>

ጠለቅ ብለን ስንመረምረዉ ይሄን እናገኛለን - እስኪ ለአቃቢ ህጉ አድርሱት!!! (ሚኪ አምሀራ)

ጠለቅ ብለን ስንመረምረዉ ይሄን እናገኛለን – እስኪ ለአቃቢ ህጉ አድርሱት!!!
ሚኪ አምሀራ
አደም ሀሚድ ሱሌማን ኦሪጅናሊ ኤርትራዊ ሲሆን የካናዳ ዜግነት አለው ዱባይ የሚኖር ሲሆን ኤርትራ ስትገነጠል አሰብና ምጽዋ የነበሩ መርከቦችን ከኤርትራ መንግስት ጋር በመመሳጠር እጁ አስገብቶ የመርከብ ባለቤት የሆነ ግለሰብ ነው። በህግ የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ብቸኛ import export አጓጓዥ ከመሆኑ በፊት ዝቅተኛ የጭነት ዋጋ በመጠቀም ንግድ መርከብን ከጭዋታ ውጭ አድርጎት ነበር በአንድ ወቅት የኢንሹራንስ ብር ለማግኘት ሲል አንዷ መርከብ መኪና ጭና ወደ ምጽዋ ወደብ ስታመራ በእቅድ እንድትሰጥም ካደረገ በኃላ ብዙ የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ሀብት አክስሯል ከኢትዮጵያም ከኤርትራም መንግስት ጋር ተጣልቶ ዱባይ ይኖር ጀመር ከጊዜ በኃላ ኢንቨስተር ተብሎ የቀድሞው ያኮና ኢንጅነሪንግን ከንግድ ባንክ ላይ ያለ ጫረታ በ 1 ሚሊየን ዶላር ገዝቶ ወደ ኢትዮጵያ መጣ እስከ አሁን ድረስ የቀድሞው ያኮና ኢንጅነሪንግ የአሁኑ ኢንተር ኤመሬት ኢንደስትሪ ተብሎ ከሜቴክ ያለ ጨረታ ስራ እየተሰጠው የትራንስፎርመር ቦዲ እና ብዙ ስራውችን ከሜቴክ ሰዎች ጋር በሽርክና ይሰራል።
አደም 50 ሺ ዶላር የሚገዛን እቃ 250 ሺ ብሎ ፕሮፎርማ በማሰራት ዱባይ ወደ ሚገኘው ናሮ ትሬዲንግ ወደሚባለው ወደ ራሱ ድርጅት ዶላር ያሸሻል ከሜቴክ የሚያገኘውን ብር በዚህ መልኩ ወደ ዱባይ ያሸሻል ከሜቴክ ሰዎች ጋር የጥቅም ተጋሪ ሆነው ይሰራሉ ።  ድርጅቱ ግቢ ውስጥ የአቶ አደም መኖሪያ ቤት አለ እና እዚህ ቤት ውስጥ ትልልቅ እቅዶች ይነደፋሉ አደም ይመክራል እነሱ ተግባራዊ ያደርጋሉ ። አደም ከየትኛውም አለም ምንም አይነት ነገር መስራት የሚችል ኮንታክትም አለው ብርም አለው። ከመድሀኒት እስከ ጦር መሳሪያ እና አውሮፕላን ድለላ ይሰራል።
አደምን ብሄራዊ ባንክ በዶላር ማዘዋወር ምክንያት ብላክ ሊስት ዉስጥ አስገብቶታል፡፡ ይህች አዉሮፕላን የሳውድ አረቢያው የቀድሞው ልኡል የግል አውሮፕላን ናት መጀመሪያ ለፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ሊሸጥለት በ ጻድቃን በኩል ብዙ ተሞከረ ግን ስላረጀች ጻድቃን ዋጋዋ ተወደደ ብሎ ከፈረንሳይ አዲስ እንድትገዛ ምክር በመስጠቱ የሱዳኑ ሳልቫኪል ሳይገዛት ቀረ ከዛ ክንፈን ግዛት ብሎ አደም ማግባባት ጀመረ ከዛ ክንፈ ወደዚህ ስራ ገባበት፡፡ ከአዉሮፕላኗ ስር ፎቶ ሚነሳዉ አደም ሲሆን ፎቶ አንሽዉ ትናንት ከሁመራ ያመጣነዉ ሰዉየ ነዉ፡፡
በነገራችን ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ጉዳይ ZTE እና አንድ ሌላ ድርጅት ማስፋፊያ ተብሎ የመጣዉ 5.5 ቢሊየን ዶላር ጉዳይ እየመረመርኩት ነዉ ፡፡ ጉዱ ብዙ ነዉ፡፡
¤¤¤¤¤
የተወልደ እና የክንፈን አዉሮፕላን ጉድ!!!
 
አዉሮፕላኗ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊዝ የተደረገቸዉ ከ 2007 እስከ 2010  ድረስ ከሆነ ከደች ድርጅት (leased from Deutsche Structured Finance Jun 2007) ነዉ፡፡ 2010 ላይ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊዝ ያደረገዉ ድርጅት ስም የለም (hidden) ይላል፡፡
እዚህ ላይ ነዉ ጉዳዩ አዉሮፕላኑዋን 2010 ላይ ተወልደ ገዛት እና ኢትዮጵያ አየር መንገድ ዉስጥ ይነግድባታል፡፡ ሪማርክ ሚለዉን እዩት፡፡ ምርመራዉ እዚህ እየደረሰ ነዉ፡፡ ሶስተኛዉ ምስል ላይ 2010 ባልታወቀ ሰዉ ከድርጅቱ እንደተገዛ እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሊዝ እንደተደረገ ያሳያል፡፡ይቀጥላል፡፡ ከሰአት ከሁመራ አዲስ ከገባን በኋላ አንድ ከፍተኛ ኦፐሬሽን አለን፡፡ወደ በኋላዉ እንገልጸዋልን፡፡
Filed in: Amharic