምነት ካለው በቀናት ውስጥ በየአስተዳደር እርከኑ ካሉ የአሱ ካድራዎች ጋር ሳይሆን ወደ ሰፊው ህዝብ እራሱን አቅረቦ በመነጋገር ከህዝብ ለመነጨ የመፍትሔ ሃሳብ ድጋፉን በማሰየት ለመሪነት መዘጋጀት የግድ ይለዋል። በመሆኑም አዴፓ ክልሉም ሳይናጋ በተመዘዙት ቀይ ካርዶች ግባዓተ መሬቱ አውን ሰለመሆናቸው ጥርጥር ሳያሻው የመጫውቻ ቦታውን በመልቀቅ ህዝብ ተተክቶ የአማራ ክልልን የማረጋገትና ወደ ሰላሙ የመመለስ ስራ እንዲሰራ ቢተው። በአውቅትና አቅም ማነስ አለመቻል ሽንፈት ሳይሆን አንደገና ለመማርና አቅም ለማዘጋጀት መነሳት አዋቂነት ነው።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
Filed in: Amharic