የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባላቶቹ እየታሰሩ መሆኑን አስታወቀ!!! ( ኢትዮ 360 )

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባላቶቹ እየታሰሩ መሆኑን አስታወቀ!!!
( ኢትዮ 360 )
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) 56 አባላቶቹ በፖሊስ ተይዘው መታሰራቸውን ለአለም አቀፉ የዜና አውታር ሮይተርስ አስታወቀ።
የንቅናቄው ቃል አቀባይ ለሮይተርስ እንደገለጸው አባላቱ በአዲስ አበባ ከተማ በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለፈው ቅዳሜ በባህርዳር በተፈጸመው ጥቃት እጃችሁ አለበት በሚል ነው።
በሌሎች በአራት የኦሮሚያ ክልል ከተሞችም ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ የአማራ ብሔር ተወላጆች መታሰራቸውን ነው ንቅናቄው ያስታወቀው።
ንቅናቄው በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ አባላትን ማሰባሰቡና ታዋቂ እየሆነ መምጣቱ ለውጡን ያበላሻል በሚል በጠቅላይ ሚኒስትሩና በደጋፊዎቻቸው ዘንድ ጣት እንደተቀሰረበት ነው ቃል አቀባዩ ክርስቲያን ታደለ ለሮይተርስ  የገለጸው።
እንደዘገባው ከሆነ በክልሉ የተፈጠረው አለመረጋጋትና ተወላጆቹን እያሳደዱ ማሰር ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ወደ ስልጣን ሲመጣ ተቀባይነትን አትርፎ የነበረው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አስተዳደር ጥያቄ ውስጥ መውደቁንም ነው ዘገባው በጽሁፉ ያሰፈረው።
ለዚህ ማሳያው ደግሞ በሃገሪቱ አብዛኞቹ አካባቢዎች የጸጥታ ሁኔታ አስጊ እየሆነ በመምቱ ነው ሲል ሮይተርስ በጽሁፉ አስፍሯል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.