>
7:33 pm - Monday May 16, 2022

መስከረም 4 የፈራ ይመለስ!! *በጅማ የተዋህዶ ልጆች ድል አደረጉ! (ቅዱስ ማህሉ)

መስከረም 4 የፈራ ይመለስ!!
ቅዱስ ማህሉ
 * “እኛ ካልፈለግን በክልልላችን አታመልኩም፤ ለኦርቶዶክ ተዋህዶ እውቅና አንሰጥም!!!”  
የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር
* ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ የቅዱስ ሲኖዶስን መግለጫ “የሚዲያ ዛቻ” በማለት አጣጣሉ!!!
 
በጅማ የተዋህዶ ልጆች ድል አደረጉ! በሌሎችም ክልሎች ይቀጥላል!!!
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ትናንት ባደረገው ንግግር ከፈልግን ኦርቶዶክን ተዋህዶ እንዳትንቀሳቀስ  በክልላችን የማገድ መብት አለን የሚል እንድምታ ያለው መግለጫ መስጠቱ ሳያንስ የቅዱስ ሲኖዶስን መግለጫ “የሚዲያ ዛቻ” ብሎ ማጣጣሉ ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ባስተላለፉት መልክት ቅዱስ ሲኖዶስን ደግፈን እንሰለፋለን ለሚሉ ሰዎች እውቅና እንደማይሰጥ እና በክልሉ ሰልፍ ማድረግ እንደማይችሉ ለኢዜአ ተናግረዋል።
እንግዲህ የኦሮሞ ክልል መንግስት በግልጽ ኦርቶዶክስን ለማጥፋት አቋሙ አድርጎ ይዟል። የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞችንም ለሃይማኖቱ የበላይ መሪዎች እና ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ሳይሆን በኛ መንገድ ካልተጓዛችሁ ኦርቶዶክስን ከክልሉ እናግዳለን ወደ ማለት እየመጡ ነው። ይህን የሚያስጠንቅቁት የፖሊስ ኮሚሽነሩ አብያተ ክርስቲያናት እና ካህናት እንደ ችቦ ሲነዱ በዝምታ ያዩት እና ወንጀለኞችን ለማቅረብ ዳተኛ የሆኑት ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያንቷን ለማጥፋት ከጥፋት ሃይሎች ተባባሪ ሆነው የሚሰሩት ዋነኛው ባለስልጣን ናቸው። በጅማ የተዋህዶ ልጆች ሲታረዱ እና ሴቶች እየተደፈሩ ሃይማኖታቸውን በግድ እንዲለውጡ ሲደረግ የፖሊስ ኮሚሽነሩ ይህን የጥፋት ውጥን አልጋ ባልጋ እንዲሆን ሲያመቻቹ የነበሩ የኦሮሞ አክራሪ ብሄርተኞች ቀኝ እጅ ናቸው። ሕግና ስርዓትን ማስከበር ያልቻሉት የኦሮሞ ክልል ፕሬዝዳንት እና የፖሊስ ኮሚሽነሩ በአጭሩ “እኛ ካልፈለግን በክልልላችን አታመልኩም፤ለኦርቶዶክ ተዋህዶ እውቅና አንሰጥም።”  እያሉ ባለበት በዚህ ወቅት የጅማ ህዝብ አኩሪ ተጋድሎም ሳይውል ሳያድር ተስተውሏል፤ በአዲስ ርእስ ልመለስበት።
በጅማ የተዋህዶ ልጆች ድል አደረጉ! በሌሎችም ክልሎች ይቀጥላል!!!
 
ለመስከረም 4 ቀን የተጠራውን ሃይማኖቴን አትንኩ ሰልፍ ዋና  አስተባባሪ የሆነውን አቶ ቤትም ማሞ ፖሊስ አፍኖ እንደወሰደው በተሰማ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የጅማ ከተማ ህዝብ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ “እዚያው በለመዳችሁበት፤ይሄ ሃይማኖት ነው። ወደ ኋላ አናፈገፍግም።” በማለት እስር ቤቱን ከቦ ተቀመጠ። ፖሊስ ትጥቁን ይዞ ወዲያ ወዲህ ቢል የሚፈራው ቀርቶ ትኩረት የሰጠውም አላገኘም። ህዝቡ ይህ ሃይማኖታዊ ጉዳይ እንደሆነና በዚህ ጉዳይ ለመሸሽ ሳይሆን መስዕዋት ለመሆን እንደመጡ እንዲያውቁላቸው እርግጡን ነገራቸው። በመጨረሻም የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሲፎክርባት ያመሽው ቤተክርስቲያን እና የተዋህዶ ልጆች የታሰረባቸውን ሰው ከእስር ነጻ አውጥተው የመስከረም አራቱን ሰልፍ ዝግጅት በሰፊው እያደረጉ ነው። ይህ የሆነው ዛሬ ነው። የመስከረም 4ቱ ሰልፍ በመላው ኢትዮጵያ ይደረጋል። በኦሮሚያም በናዝሬት፣ በሐረር፣ በድሬዳዋ፣ በጅማ፣በአሰላ  ሰልፉ በከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገበት ነው። መስከረም 4 በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሰረት በአንድነት እና በሕብረት ለቤተክርስቲያናችን የምንቆምበት የቃልኪዳን ቀናችንም ነው።  ይህ እንዳይሆን የሚያግደን እና የሚያቆመን ምድራዊ ሃይል የለም!!!
እያሉ ነው። ምላሹን ቀኑ ሲደርስ አብረን እናየዋለን!!! መስከርም 4 ለሰማዕትነት ዝግጁ በሆኑ የተዋህዶ ልጆች ሰልፉ በመላው ኢትዮጵያ ይደረጋል። የፈራ ይመለስ!!
Filed in: Amharic