>

ኦህዴድ የተባለ የህወሓት ፈረስ በእነ አቦይ ስብሀት ዳንግላሳ ሲመታ ኖሮ ሁሉንም ጉድ ስራቸው!!! (አየለ መንክር)

ኦህዴድ የተባለ የህወሓት ፈረስ በእነ አቦይ ስብሀት ዳንግላሳ ሲመታ ኖሮ ሁሉንም ጉድ ስራቸው!!!

አየለ መንክር
ኦነግ ለረጅም አመታት በፖለቲካውና በጦር ሜዳ ላይ ታች ሲል ትከሻ ሲመታ ኖረ። ውጤቱ ያገኘው ስኬት ለዜሮ በጣም የቀረበ ነበር።ሲያልቅ አያምር እንዲሉ ወደ መጨረሻውማ በኤርትራ በረሃ ውስጥ ፍየል እያረባና እየነገደ በጣት ከሚቆጠሩ ወታደሮቹ ጋር የመከራ ቀንበር እስከ መግፋት ተገዶ ነበር።
ዛሬ በኦሮሞ የነጻነት እንቅስቃሴ ውስጥ ታላቅ ክብር የተሰጠው አክቲቪስቱ ጃዋር መሐመድ ከኦህዴድ አንጻር ሲለካ ይህ ነው የሚባል ፍሬ ያለው ውጤት አላስመዘገበም። አንዳችም ፍሬ ያለው የትግል ውጤት አላሳዩም ኦህዴድ ቀስ በቀስ በውስጡ ወኔ ማብቀል ጀመረ።የአቶ መለስ መሞት ለለውጡ ከላይ የተሰጠ ታላቅ ስጦታ ነበር።ቀጣዩ ጠ/ሚርም በኦህዴድና በብአዴን ድብቅ ትግል ውስጥ በማር ላይ የታከሉ ወተት ነበሩ።
ትግሉ ከውስጥ ወደ ውጪ ተቀጣጠለ።የኦህዴድ ካድሬዎች ለኦሮሞ ወጣቶች የልብ ልብ እየሰጡ ክብሪት አስይዘው ንብረት ሲያጋዩ፤ ፋኖም ከብአዴን ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ትግሉን ጣሪያ አስነካው!።
ኦህዴድ ከህወሓት ጋር ተመሳጥሮ በሰራቸው ዘመናት ለኦሮሞ ትግል ትልቁ መር ግምት ነበር።ኦነግና መሰል ድርጅቶችን አይቀር ቅጣት ቀጥቷል። በከዳተኝነት ተፈርጆ በጎበና ዳጬ እየተጠራ ብዙ የስሜትና የአካል ጉዳት አስተናግዷል። ብበመጨረሻ ነቃ!ወያኔን አከረባብቶ ወደ መቀሌ ሲሸኛት እሱ የምኒሊክ ቤ/መንግስት ሰተት ብሎ ገባ!።
አብይ አህመድ ስልጣኑን ተረከበ።ምድረ እበላ ባይ ከተሸሸገበት ጎሬ ወጣ!።የኦሮሞ ብሔረተኛ በሐገሪቱ ፈላጭ ቆራጭ መሰለ።ጃዋር ፎለለ!።”ሁለተኛው መንግስት ነኝ!” እስከ ማለት ርቆ ሄደ።ይህ ሁሉ ሲሆን ኦህዴድ በኢህአዴግ እናት ድርጅት ውስጥ እንደ ተወተፈ ነው።ብዙ ጊዜ ስልጣን እስኪነጠቅ ድረስ ነጣቂዎቹ ፍቅር በፍቅር ናቸው።በአንድ አፍ ይናገራሉ!።ሰያነጥስ አንዱ ለሌለኛው ፈጥኖ መሐረብ አቅራቢ ነው።በኦሮሞዎቹ መሃከል የተፈጠረውም ይህን መሰል ነው ነገር ግን ፍቅሩ አልቀጠለም።ስልጣን ያናጫቸው ገባ።በተለይ አብይ አልጣማቸውም።ተቃወሙት።ተቋቋማቸው።በመጨረሻም የኦሮሞ ብሔረተኞች ከህወሓት ጋር በመመሳጠር ሊፈነግሉት ዶለቱ!።
ዳሩ የገጠማቸው ባላጋራ የእራሱ ብዙ ድክመቶች ቢኖሩበትም ስልጣኑን ለመጠበቅ እንደ ቆቅ ንቁና እንደ አቦ ሸማኔ ፈጣን ነበር።”ለምሳ ያሰቡንን ለቁርስ አደረግናቸው!”ህወሓትና የኦሮሞ ብሓረተኞች በድምጽ ብልጫ ከስልጣን ሊፈነግሉት እንደ መስሪያ ሊጠቀሙበት የተዘጋጁበትን ኢህአዴግ በአንድ ምሽት አፈራርሶ ከአዲስ። ፓርቲ ጋር ብቅ አለ!።
ዛሬ ብሔርተኞቹ ቅስማቸው ተሰብሯል።ከብዙ አንጻር እያደፈጡ የተሰገሰጉበት ኦህዴድ የለም።አብይ ከእዚህ በኃላ ጣቱን እየቀሰረ የሚያስፈራራው ብሔረተኛ አይኖርም!።የጃዋር ባዶ ጉራና ለሽብር ያደራጀው ቄሮ በአብይ ላይ ስልጣን የለውም።አሁን ባለንበት ሁኔታ ብቸኛው ንጉስ  እናቱ ከረጅም ጊዜ በፊት 7ኛው ንጉስ ትሆናለህ ብላ የተነበየችለት አብይና አብይ ብቻ ነው!።
Filed in: Amharic