>

የወንድሞቻችንን ነፍስ የቀጠፈውን ወንጀለኛ እናስተዋውቃችሁ! (መምህር ምህረተአብ አሰፋ)

የወንድሞቻችንን ነፍስ የቀጠፈውን ወንጀለኛ እናስተዋውቃችሁ!

 

 

መምህር ምህረተአብ አሰፋ
አቶ ጥላሁን ፍቃዱ የቦሌ ክ/ከተማ ስራ አስኪያጅ ሲሆን የሌላ ሀይማኖት ተከታይ በመሆናቸው ብቻ ለኦርቶዶክስ ከፍተኛ ጥላቻና ንቀት ያላቸው ሰው እደሆኑ በሰፊው ይነገራል:: አሁንም በተደጋጋሚ በማን አለብኝነት ግድያውን ያዘዙት እሳቸው መሆናቸውን ይናገራሉ የተገደሉትም ሁለት ወጣቶች ላይ ግድያው ሳይበቃው የሀሰት ክስ በመፈብረክ “የፖሊስ መኪና በማቃጠላቸው ምክንያት” ነው የተገደሉት በማለት የሟች ቤተሰብን ሀዘን አክብዶታል። 
በአሁን ሰአት የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ በመሆን የታከለ ኡማን ትእዛዝ የሚያስፈጽም ሲሆን ለኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን እና ለአማራ ህዝብ ያለው ጥላቻ በቃላት መግለጽ እንደሚከብድ የቢሮው ሰራተኞች ይናገራሉ።
በትላንትናው እለት ኦሮምኛ ተናጋሪ ወታደሮችን ወደ ቦሌ ልኮ ቤተክርስትያን ያስፈረሰ፣ ሁለት ንጹሃንን መስዋእት ያደረገ እና 17 ንጹሃን ደግሞ ቁስለኛ ያደረገ ሰው ነው። ታከለ ኡማ ቤተክርስትያኑ እንዲፈርስ ለዚህ ሰው ትእዛዝ ሰጠ፣ ይህ ሰው ደግሞ አስፈጸመ።
ስለጉዳዩ የተጠየቀው ይህ ወንጀለኛ ሲመልስ እንዲህ አለ :-
”ቤተ ክርስቲያን እንዲሰራ የታሰበው ቦታ ለአረንጓዴ ስፍራ የተተወ ነው ይላል። አክሎም “ይህ ሆን ተብሎ ፅላት እንኳን ሳይገባ የተደረገ መሬት የመያዝ ስራ ነው። እነዚህ በቅርቡ በተደጋጋሚ እየታዩ ያሉ ድራማዎች ናቸው” ብለዋል።
“ጉዳዩን ወረዳውም፣ ፖሊስም ከካህናት ጋር ሲወያይ ነበር። ነገር ግን እናነሳለን ብለው እድሜ ከማራዘም ውጪ ምንም አላደረጉም። ከሌላ ቦታ የመጡ ወጣቶች ነገሩን ተባብሷል።  ከዛም የከተማው ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ ህግ እንዲያስከብሩ ተደርጓል። በዚህ ወቅት የፖሊስ መኪና አቃጥለዋል።”
“ለምን ቦታው ላይ የእምነት ተቋም መሰራት አይችልም?” ለሚለው ጥያቄዬ ሰውየው ሲመልስ “እዛው ጋር ቤተ ክርስቲያን አለ። ህጉም አይፈቅድም፣ ተገቢው ቦታም አይደለም” ብለዋል።
“ለምን እርምጃው ለሊት ላይ ተደረገ?” ተብሎ ለተጠየቅው ሲመልስ ደግሞ “እንደዚህ አይነት ስራዎች ብዙ ግዜ የሚሰሩት ማታ ላይ ነው። ቀን ላይ ከሆነ ቀውሱ ይበዛል። ከዚህ በፊት ሁለት ግዜ ቀን ላይ ተሞክሯል፣ አልሆነም። ሌላ ተአምር የለውም” ብሏል።
Filed in: Amharic