>

የኦነጋውያኑ እቅድ ክልል የሆነችውን ሀዋሳ በሪፍረንደም ወደ ኦሮምያ መቀላቀል ነው!!! (አቤል ዘመነ)


የኦነጋውያኑ እቅድ ክልል የሆነችውን ሀዋሳ በሪፍረንደም ወደ ኦሮምያ መቀላቀል ነው!!!
አቤል ዘመነ
 እየወጡ ያሉት መረጃወች እጅግ አስገራሚና አደናጋሪም ናቸው!
“ኤጄቶ 40% የሚሆነው ሌላ ነው በጃዋር የተፈጠረ ጥምር ነው ። እርግጠኛ ሆኘ የምናገረው ነገሩን ታይቱላችሁ ከተማዋን ወደ ምስቅልቅል በመክተት ቶሎ የክልል ጥያቄ ሲመለስ ያቀዱት ሌላ ነገር አለ”
ይህ ንግግር ከአንድ የአዋሳ ዩኒቨርስቲ የሲዳማ ተወላጅ ከወራት በፊት ያሉት ነበር።
ጃዋር በቀጣይ እንዲህ አለ በራሱ የቴሌቭዥን ጣቢያ
” መንግስት ግዴታው ነው አዋሳ ክልል መሆን አለባት የተሰጠውን ጊዜ ተጠቅሞ መልስ መስጠት አለበት ያ ካልሆነ ህዝቡ ክልል መሆኑን በግድም ያውጃል ለዚህም ኢጄቶ እየተዘጋጀ ነው “
ካለ በሁዋላ ” ኤጀቶ ከዛ ቀን በሁዋላ እርምጃ መውሰዱ አይቀርም “
አለ ይህ ንግግር ዛሬም ድረስ አለ እዩት
እናም ዛሬ የሲዳማ ክልል ጥያቄ የመጨረሻው ቀን ነበር በከተማዋ የታየው ነገር ለሲዳማ ህዝብ ለራሱ ግራ ገብቶት አንዳንዱ ቤቱን ዘግቶ ተመልካች ሆኖዋል።
በመልክት አንዱ እንዲህ ሲል ላከ ” እኔ እንደዚህ መሆኑን አላውቅም የክልል ጥያቄ እኛ ሲዳማወች አንስተናል ይህ ይመለስ ዘንድ እንታገላለን ዛሬ ያየሁት ግን ሌላ ነው ። ኢጀቶ መስለው ሌላ አላማ ያላቸውን ነው ያየሁት የህዝቡን ንብረት እያወደሙ ንፁሀንን ሳይቀር እየደበደቡ ውጡ የሚል ከዛም አልፎ በተለይ ከገብሬል ቤተክርስቲያን ጀርባ ገባ ብሎ ያሉት የኦነግን ባንዲራ ለብሰው ነበር የኮብል ስቶን ድንጋይ እያፈረሱ የሰወችን ቤት እየሰበሩ አሁን ቀስ ብሎ እጃችን ይገባል የእኛ ንብረት ነው እያሉ ነበር ከዛም አልፎ ሳያውቁ አብረዋቸው የነበሩ የሲዳማ ኤጀቶወችን በሚሰቀጥጥ ሁኔታ ሲደበድቡ ነበር ። ቀይ መለዮ ለባሾች ሶስት ጊዜ መተው የኦነግ ባንዲራ አርገው ወንጀል የሚሰሩትን ትተው እውነተኛ ሲዳማወችን በኦራል እየጫኑ ነበር ። እኔ እንደዚህ መሆኑን አላወቅኩም ነበር ነገሩ ሌላ ነው ” ሲል ያየውን ገልፁዋል።
በጣም አስገራሚው ነገር ልጁ ያለው ብቻ ሳይሆን ከሀዋሳ የኦነግ ባንዲራን ለብሰው ጎማ በማቃጠል የሰው ቤት በመዘረፍ ያሉትን ፎቶወች እየወጡ ነው።
እንግዲህ የዚህ ማስተሩ ጃዋር ነውና የተናገርናት አንዲትም ሳትቀነስ ሳትጨመር ደርሳለች።
የሲዳማ ህዝብ የጠየቀው ሌጅቲማት ጥያቄ ይበልጥ ውስጡን ማርለውሰው ዋና አላማቸው የሲዳማ ክልል መሆንን ቶሎ ካገኙ በፍጥነት የሲዳማ ክልልን ዲሞግራፊ በመቀየር በሪፍረንደም ወደዛው መጠቅላል ነው ።
ይህንም አለማቀፍ ትልቁ የዜና አውታር ዘጋርዲያን በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገች ያለችው ሀዋሳ ከተማ የስጋት ቀጠና ወደመሆን መሸጋገሩዋ አይቀርም ዲሞግራፊ ለውጥም በፍጥነት አለ ሲል አብራርቶታል።
እኔ ግን ለምን ኦነግስት በዚህ መንገድ መሄድ ፈለገ ? የህዝቡን ንብረት በማውደም ቶሎ ክልል መልስ ከተሰጠ ኦነግ በሲዳማ የህዝብ ለውጥ demographic change በማፍጠን ወደ ራስ የመጠቅለሉ ጉዳይ ከሆነ ለምን የህዝብን ንብረት ማውደም አስፈለገ?
የሌሎችንስ ሀብት ለምን መዝረፍ ማስወጣት አሻ?
ልክ ነው የሌሎችን ቤት እየዘረፉ በፍጥነት ኦነጋውያን ሀዋሳን እየተቆጣጠሩዋት እንደሆነ ያው አለማቀፍ እውነት ሆኖዋል።
ግን የድሆችን ከመዝረፍ ኦነግ የፈለገውን ያህል ህዝብ በሀዋሳ በልቡ ሰርቶ እንዲሰራ ቢያደርግ።
የ15% የህዝብ ቁጥር በሀዋሳ የነበረው የኦሮሞ ኦነጋውያን ቁጥር በ2011 ወደ 28.4% ተሽቀንጥሮ አድጉዋል ።
ይህም ማለት በቀጣይ ሶስት አመታት በሀዋሳ ከተማ የኦነግ አላማ ወደ 67% ይደርሳል ስለዚህ ክልል የሆነችው ሀዋሳ በሪፍረንደም ወደ ኦሮምያ ትጠቃለል የሚለውን መልስ በምርጫ 67% የያዘው ስለሚያሸንፍ ያኔ ወደ ተፈለገው ሀዋሳ ትጠቃለላች።
ምክንያቱም ጃዋር ” አባቶቻችን ናቸው አዋሳን የመሰረቱዋት ከስሞቹ ጀምሮ ኦሮሞወች ናቸው የቆረቆሩዋት ” ሲል በግልፅ ተናግሮዋል።
እኔምለው የሲዳማ ህዝብ ክልል መሆን ጥያቄን ያንሳ ክልልም ይሁን ግን ይህን ከባድ በግልፅ ዛሬ የታየውን ጉዳይ እያየው ይሆን? ብዙ የሲዳማ ሙህራን እኮ የተናገርነው ይደርሳል ስለዚህ እውነቱ ያ ነው ብለው ገለል ብለዋል።
እኔ ግን የነጃዋር ኦነግ አላማ ለማሳካት ያሰቡት እውነት መሆኑ በአመታት ባይቀርም ቢያንስ ምስኪን ለፍቶ አደር ሰርቶ ያገኘውን ንብረት ሳይቀሙ የሚፈልጉትን ቢያሳኩ እላለሀ።
ንፁሀን በዚህ አይነት ሴራ መጎዳት የለባቸውም።
Filed in: Amharic