>

ይሄ ለኩሽ መንግሥት መስራቾች ትልቅ ድል ነው!!!  (ዘመድኩን በቀለ)


ይሄ ለኩሽ መንግሥት መስራቾች ትልቅ ድል ነው!!! 
ዘመድኩን በቀለ
★ ይህቺ አጭር ጦማሬ ለታሪክና ለምስክርነት  ትቀመጥልኝ።
 “ ኦ እግዚኦ አእርፍ ነፍሳተ አግብርቲከ ኩሎሙ ክርስቶሳውያን ” ።
• ሟቾቹ፣ የተገደሉት ሁሉም ሰሜነኞች፤ ነገደ ሴማውያን፤ ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች መሆናቸው ስታይ ደግሞ ሌላኛው አስገራሚ መገለጥ ይመጣብሃል።
• ሁለት ትግራዋይ፤ 4 ዐማራ ተቀንሷል።
• አሁን የከሚሴው ጭፍጨፋ ፋይል ይዘጋል። በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙት ተጠርጣሪዎች በሙሉ ይፈታሉ። በጉዳዩ ላይ ወንጀለኞቹን አድኖ ለፍርድ በማቅረብ ሥራ ላይ የነበሩት በሙሉ በአንድም በሌላም ምክንያት እንዲወገዱ ተደርገዋል።
• ዶር አምባቸው መኮንን የዐማራ ክልል ፕሬዘዳንት። [ ዐማራም ኦርቶዶክስም ነው። ተገድሏል ]
• አቶ እዘዝ ዋሴ የክልሉ የፖለቲካ አደረጃጀት ሓላፊ። [ ዐማራም ኦርቶዶክስም ነው። ተገድሏል ]
• አቶ ምግባሩ ከበደ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሓላፊ። [ ዐማራም ኦርቶዶክስም ነው። ተገድሏል።]
• ብ/ጀ አሳምነው ጽጌ የክልሉ የሰላምና ደኅንነት ሓላፊ። [ ዐማራም ኦርቶዶክስም ነው። ተገድሏል።]
• አቶ አበረ አዳሙ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽ ሓላፊ [ የታሰሩ ]
• ብ/ጀ ተፈራ ማሞ የክልሉ ልዩ ሓይል ሓላፊ [ የታሰሩ ]
★ ጀነራል ሰዓረ መኮንን [ ዐማራና ትግሬ ኦርቶዶክስም ናቸው። የተገደሉ ]
★ ጀነራል ገዛኢ አበራ [ ትግሬም ኦርቶዶክስም  ናቸው።  የተገደሉ። ]
• ይሄ ለኩሽ መንግሥት መስራቾች ትልቅ ድል ነው።
★ ጥያቄ መቀጠላችንን እንቀጥላለን።
★ [ ምእመናን የአስራት ገንዘባችሁን በጊዜ ክፈሉ እንጂ። የባንክ ዕዳ እያፋጨብን እኮ ነው። ቤተ ክርስቲያን ልትዘጋ እኮ ነው። ብለው ወጥረው ሳይታክቱ፣ ሳይዘነጉና ሳይረሱ የሚሰብኩ ጳጳሳት፣ ካህናትና ሰባክያንን አያሳጣን።]  አሜን።
★ እንደተጠበቀው ዐማራና ትግሬ አልተፋጀም። ከዳር ቆመው የሁለቱን ሴማውያን እልቂት ይጠባበቁ የነበሩት ሴረኞችም ለጊዜው ያሰቡት አልተሳካም። ሴረኞቹ ግን ከባለቤቶቹ በላይ ለሟቾቹ ማልቀስ፤ በጄነራል አሳምነው ጽጌ ሞትም ከበሮ በመደለቅ ላይ ናቸው።
• ባላዝንም የሚቆጨኝ ግን ይሄ ሁሉ እየሆነ፣ ሃይማኖቱና ሃገሩ አደጋ ላይ ሆናም እያየ፣ እየተመለከተም በዝምታ የተዋጠው ፣ ደግሞሞ ከባለ ሜንጫዎች ተደርቦ የሚሳደበው ክፍል ነው።
• ጎርፉ ከጉልበታችን ከፍ ብሎ ወገባችን ላይ ደርሷል። አንገታችንን በሜንጫ፣ አፍንጫችንን ደግሞ በጎርፉ ውኃ ዘፍቆ ሲያሰጥመን ያን ጊዜ ልክ ይገባናል። መጽሐፍ እንዲል ያን ጊዜ ልቅሶ ይሆናል። የማይጠቅም ልቅሶ ነው። ያን ጊዜ ጩኸት ይሆናል የማይጠቅም ጩኸት ነው።
•••
ሻሎም !   ሰላም !
ሰኔ 18/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።
Filed in: Amharic