>
7:07 am - Tuesday December 6, 2022

ቢመራችሁም እውነታው ይህው ነው ተጋቱት!!! (ዘመድኩን በቀለ)

ቢመራችሁም እውነታው ይህው ነው ተጋቱት!!!
ዘመድኩን በቀለ
* ማን ነበር ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አንድ ላይ ይበራሉ ያለው? 
•••
ጠዋት በቤተ መንግሥት እንዲህ ሆነ። የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ጠቅላዩ በነበራቸው ውይይት ማጠቃለያ ላይ አባቶቻችን በጽሑፍ ያቀረቡለትን በቃል ደግመው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ላለው በደል መንግሥታቸው ይቅርታ እንዲጠይቅ ይጠይቁታሉ።
•••
ጠቅላዩም አለ በነገራችን ላይ ይሄ በላይ የሚባለውን ሰውዬ እኔ በግሌ አላውቀውም። ከእኔም ጋር ግኑኝነት የለውም። ( የአንድ ፓርቲ አባሉን እኮ ነው አላውቀውም የሚለው) ቀጠለና ቀሲስ በላይ ሲፈልግ ጴንጤ፣ ሲፈልግ እስላም መሆን ይችላል። ኦርቶዶክስ ነኝ እያለ ግን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆኖ ጅማ ማርያምን መገንጠል አይችልም። ወዘተ አለና ቀጠለ።
•••
ያቀረባችሁልኝ ጽሑፍ የክሥ ነው። “ እኔኑ እየከሰሳችሁኝ ነው። እኔ ካህናትንና ምእመናን አልገደልኩም፤ቤተ ክርስቲያንን አላቃጠልኩም፤ አዝናለኹ፤ ሳላጠፋና ሳልበድል እንዴት ይቅርታ ጠይቅ፤ ወርቅ ላበደረ ጠጠር እባላለኹ፤ ይቅርታ አልጠይቅም፤ ካሳም አልከፍልም፤” በማለት የአባቶችን ወሽጥ ከቆረጠ በኋላ ጥያቄው የመተጋገዝ ከኾነ ግን  እንደሚቀበሉትና እንደሚረዱም እያላገጠ ነግሯቸዋል ተብሏል። ወደፊት ግን ቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ጥበቃ ማድረጉ ላይ እነበረታለን። እናም መንግሥቴ ይቅርታ አይጠይቅም። አራት ነጥብ ብሎ መራራውን ኮሶ የ42 ዓመቱ ጎረምሳው ጠቅላይ ሚንስትሬ እነዚያ ለሰማይ ለምድር የከበዱ አረጋውያን አባቶችን አስቀምጦ እየመረራቸውም ቢሆን አፋቸውን በግድ ፈልቅቆ ግቷቸዋል።
•••
እኔም እጅግ በጣም ደስስስ ነው ያለኝ። አንጀቴ ነው ቅቤ የጠጣው። አቢቹን ከልቤ ነው  ያመሰገንኩት። ከልቤም ነው የመረቅኩት። እንኳንም እውነቱን፣ ትክክለኛውን መገለጫ አቋሙን በ11ኛው ሰዓትም ቢሆን ገለጠላቸው ብዬ ነው መደሰቴ። ትንሽ ደግሞ አስኬማቸውን አስወልቆ፣ መስቀላቸውን ቀምቶ ትንሽ #ፑሻፕ ቢያሠራቸው እጅግ መልካም ነበር። አቦ ደግ አደረክ ያ ሌንጨ ኮ። በጊዜ እንኳንም አወቁህ። ገለቶሚ። አሁን ቁርጡ ሲታወቅ የግድ ወደ አንድ አቋም ይመጧታል።
ከሰዓት በኋላም በቤተ ክህነት እንዲህ ሆነ፦
•••
የኦቦ ሜንጫ ጃዋር አድራሽ ፈረሱ ቀውስ በላይ መኮንን በአስቸኳይ ወደ ቤተ ክህነት እንዲመጣ ከሲኖዶሱ ይነገረዋል። ቀወሴም “ ጠዋት ሄጄ አጥቻቸዋለሁ እና አልመጣም ይላቸዋል። መልካም ተብሎ ለአለቆቹ ተነግሮ ቢነገረውም ያንኑ ቃል ደገመ። ኋላ ማን ምን እንዳለው አይታወቅም ቀውሲ በላይ መኮንን 6 ጀሌዎቹን አስከትሎ ቤተ ክህነት ደረሰ። ጉባኤውም ተጀመረ። ጥያቄዎች በዝርዝር ቀረቡለት። እሱም እንዲህ አለ። “ እኔ እዚህ ነገር ውስጥ የገባሁት በየአህጉረ  ስብከቱ ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት ምንም ስላልሠሩ ነውም። እናም ወይ ፍንክች አላቆምም አለ።
•••
እንዲያውም አለ ፤ እንዲያውም አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ። ሁሉም የኦሮሞ ህዝም ድሮ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነበር የሚጠቀመው። ከዚያ የኦሮሚያ ባንክ ሲከፈት ኦሮሞው በሙሉ ግልብጥ ብሎ ወደ ኦሮሚያ ባንክ ገንዘቡን አስገባ። ባንኪ ኬኛ ብሎ እኮ ነው። አሁንም የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ቢከፈት ወደ ጴንጤ፣ ወደ መናፍቅነት የሄዱት በሙሉ ግልብጥ ብለው ይመጣሉ። ኦርቶዶክሲን ኬኛ ብለውም ይመለሳሉ። ብሎት አረፈው።
•••
እኔ እኮ ድሮም ተናግሬአለሁ። ፀቡ ኢትዮጵያ ከሚለው ስም ጋር ነው ስንል ሰሚ አጥተን የነበርን ሰዎችንም ዛሬ ገላገሉን። አገኘንህ።  እንኳንም ደህና መጣህ አልነው። በነገራችን ላይ የኦሮሞ ጽንፈኞቹ የጃዋሩ OMN ሰሞኑን አንዲት ነፍስ ነገር የሆነች መረጃ ለጥፎ ነበር። መረጃዋ እንዲህ የምትል ናት። የተጻፈችው በቁቤ ቋንቋ ነው። “ የኦሮሚኛ ቋንቋ በአፍሪካ በሙሉ የሚነገር ቋንቋ ነው። በዙ ኦርቶዶክሳውያን የኦሮሞ ልጆች በቋንቋቸው ማምለክ አልቻሉም። ስለዚህ ለኦሮሞ ልጆች ሲባል የግድ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት በአስቸኳይ መቋቋም አለበት። ይሄ ነገር ከተሳካ ኦሮምኛን የፌደራል ቋንቋ ለማድረግ የሚደረገውን ትግል በቶሎ ያቀላጥፈዋል። ብሎ ነው የደመደመው። ስለዚህ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ምስረታ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም አሽቀንጥሮ ለመጣል ነው። ይኸው ነው ትግሉ።
•••
እነሱ እየሠሩ ያሉት ከኦሮሚያ ምድር ዐማራንና አማርኛ ቋንቋን፣ ኢትዮጵያ የሚለውን ስምና የኢትዮጵያን ባንዲራ ለማጥፋት ነው። አከተ። ሌላው ቦለጢቃ ትርፍ ነው። ከዚያ የሸዋ ዐማራውን ብቻውን አግኝተው እሬቻውን ሊያበሉት ነው ፍላጎታቸው።
•••
ዶር ብርሃኑ ነው ማንትስዬ ነኝ ያለ ሰው ደግሞ መናገር ጀመረ። እንዲህም አለ። “ እኛ ኦሮማራ ብለን ጀምረን ነበር። እሱም አልተሳካም። ከኢትዮጵያ አንድነት ኃይሎች ጋርም ሞከርን እሱም አልተሳካም። አሁን የቀረን ነገር የለም። ሁሉንም ትተን ኦሮሙማን ማጠንከሩን መርጠናል። በቃ ይኸው ነው። እርማችሁን ብሉ ብሏቸው አረፈው።
•••
በመጨረሻም ሲኖዶሱ እነ ቀሲስ በላይን ይቅርታ ትጠይቃላችሁ ወይስ አትጠይቁም አላቸው? አንጠይቅም አሉ ኮምጨጭ ብለው። ለምን ሲባል ሚልዮኖች ከኋላችን ስላሉ አንጠይቅም አሉ። እሺ ብለው ወደ ውሳኔ ሊገቡ ሲሉ። አረጋዊው ሊቀጳጳስ ቀድሞ የዚህ ነገር ደጋፊ እንደነበሩ የሚነገርላቸው በትውልድ ኦሮሞ የሆኑት አቡነ ዮሴፍ ጣልቃ ገብተው እንዲህ አሉ።
•••
“ የለም የለም ቆይ አንቸኩል። እኛ ለህዝቡ ጋዜጣዊ መግለጫ የምንሰጠው ጠዋት 3 ሰዓትም አይደል? ግድየለም ልጆቹም የማሰቢያ የማሰላሰለያ ጊዜም እንስጣቸው። እኛ ጠዋት 2 ሰዓት ቀደም ብለን እንሰብሰብ። እናንተም አስባችሁበት አድራችሁ ኑ። እስከ 3 ሰዓት ከላደረሳችሁ። እኛም በእናንተ ላይ ውሳኔአችንን ወስነን እንለያያለን። ይኸው ነው አበቃ አሉ። ጉባኤውም በዚሁ ተጠናቀቀ።
•••
አዲሱ አረጋ ስለ አኖሌ ሃውልት የውሸት ትርክት  ነው ብሎ አምቦ ላይ ተናገረ። ኢትዮጵያውያን ጮቤ ረገጡ። ጃዋር ጆሮውን ጠምዝዞ ይቅርታ አስጠየቀው።
•••
አቶ ሽመልስ አዱኛ ትናንት በሲኖዶሱ ላይ ተገኝቶ ለሲኖዶሱ የኦሮሚያ ቤተ ክህነት የሚባል የለም ብሎ ተናገረ፣ ኢትዮጵያውያን ጮቤ ረገጡ። ጃዋርም ጆሮውን ጠምዝዞ ይቅርታ አስጠየቀው።
•••
ዛሬ ደግሞ ጠዋት ላይ ጠቅላዩ ይቅርታ አልጠይቅም አለ። ከሰዓት ላይ የፓርቲ ጓደኛው ቀውሲ በላይ መኮንን እንደ አለቃው ይቅርታ አልጠይቅም አለ።
••
ከሰዓት ላይ ታከለ ኡማ ከአቡነ መልከጸዴቅ ጋር ተሞዳምዶ በሚልየን የሚቆጠር ብር ከቤተ ክርስቲያኒቱ ካዝና አውጥቶ ለፕሮቴስታንቱ ታከለ ኡማ አስረከበ። በዚያው ከሰዓት ላይ ደግሞ አቢቹ ለፓስተሩ ለዮናታን 25 ሺ ዩሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ሸለመው። እየሆነ ያለው ይሄው ነው። አከተመ።
•••
አዳሜ እርምህን አውጣ። ደግነቱ አሁን ሁሉም ስለባነነ እኔ ጩኸቴን መቀነስ አምሮኛል። እስከዛሬም እናንተ ባታነቡት እንኳ ሼር አድርጉት እያልኩ የነዘነዝኳችሁ ቀድሞ የሸተተኝ ነገር ስለነበረ ነው። በእርግጠኝነት የምነግራችሁ። በዚሁ ከቀጠለ ነገሩ ሁሉ ይደፈርሳል። ከዚያ የግዱን ይጠራል። የሚታየኝ ይሄው ነው።
•••
የዐማራው ተለቅሞ መታሰር። የትግራይ ከዳር ቆሞ መሳቅ። የኦሮሞ ኦርቶዶክሱ ከሃይማኖቱ ይልቅ ዘሩ በልጦበት ማሽካካት የመሪዎቹ እንደ ፍንዳታ ታላቅ ሀገር ላይ መቀለድ ነገን ሳያጨልመው አይቀርም።
•••
ዘሬ ዝም ያለ ሽማግሌ ነገ ከዘራውን ለማንሳት እንኳ ጊዜ አያገኝም። ዛሬ ምን አገባኝ ያለ ሁላ ነገ ጉድጓድ ከፊቱ ይጠብቀዋል። ግብፅ፣ ሱዳን፣ ሳኡዲ፣ ኳታር፣ ሶማሊያ፣ ኤምሬትስ፣ እንግሊዝና አሜሪካም ካርታ ጨዋታውን አጧጡፈውታል።
•••
በመጨረሻም ግን ዐማራም፣ ኢትዮጵያም፣ ኦርቶዶክስም፣ ያሸንፋሉ። የሚመጡት አራጆች ግን የዐማራን ሙስሊም እንኳ አይምሩትም። ይኸው ነው ቴሌቭዥኑ ላይ የሚታየው።
•••
ኦቦ አቢይ፣ ያ ሌንጨ ኮ ገለቶሚ።
ኦቦ ሽመልስ፣ የፈርደ ኮ ገለቶሚ።
ኦቦ በላይ፣ የቱቀማ ኮ ገለቶሚ።
ኦቦ አባ ሜንጫ ጃዋር አቲስ ገለቶሚ።
ኦፒዲኦ/አባኦ ኢሲን ሁንዱማ ገለቶማ። ከኑማ ጋ ዱቢን። 
•••
ሻሎም !   ሰላም !   
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጳጉሜ 1/2011 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
Filed in: Amharic