>
5:13 pm - Wednesday April 19, 5933

አዴፓ በህዝቡ ለመታመን ከፈለገ •••!?! (ቅዱስ ማህሉ)

አዴፓ በህዝቡ ለመታመን ከፈለገ •••!?!
ቅዱስ ማህሉ
1• አብይ አህመድ ባህርዳር የላከውን ጦር የሚያስዎጣ ከሆነ፣
2• በአብይ አህመድ ትዕዛዝ እንዲያውም ያለ አዴፓ ፍላጎት የታሰሩትን እነ ጀነራል ተፈራ ማሞ እና ኮሎኔል አለበል አማራ ከእስር የሚፈታ ከሆነ፣
3• በመርጦ ለማሪያም የአማራ ወጣት ማህበር አደራጆችን ለመግደል የዘመተውን ገዳይ ቡድን ከአካባቢው የሚስዎጣ ከሆነ (ወንጀለኛ ካለ ህዝቡ ከተረጋጋ በኋላ በራሱ ሃይል መያዝ ይችላል)
4•  የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ልዩ ሃያሎች በመከላከያ ስም እንደ ጋለሞታ ቤት እየፈነጩበት ከሚገኘው የአማራ ክልል በአስቸኳይ የሚያስዎጣ ከሆነ
5• በኦዴፓ ልዩ ሃይል ከክልሉ፣ከአዲስ አበባ እና ከኦሮሚያ የሚታፈኑ አማራዎችን ካስፈታ እና ለነሱ ድምጽ ሆኖ መግለጫ ካወጣ አዴፓ መቀየሩን ከልቤ
እቀበላለሁ። አለዚያ ግን መግለጫው ትርጉም ያለው በስሜት ለሚነዱት ብቻ ይሆናል። አዴፓ ያን ማድረግ ካልቻለ  ለኔ የሚታየኝ ጌታ መቀየሩ ብቻ ነው።
             እንዲያውም በራሱ ቋንቋ ልጠቀምና አዴፓ የሚያውቃትን የድሮ አለቃውን ሕወሃትን የማይድን በሽታ አለባት እንዳለው እሱም እኛ የምናውቀው የማይለቅ የሎሌነት በሽታ እንዳለበት መገንዘብ ይኖርበታል። አዴፓ ከሎሌነት ወጥቶ ሌሎችን ለማስደሰት ሳይሆን ለቆመበት እና ለቆመለት ህዝብ ብቻ መስራት ይኖርበታል። ስለዚህ የታሰሩትን እና እንደ አውሬ እየታደኑ የሚገኙትን የአማራ ልጆች በክልሉ ገብቶ የሚያድነውን መከላከያም ይሆን የኦሮሞ ልዩ ሃይል አሁኑኑ አስወጣልን። መጀመሪያ በተግባር እንተማመን!!!
Filed in: Amharic