>

ዶ/ር አብይ ወደ አክሱም ዩኒቨርሲተው መሄዳቸው ከግጭቱ በስተጀርባ ትልቅ የፖለቲካ ሴራ እንዳለ አመላካች ነው! (ናስትሮዳሙስ ኪንግ)

ዶ/ር አብይ ወደ አክሱም ዩኒቨርሲተው መሄዳቸው ከግጭቱ በስተጀርባ ትልቅ የፖለቲካ ሴራ እንዳለ አመላካች ነው!
ናስትሮዳሙስ ኪንግ
 
የጠቀላይ ሚንስትሩ የአክሱም ጉዞ ሚሽን ክሪቲካል ነው፡፡ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ ወደ አክሱም አቅንተው የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ እንደሚያነጋግሩ መዘገቡ በጥንቃቄ ሊተነተን ይገባል፡፡ ምክንያቱም፡-
1. በቅርቡ የደብረ ማርቆስና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ሁለት ተማሪዎቻቸውን ዘርን መሰረት ባደረገ መልኩ በድንጋይ ተወግረው እንዲገደሉ ከመደረጉ ጀርባ የመንግስታ የፖለቲካ ሴራ እንደሆነ የማያምን ካለ ይከስራል፡፡ ወቅቱ ተማሪ እርስ በእርስ ሊጣላ ቀርቶ የሚበላውን እና የሚጠጣውን የማያውቅበት ነው፡፡ ግድያዎቹ  የተፈጸሙት ተማሪዎች ለማጠቃለያ ፈተና በተዘጋጁበት እና በጥናት የሚበሉና የሚጠጡትን በማያውቁበት ( በግቢ ቋንቋ ቴንሽን በሚኖርበትወቅት) ነው፤
2. የሞቱት ተማሪዎች የትግራይ እና አማራ ተወላጅ ብቻ መሆናቸው እና የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል መንግስታትት እና ህዝብ እርስ በእርስ እንዳይተማመን እና ወደ ግጭት እንዲገባ በስሌታዊ ቀመር የተሠራ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ገዳዮቹ እነማን እንደሆኑ አለመታወቁ ስውር የመንግስት የስለላ ድርጅቶች እጅ እንዳለበት በቀላሉ መገመት ይቻላል፤
3. ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ላይ ተማሪው ከሞተ በኋላ ሁሉም የትግራይ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ለቀው ወደ አዲስ አበባ እና ትግራይ የሄዱ ሲሆን በተለይ የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ፍላጎት እንዳለው በማስታወቂያ ሳይቀር አሳውቋል፡፡
4. በሌላ በኩል አክሱም ዩኒቨርሲቲ የአማራ ወጣት ሲገደል ተማሪዎች ተረጋግተው መፈተን ስለማይችሉ ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ ያቀረቡትን ጥያቄ ዩኒቨርስቲው ባለመፍቀዱ ተሸከርካሪ እንኳ እንዳይጠቀሙ  በከለከሉም ተማሪዎቹ በእግራቸው መንገድ ከጀመሩ በኋላ ይህ የሴራ ማስፈጸሚያ የሆነ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሴኔት ህጉ መሠረት መልቀቅ እንደሚችሉ ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡ ይህም የሆነው መንገድ የጀመሩት ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ፎርም ሞልተን እንውጣ ብለው ሊመለሱ ይችላሉ ከሚል በመነጨ ሀሳብ ነው፤
5. ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደ ዩኒቨርሲተው መሄዳቸው ደግሞ ከግጭቱ በስተጀርባ ትልቅ የፖለቲካ ሴራ እንዳለ አመላካች ነው፡፡ በአንድ በኩል በቅርብ ጊዚያት ህወሀት የትግራይን የነጻ መንግስትነት ጥያቄ ለማስፈጸም የሚያስችለውን የመጨረሻ ፍኖተ- ካርታ ለመንግስት ያቀርባል በሚባልበት ጊዜ የጄኔራል ሰዓረ (የህወሀት ቀድሞ ታጋይ)  ከዓብይ ጋር ወደ አክሱም መጓዝ ህወሀት እና ኦዴፓ/ኦነግ በጋራ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ብሎም አማራን በግራ ቀኝ ለማዋከብ የሚያስችል ምስጢራዊ ውይይት ለማድረግ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡
ስለሆነም ጠቅላይ ሚንስት ዓብይ ከመለስ ዜናዊ የበለጠ እና የረቀቀ በቀላ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸሙ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡ በአሁኑ ጊዜ ለማ መገርሳ ታመዋል በሚል ሰበብ በመከላከያ ሚንስትር ቦታቸው ሆነው ከጃዋር መሀመድ ጋራ የታላቋን  ኦሮምያ ምሰረታ ዝግጅት እከናወኑ ስለመሆኑ ማስረጃው ጃዋር በኦሮምያ ክልል እየተንቀሳቀሰ በሚሰራው የማደራጀት ሥራ የመከላከያ ሠራዊት እጀባ የሚደረግልት መሆኑ ነው፡፡
በሌላ በኩል እስክንድር ነጋ ጋዤጣዊ መግለጫ እንዳይሰጥ እየተከለከለ ጃዋር በመከላከያ ኃይል መታጀቡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ጃዋር ነው ወይስ ዓብይ የሚል ጥያቄም እያስነሳ ነው፡፡
ለትግራይ መገንጠል እና ለኦሮምያ ሪፐብሊክ ምስረታ እንቅፋት የሆነው አማራ ስለመሆኑ የሚክድ የለም፡፡ አማራ በመላው ኢትዮጵያ መሠራጨቱ ከሁሉም ማህበረሰብ ጋር ተሰባጥሮ መኖሩ ለኦዴፓ/ኦነግ የእግር እሳት ሆኖባቸዋል፡፡ ስለሆነም አማራ ክልልን ብቻ ማጥቃት ህወሀትም ሆነ ለኦነግ/ኦዴፓ ራስን የማጥፋት ያህል ከባድ መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ አማራ የተገፋ ኃይል ነው፡፡ የተገፋ ኃይል ደግሞ አሸናፊ ነው፡፡
Filed in: Amharic