>
11:22 am - Tuesday May 17, 2022

የአማራ ጠላቶች ፍጹማን ናቸዉ:- ነዓምን ዘለቀ እንደ ማሳያ (ሸንቁጥ አየለ)

የአማራ ጠላቶች ፍጹማን ናቸዉ:- ነዓምን ዘለቀ እንደ ማሳያ
ሸንቁጥ አየለ
 
ነዓምን ዘለቀ ዛሬ ባወጣዉ ግለሰባዊ መግለጫዉ ሆኖም የኢዜማ/የብርሃኑ ነጋ/ ድርጅት ግልባጭ በሆነዉ ሀተታዉ ብዙ የአማራ ድርጅቶች መኖራቸዉ እና ጽንፈኛ መሆናቸዉ ለተፈጠረዉ ችግር መነሻ ነዉ::ሀገርም ሊያፈርስ ይችላል ሲል ፍጹማዊ የአማራ ጥላቻዉን ገልጿል::
ለመሆኑ የትኛዉ የአማራ ድርጅት ሰዉ አፈናቀል?የተኛዉ የአማራ ድርጅት ሰዉ ዘቅዝቆ ሰቀለ? የተኛው የአማራ ድርጅት ባንክ ዘረፈ?
አንድ አማራ ክልል ተከሰተ የተባለዉ ክስተት እናንተዉ ኤርትራ ወስዳችሁ ያሰለጠናችኋቸዉ እና ከኤርትራ ስትወጡ ሜዳ ላይ የበተናችኋቸዉ ወጣቶች ናቸዉ ግንቦት ሰባት አመራሮች ላይ ዛቱ የተባለዉ::ይሄንንም በደላቸዉን እራሱ ነዓምን ያለ ድጋፍ በሜዳ የተበተኑ እና የተጎዱ የግንቦት ሰባት የቀድሞ ወታደሮች ሁኔታ ስላሰጋኝ አመራርነቴን ለቅቄአለሁ ሲል አዉጇል::
እና አሁን የትኛዉን የአማራ ድርጅት ነዉ የሚወቅሰዉ?
የአማራ ጠላቶች ፍጹማን ናቸዉ:: ነዓምን ዘለቀ በብዙ ሽህ የአማራን ህዝብ እየጨረሰ ያለዉን አቢይን ሳይከስ ደካማዎቹን እና ምን ሀጢያት ያልሰሩትን የአማራ ድርጅቶች የችግሩ ምንጭ አድርጎ ያብራራል::ኢዜማም በትናንትናዉ መግለጫዉ ያድረገዉ ይሄንኑ ነዉ::
ነዓምን ዘለቀ ክርስቲያን አንገቱን በገጀራ እረድ እያለ መመሪያ ሰጥቶ በከሚሴ: በሸዋ: በቡራዩ: በጅማ:በአርሲ እና በሀረር አካባቢዎች ክርስትናን እና ቤተክርስቲያን እንዲቃጠል ከሚያዝ ጀዋር ጋር አብሮ እየፈነጨ: ኦሮሚያ የሚባለዉን ሀገር እና ድንበር የማያዉቁ ኢትዮጵያዊ ፓርቲዎች ወደ ኦሮሚያ አይገቡም ብለዉ ከሚያዉጂ የኦህዴድ ካድሬዎች ጋር ቡና እየጠጣ: ኢትዮጵያ የሚለዉ ቃል ከመጽሃፍ ቅዱስ ለማስፋቅ ከሚዳክሩ ኦነጋዉያን ጋር አብሮ ሀገራዊ ግንባር መስርቶ እየሰራ : ኢትዮጵያን ከፈለግን እናፈርሳታለን የሚሉ ጀዋራዉያን ጋር አብሮ እየተሞዳሞደ አሁን በብዙ ሽህ አማራ ሲታረድ የችግሩ ምንጭ የአማራ ፓርቲዎች ናቸዉ ብሎ የቀረዉን የአማራ ወጣት ለማስፈጀት ከኢዜማ ጋር ተመሳሳይ መግለጫ አዉጥተዋል::
አንድ አመት ሳይሆን  ማን ነዉ በአራት ሚሊዮን የሚገመት ኢትዮጵያውያንን ያፈናቀለዉ? ማን ነዉ ኢትዮጵያዉያንን  እየዘረፈ: እየሰለበ: ቤታቸዉን እያፈረሰ ያለዉ? ማን ነዉ ኢትዮጵያዉያንን በመሃል አዲስ አበባ ቤት ልትሰሩ አትችሉም መጤ ናችሁ እያለ ያለዉ? ይሄን ሁሉ ከሚሰሩ ሀይሎች ጋር እየተሞዳሞዳችሁ ምንም ወንጀል ባልሰሩ የአማራ ድርጅቶች ላይ ጣታችሁን ትቀስራላችሁ::
ደግሞ ለሀገር እንደሚያስብ ሰዉ መግለጫቸዉ ማሳለጫ እንዲሆን ሀገር እንዳይፈርስ የሚል ማሳሰቢያ አክለዉበታል::ሀገር እንዳይፈርስ የተደራጀዉን አማራ ሁሉ እያሳደድክ እረደዉ::የችግሩ ምንጭ እሱ ነዉ ማለታቸዉ ነዉ::አሁን ሀገር ቤት ማን ቀራችሁ?
ትናት  ደረጀ ሀብተወልድ የሚባል የነዚሁ ሰዎች አጋር የሆነ ሰዉ  ወንበዴዉ አሳምነዉ ጽጌ ተደመሰሰ ሲል ተሳልቋል::  ደስታዉንም መቆጣጠር አቅቶት ተንፈቅፍቋል::
የአማራ ህዝብ የአማራ መታረድ መቆም አለበት ብሎ በጅምላ የተናገረለትን ደፋር ጀግና  አገኘሁ ብሎ ገና የአሳምነዉ ጽጌን ንግግር አጣጥሞ ሳይጠግበዉ በብርሃን ፍጥነት የአማራ ጠላቶች: የኢትዮጵያዊነት ነቀዞች በጋራ ተረባርበዉ አይኑን አጠፉት::ለዚህ ተጠያቂዉ አቢይ ኢሳያስ እና ከነዚህ ሰዎች ጋር በምክር የተባበሩ ሁሉ ሆነዉ ሳለ ዛሬ የህዝባችን ጠላቶች የሚከሱት ዞረዉ አማራዉን የአማራን ወጣት ነዉ::
የአማራ ጠላቶች ፍጹማን ናቸዉ:: የአማራ ህዝብ ማወቅ ያለብህ እራስህንም ሆነ ታላቂቱን የአባቶችህን ሀገር ኢትዮጵያን ማዳን የምትችለዉ  ከብረት በጠነከረ መርህ  ስትመራ እንዲሁም በመራራ የድርጊት መርሃ ግብር ስትመራ ብቻ ይሆናል::
የአማራ ጠላቶች እጅግ ፍጹማን ናቸዉ:: በሽህ ህዝብ እየተጨፈጨፈበት እንኳን የሚከሰሰዉ አሁንም አማራዉ ነዉ::
Filed in: Amharic