>

ይድረስ "ከእኛ ወዲያ ወያኔ ለአሳር " እያላችሁ ቁም ስቅላችንን ስታሳዩን ለነበራችሁ ኮካዎች!!! (ፍርድአወቀ ነጋሽ)

ይድረስ “ከእኛ ወዲያ ወያኔ ለአሳር ” እያላችሁ ቁም ስቅላችንን ስታሳዩን ለነበራችሁ ኮካዎች!!!
ፍርድአወቀ ነጋሽ.
ስለግድያው ፣ ስለዘረፋው ፣ ከሀገር ይልቅ ዘር ስላስቀደመ ፖለቲካቸው … በቁጭት እያነሱ የዘር ገመድ ሳይጎታቸው ከህዝብ ጎን ለቆሙ እና ተቃውሟቸውን በአደባባይ ሲገልጹ ለነበሩ ክብር አለኝ!!
የቀን ጅቦቹን ስራ ከረጀም ጊዜያት ጀምሮ የምንሰማው የነበረ ቢሆንም “” ሃገራችን እያሉ ነገር ግን ስለሃገራቸው ምንም ደንታ ስለሌላቸው “” መሪ የሚያስፈለጋቸው ሆነው መሪ ነን ሲሉ ለነበሩ ወራዳ የወያኔ ቱባ ባለስልጣናት ክፋት እና አንጀትን የሚያቃጥል ዘረፋ ይፋ ሆኖ ሜዲያዎች ባሉበት መግለጫ ሲሰጥበት ስለነበረው ጉዳይ ነበር።
ሜቴክ የኢትዮጲያ ህዝብ ንብረት ነው ሲሉ ያዝጉን የነበሩት እነዚህ “ሞላጫ” ሌቦች የሃገሪቷን ንብረት እንደፈለጉ ሲመዘበሩ የነበሩ ” ቆሻሻ ወንበዴዎች” መሆናቸውን የዓለም ህዝብ በይበልጥ ደሃው የኢትዮዺያ ህዝብ በሚገባ እንዲሰማው የተደረገበት ሁኔታ ነበር ።
ይህ በቢሊየንስ የሚቆጠር ገንዘብ ባለእዳው ትላንትም ነገም ከፋዩ ምስኪኑ የሃገሬ ህዝብ መሆኑን ሳስብ ደግሞ ንዴቴ እና ቆጭቴ ይበልጥ ይጨምራል። በነገራችን ላይ ይህንን ሁሉ በአንድ ዘር ብቻ የተሰባሰቡ ህሊና ቢስ መሃይማን ሲዘርፉ ፣ ሲተባበራቸው የነበረ ግን ሆዳም አማራ ፣ኦሮሞ፣ ጉራጌም ሆነ ሌላም ብሄር መኖሩ ግልጽ ነው።
ከምንም በላይ የሚያናድደው ደግሞ ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩላቸው የነበሩ በውጭ ሃገር በሰላም የሚኖሩ ከርሳም ሆድ አደሮች ከመቼውም የበለጠ አንገታቸውን የደፉበት እለት ስለሆነ ፈጣሪዬን አመስግኜዋለሁ።
በሰው ልጅ መብት ጥሰት ዙሪያ ሃገራችን ውስጥ ስለሚደረገው የማፊያ ቡድን ክፋት ለመቃወም በተለያየ ቦታ እና ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ ስንወጣ እና ስንቃወም ” እናንተ ስራ የሌላችሁ ” እያሉ ስለሃገራችን ሳይሆን ስለሚያመልኳቸው እነዚህ ወራዶች የአስራ አንድ ፐርሰንት እድገት እና ስለህዳሴያቸው ግድብ ሲደሰኩሩ የነበሩ እዚሁ አጠገባችን ስላሉ ሰውነታቸው አውሮፓ ጭንቅላታቸው ደግሞ ደደቢትን ስለሚያስቡ አቃጣሪዎች የአይጥ ምስክር ድንቢጦች ሃፍረት እና አንገት መድፋት ስንመለከት ልባችን ሃሴትን አድርጋለች።
እውነት ተደብቃ አትቀርም !!!
*** ማነህ አንተ በተቃውሞ ሰልፍ ላይ የመሃል ጣትህን ስታወጣ የነበርክ ወራዳ – ና – እና የአጎቶች ህን ሌብነት እና ወራዳነት ተመልከት።
*** ማነህ ሌላኛው ስልክህን ይዘህ ፎቶ ስታነሳን እና ለኤምባሲ ስትሰጥ የነበርክ ከርሳም ዘመዶችህ ወንድን ሳይቀር ሲደፍሩ እና ሲያስደፈሩ እንደነበር ተመልከት።
*** ሌላኛው ሆዳም አማራ እና ኦሮሞ ሆነህ የደደቢት ደደቦች ስለሚሰሩት ግፍ ብርድ ላይ ቆመን ስንቃወም ባንዲራቸውን ይዘህ ህዳሴአችን መዝሙርህን ስትዘምር የነበርክ – ና – እና ወገኖችህ እንዴት እንደተነገደባቸው ኢቢሲህን ክፈት እና መርዶህን ጠጣ።
*** ሌላኛው ደግሞ በኢንቨስትመንት ሽፋን የአየር ትኬት ተሰጥቶህ ከዚህ ሃገር ሄደህ እንድትመለከት እና እድገት እድገት ዘፈንህን ስትዘፍን የነበርክ አባይ ድልድይ ላይ ቆመህ ፎቶህን የለጠፍክ እና የሰው ልጅ መብት ሲጣስ የአንተን የሃምሳ ሜትር ድልድይ በአድናቆት ስትደሰኩር የነበርክ እንከፍ ቲቪህን ከፍተህ ይህንን ዘግናኝ ዘረፋ እና ለሆድህ እንደውሻ የተጣለልህን ቅንጥብጣቢ እያስታወስክ ሃፍረትህን ዋጥ።
*** አንቺ ደግሞ ማነሽ ያለአግባብ የወጣቶች ህይወት ሲቀጠፍ በተቃውሟችን የተሳለቅሽ እና የተገደሉት “” ዱርዬዎች “”ናቸው እያልሽ ለልጆችሽ ሳይቀር ክፋትን ያስተማርሽ ከንቱ እንደልማድሽ ፌስቡክሽን ከፋፍተሽ አፍሽን የከፈትሽብንን እኛን በጨው ባጠብሽው ዓይንሽ ፣ አፍሽን የከፈትሽላቸውን እነዚህን አርኩሳን የደደቢት ደደቦች ደግሞ ባደረ አይንሽ ለመመልከት ሞራልሽን ሰብስበሽ ነይ ።
*** መቶ ፐርሰንት የኢትዮጲያ ህዝብ መርጧቸው ነው እያልክ ስትለፋደድ የነበርክ አንተኛው ደግሞ አንድ ሺህ ፐርሰንት የኢትዮጲያን ህዝብ የዘረፉትን የጡት አባቶችህን ሌብነት ለመመልከት እንኳን አበቃህ።
እረ ለመሆኑ እንዲህ “ከእኛ ወዲያ ወያኔ ለአሳር ” እያላችሁ ቁም ስቅላችንን ስታሳዩን የነበራችሁ ኮካዎች አለቆቻችሁ በብርሃን ፍጥነት ሶስት መቶ ስልሳ ድግሪ ተሽከርክረው እያሉ ያሉትን ሰምታችሁ ይሆን? ካልሰማችሁ ላስነብባችኋ:-
የትግራይ ህዝብና መንግስት ሀገር እንዲዘረፍ አይደለም የታገሉት። ሀገርና ህዝብን የዘረፉ መሪዎች ህግ ፊት እንዲቆሙ ህዝቡም ሆነ የትግራይ ክልል መንግስት ቁርጠኛ ነዉ። አሁንም ቢሆን የፌደራል ፖሊስ ለምርምራ
የሚፈልጋቸዉና በትግራይ ክልል ያሉ ግለሰቦችና መሪዎችን አሳልፎ ለመስጠት ክልሉ ዝግጁ ነዉ።”
ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል የትግራይ ክልል ም/ ፕሬዝዳንት ማምሻዉን ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል አመራሮች ከተናገሩት፣
እነዚህ መሃይማን ዘራፊዎች የትግራይ ህዝብን እንደማይወክሉ አሁንም ወጥቶ መናገር ያለበት የትግራይ ህዝብ ነው። በርግጥ ማስፈራራቱ እና እንግልቱ አዚያ ሃገር ቤት ያለው ደሃው የትግራይ ህዝብ ላይ ቢበረታም አሁን እንኳን በስማችን መነገዳችሁን አንፈልግም ብሎ የመናገሪያው ጊዜ ነውና ውጡ እና ተናገሩ።
እነዚህ ሌቦች የዚያን አካባቢ ሰው የማይወክሉ ስለመሆናቸው ከአመታት ጀመረው ሲጸየፉ እና ሲጽፉ የነበሩ ጥቂት የዚያው ብሄረሰብ ነገር ግን በኢትዮጲያዊነታቸው የማይደራደሩ ግለሰቦች
– ስለግድያው
– ስለዘረፋው
– ስለርካሽ ፖለቲካቸው
– ስለ ሆዳምነታቸው እና አልጠግብ ባይነታቸው እንዲሁም ህዝብን በጅምላ ፈርጀው ስለመግደላቸው ባላቸው አቅም ሁሉ ከጭቁኑ ህዝብ ጋር የወገኑ እና የተቃወሟቸው የረጅም ጊዜ ተከታያቸው ስለነበርኩ በደንብ እከታተላቸው ስለነበር ጥቂት ግለሰቦች ለመመስከር እና ከደሃው ጋር ስለወገናችሁ እናንተ ውድ የኢትዮጲያ ልጆች ናችሁ እና እንኮራባችኋለን ብዬ ለመናገር ቃላት ስለሌለኝ በበኩሌ ከምስጋና ውጭ ምንም ስለማልቸራችሁ ክብር ይገባችኋል።
• ከእውነት ጋር የወገናችሁ ናችሁ እና ህሊናችሁ ሁሌም እረፍት እንደሚኖረው ስነግራችሁ ደስ እያለኝ ነው። ሌሎችም ሽርጥን አንገታችሁ ላይ ጠምጥማችሁ በየጭፈራው ላይ ያልደነፋችሁ
• በትግራይ ህዝብ ስም ሲነገድ ምንም እንኳን ወጥታችሁ ለመናገር የያዘ ነገር ቢይዛች ሁም አንዲት ቀን እንኳን ከዚያ ብሄር ስለተፈጠርኩ የተለየሁ የወርቅ ህዝብ ነኝ ያላላችሁ
• በትግራይ ተራራ ላይ የአማራ መቀበሪያ ” ኮንሰርት” ላይ አሽክርክሪት ጭፈራን የተጸየፋችሁ ዝምታችሁ ከምን የተነሳ ሊሆን እንደሚችል ስለምናውቅ ወገኖች ናችሁ እና ትመሰገናላችሁ።
እንግዲህ እዚህ ደርሰናል ።
ይህ ወቅት የሚያስተምረን ሁለት ትልልቅ ትምህርቶችን ነው።”
የመጀመሪያው በዘር መደራጀትን ለሌብነት እና ቅጥፈት መጠቅሚያ ማድረግ የአንድን ትልቅ ህዝብ ማሳነስ ሲሆን እና ሃገርን እንደ ሃገር ማስቀጠልን ፈተና ውስጥ የሚከት ስለሆነ አሁንም ተባብረን እና አንድ ሆነን ትልቋን ኢትዮዺያችንን የበለጠ ትልቅ ማድረግን መስራት እንደሚኖርብን ሲሆን
ሁለተኛዉ ደግሞ የፈለገ ቢሰርቁ የፈለገ ቢገድሉ፣ የፈለገ ቢያፈናቅሉ እና እንደፈለጉ ቢታትሩ የክፉ ሰው ስራ እና ውርደት ጊዜውን ጠብቆ እንደዚህ መውጣቱ አይቀርም እና አሁን በስራ ላይ ያሉትን አዳዲስ አመራሮች ህግን ተከትለው ራሳቸውን ብቻ ሳይሆን ሌላውንም በእኩልነት እንዲመለከቱ ይረዳቸዋል ብዬ አምናለሁ።
ይህንን ያሳየንን አምላክ ከማመስገን ውጭ የምለው ነገር የለኝም።
ቸር እንሰንብት!!!
Filed in: Amharic