>
5:13 pm - Tuesday April 20, 8737

ጀነራል አሳምነው ፅጌ ሥርዓተ ቀበር ተፈጸመ!!!  (ዘመድኩን በቀለ)

ጀነራል አሳምነው ፅጌ ሥርዓተ ቀበር ተፈጸመ!!!
     ዘመድኩን በቀለ
የጄኔራል ሳዕረ ሞት የኔም ነዉ
[ ዐማራው የላሊበላ ህዝብ ] 
ዐማራ ማለት ይሄ ነው  ~ ይሄን ይሄን ሳይና ስሰማ ዐማራና ትግሬን የማባላቱ ፕሮጀክት መቼም እንደማይሳካ ስለሚጠቁመኝ ፈጣሪዬን አመሰግነዋለሁ። 
•••
የአካባቢው ሕዝብ ከገጠር መንደሮች ጭምር በነቂስ ወጥቶ የጀነራሉን የቀብር ሥነ ሥርዓት ደማቅ ማድረጉም ተነግሯል።
የጀነራል አሳምነው ጽጌን አስከሬ ከመቀበሩ በፊት አስከሬኑ በትክክል የራሳቸው መሆኑን ለማረጋገጥ በማስፈለጉ የቀብር ሥርዓት አስፈጻሚ ኮሚቴው በቅድሚያ ገና አስከሬኑ ሽምሽሃ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርስ ሳጥኑን ከፍተው ማረጋገጣቸውም ተነግሯል።
በሽለላና በፉከራ ተቀብሎ አስክሪኑን አጅቦ  ላሊበላ ከተማ መነሃርያ ድረስ ማጀቡን የዶቼ ቬለ «DW» ምንጮች ገለፁ።
ከቀብሩ ዋዜማ ጀምሮ ምሽቱን ላሊበላ አቅራብያ ከሚገኙ የገጠር ቀበሌ የመጡ ነዋሪዎችን ጨምሮ የላሊበላ ከተማ ነዋሪ በነቂስ አደባባይ ወጥቶ የሻማ መብራት መረሃ-ግብር ማካሄዱን፣ አብዛኛውም ሕዝብ የጸሎተ ፍትሃቱን መረሀ – ግብሩንም በመከታተልና ወጣቱ ሁሉ በአደባባይ ተሰብስቦ ቆሞ ማደሩን የ«DW» ምንጮቹን ጠቅሶም ዘግቧል።
•••
በጸሎተ ፍትሃት ሥርዓቱ ላይ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ቃለምዕዳንና አባታዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተዋል።
• የአካባቢው የመንግሥት ተጠሪዎች በሥርዓተ ቀብሩና ጸሎቱ ላይ ንግግር ባያደርጉም ከለቀስተኛዉ ጋር ከኅብረተሰቡ ጋር በጋራ መሆናቸም ታዉቋል ብሏል DW ።
•••
ከሁሉም አስደናቂው ነገር ግን ለጀነራል አሳምነው ቀብር አደባባይ የወጣው ህዝብ በግድያው የሞቱትን የማቾችን ሁሉ ፎቶ በባነር አስርቶ፤
የብርጋዴር ጀነራል አሳምነዉ ፅጌ ሞት የኔም ነዉ፤ 
 
• የዶክተር አምባቸዉ ሞት የኔም ነዉ!
 
• የጄኔራል ሳዕረ ሞት የኔም ነዉ ! 
 
•አቶ ምግባሩ ሞት የኔ ነዉ !
እያለ በባህርዳርም በአዲስ አበባም ተገደሉ ብሎ መንግሥት ብቻውን እየገለጿቸው የሚገኙትን ሟቾች ሁሉ ስም እያነሳ ሲያስተጋባ እንደዋለም ነው የተዘገበው።
•••
በየአደባባዩ እንደ ሃገሬው ባህል ለቀስተኛዉ የሟቾችን ስም እየጠቀሰ በፉከራና ሽለላ ብሎም በቅኔ ዘረፋ ሃዘኑን እየገለፀ እንደነበርም ተገልጿል።
•••
መገደላቸዉ ይፋ የሆነው ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ነበሩ።
•••
የሁሉንም ሟቾቹን ነፍስ ይማር። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ደም አፍሳሾች ግን ደማቸው ሳይፈስ አይቀርም። ይኸው ነው።
•••
ሻሎም !  ሰላም ! 
ሰኔ 20/ 2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ዳር።

https://m.youtube.com/watch?v=ZzT4OL0K5xU&feature=share

Filed in: Amharic