>

የማይነጋ ክፉ ሌሊት - የማይጨልም ብሩህ ቀንም የለም!!! (የሺሀሳብ አበራ)

የማይነጋ ክፉ ሌሊት – የማይጨልም ብሩህ ቀንም የለም!!!
የሺሀሳብ አበራ
ትህነግ ጌታቸው አሰፋን በትግራይ  ህዝብ መሾሟ፣ የትግራይ ህዝብ ዝም ማለቱ ለታሪክ አይመችም፡፡ ፋሽስቱን ሞሶሎኒ የሰቀለው የጣሊያን ህዝብ ነው፡፡ ሂትለርን የካደው የጀርመን ህዝብ ነው፡፡ ጠቅላይ አቃቢ ህጉ እንዳሉት ወንጀለኛ ብሄር የለውም፡፡ ከወንጀል ጋር መተባበር ታሪክን አጠይሞ ፣ ነገ አንገት ደፊ ትውልድ እንዲፈጠር መሰረት ይጥላል!!!
የሰው ልጅ የርህራሄ ወለሉም ሆነ የጭካኔ ጣራው የሚያርፍበት ወሰን አለው፡፡ በዚህ ወሰን መሰረትም ህጎች ይሰራሉ፡፡
 …
በኢትዮጵያ  በትህነግ መሪነት የተሰራው ግፍ  ግን ከሰው ልጆች የባህሪ ወሰን ሁሉ ያልፋል፡፡የብልት ቆዳ ከመግፈፍ እባብ እያረቡ ከእባብ ጋር እስከ ማሳደር የደረሰ የህይወት  ቅጣት በሰው ልጆች ላይ አድርሳለች፡፡
 …
የትህነግን ክፉነት የዓለም የወንጀለኞች ማህደር ሁሉ ከወንጀል ሜኖው(ዝርዝር)  ውስጥ ይተርፍበታል፡፡ ከባዱ ነገር ግን ትህነግ ህዝብን እወክላለሁ ማለቱ ነው፡፡ትህነግ ሰው አይደለም፡፡የሰው ልጅን ባህሪ አይወክልም፡፡
 ..
የማይነጋ ክፉ ሌሊት፣የማይጨልም ብሩህ ቀንም የለምና  ትህነግ እስከ ክፋቷ ግፏን ታቅፋ  ወደ ምታውቀው መስሪያ  ቤት እያቀናች ነው፡፡
ወጣቱን ሳሙኤል አወቀ ማርቆስ ላይ ያስገደሉ ደህነቶች እና የጎንደርን እስርቤት ያቃጠሉት ሁሉ ወደ ዘብጥያ ወርደዋል፡፡
 …
የክፉዎች ጊዜ አጭር ነው፡፡ ፋሺስቱ ሞሶሎኒ ተሰቀለ፡፡ናፖሊየን ቦናፓርቲ ታሰረ፡፡ተገደለ፡፡ሂትለርም ተሸነፈ፡፡ተገደለ፡፡ገዳዮች ሞትን በደብዳቤ ጠርተው ይሞታሉ፡፡የትህነግ ታሪክም ከዚህ የተነጠለ አይሆንም፡፡ሆኗል፡፡
 …
ትህነግ በሰው ልጆች ሁሉ በታሪክ ውስጥ ተሰርቶ የማያውቅ የወንጀል መሪውን ጌታቸው አሰፋን በትግራይ  ህዝብ መሾሟ፣ የትግራይ ህዝብ ዝም ማለቱ ለታሪክ አይመችም፡፡ ፋሰሽስቱን ሞሶሎኒ የሰቀለው የጣሊያን ህዝብ ነው፡፡ ሂትለርን የካደው የጀርመን ህዝብ ነው፡፡ ጠቅላይ አቃቢ ህጉ እንዳሉት ወንጀለኛ ብሄር የለውም፡፡ ከወንጀል ጋር መተባበር ታሪክን አጠይሞ ፣ ነገ አንገት ደፊ ትውልድ እንዲፈጠር መሰረት ይጥላል፡፡
 …
በሌላ በኩል አዴፓ ከጥገኝነቱ ተላቆ በራሱ እየቆመ ነው፡፡ በራሱ ሲቆም አዴሃን ቀላቅሏል፡፡ የአዴሃን እና የአዴፓ ጋብቻ የአብርሃም እና የሳራ ሆኖ በግብር እንደ ያዕቆብ  አይነት ትውልድ እንዲፈጠር ምኞቴ ነው፡፡ ከፓርቲ ጋጋታ ወጥቶ አንድ የጠነከረ መስመር መዘረጋት ብዙ ተከታዮችን አፍርቶ የስበት ማዕከል ለመሆን ወሳኙ መንገድ ነው፡፡
….
የአማራ ፓለቲካ በሁለት ጨረሮች ብቻ መመራት አለበት፡፡በአዴፓ እና በአብን፡፡ሁለቱም እጃቸውን ዘርግተው   የዓላማ ተመሳስሎሽ ያላቸውን እየተቀበሉ ነው፡፡ እነ መአህድ  እና መሰሎች ከአብን ጋር ቢቀናጁ ፣ሌሎችም እንደ አማራጫቸው ቢቆራኙ  እንደ ማዕበል የሚቀያየረው የኢትዮጵያ  ፖለቲካ ይረግባል፡፡
 ….
 ህዝብ መሪን ይወልዳል፡፡ ጠያቂ ህዝብ ዲሞክራሲን ይገዛል፡፡እምቢባይነት ለዲሞክራሲ  መሰረት ነው፡፡አጎብዳጅነት እና አዳሪነት የባለፈውን ጊዜ በልቶብናል፡፡የህዳሴ ግድብ ብር ሲበላ፣ሜቴክ 37 ቢሊየን ያለጫራታ ሲወስድ፣አውሮፕላን እና መርከብ ሲዘርፍ ጠያቂ አልነበረም፡፡ ትህነግ ህዝብ ሲዘርፍ እምቢ ባይ አልነበረም፡፡ ለዚህ ሁሉ ጥፋት መነሻው አጎብዳጅነት፣ፍርሃት እና ግለሰብኝነት የተባሉ ነቀርሳዎች ናቸው፡፡
 …
ትናንት ከፊታችን ቀድሞ እንዳይመጣ ማንበብ፣መጠየቅ፣ነገሮችን መተንተን ሁሌም ያስፈልጋል፡፡
Filed in: Amharic