>

የበረከት ሰምዖን ፍጡራንንና የፋሽስት ወያኔ የእንግዴ ልጆች...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

የበረከት ሰምዖን ፍጡራንንና የፋሽስት ወያኔ የእንግዴ ልጆች…!!!

አቻምየለህ ታምሩ

ከሰሞኑ  በአንድ አካባቢ ተወላጅነት ወስኖ የማበላለጡ ሽርጉዱ እንደገና ያገረሸበት ይመስላል። እነዚህ ዛሬ በተወለዱበት  አካባቢ እየተወሰኑ ጥብቅና ሲቆምላቸው የምናያቸው የብአዴን ግብረ በላዎች [በሕይወት የሌሉትም ይሁኑ በቁም የሞቱት] የፈጠራቸውን የበረከት ሰምዖን አማራን የማጥፋት አላማና  ግብረ በላ ያደረጋቸውን የፋሽስት ወያኔን አማራን የማጥፋት ፕሮግራም ከሁሉ በፊት ሲያስፈጽሙ የኖሩት ዛሬ እየተወሰኑበት ባለው አካባቢ ሕዝብ ላይ ነው።

የብአዴን ኮልኮሌዎችን በአንድ አካባቢ ተወላጅነት ወስነው በድጋፍና ተቃውሞ ሲራኮቱ የምናያቸው እነዚህ ጭፍሮች የአማራ ሕዝብ አላማ ስለሌላቸው ውግንናቸው በነዚህ የሕዝብ ጠላቶች ሲገደል ለኖረው የየአካባቢው ሕዝባችን ሳይሆን  የበረከት ሰምዖን ፍጡራንና የፋሽስት ወያኔ እንደራሴዎች ሆነው የየአካባቢያቸውን ሕዝብ ሲደግሉት ለኖሩትና ታሪክ ይቅር ለማይላቸው የብአዴን እስኳዶች ሆኗል።

ሰማዩንም ምድሩንም «የኛ ነው» የሚል እጅግ ነውረኛ የሆነ የአፓርታይድ አገዛዝ በሕዝባችን ላይ ተጭኖ፣ የሕዝባችን የኅልውና አደጋ ከመቼውም በላይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሶ፣ ሰብዓዊ መብቱ ተገፎ፣ ሐሳቡን እንዳይገልጽ ታፍኖና ተለጉሞ፤ የኩራት በርኖሱ ተቀዶ፣ በየሄደበት እየታገተና  የአፓርታይድ አገዛዙ ባበጀለት የቁም መቃብር  ውስጥ እየተሰቃየ ባለበት በዚህ ወቅት የአፓርታይዱ አገዛዙ ግብረበላ የሆኑትን የብአዴን ኮልኮሌዎች በአንድ አካባቢ ተወላጅነት ወስኖ ለነሱ ጭፍራ መሆንም ሆነ በነሱ ላይ መዝመት ንጹህ አህይነትና በሕዝብ ሕይወትና ኑሮ ላይ ማላገጥ ነው። እነዚህ የብአዴን ነውረኞችን በአንድ አካባቢ ተወላጅነት ወስነው ሲያወድሱና ሲያወግዙ የሚውሉ የተንኮል ውርስ የተጠናወታቸው ጭፍሮች የአማራ ሕዝብ አላማ የሌላቸው ከንቱዎችና   ከዋነኞቹ ነውረኛ ብአዴኖች ባልተናነሰ  የፋሽስት ወያኔና  የናዚ ኦነግ አህዮች ናቸው።

Filed in: Amharic