>

የሥውሩ መንግሥት ልሣን !! (ሙሉዓለም ገ/መድህን)

የሥውሩ መንግሥት ልሣን !!

ሙሉዓለም ገ/መድህን
•OMN ላይ እርምጃ መውሰድ ሀገርን ከእርስ በርስ ጦርነት የመታደግ ሚና ነው! መንግሥት እርምጃ ባይወስድ እንኳ ጦርነት እየተቀሰቀሰባቸው ያሉ ግፉዓን ተደራጅተው ጣቢያው ላይ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል። ከክስ ያለፈ እርምጃ ያስፈልጋል። 
ከስር የተያያዘው ዜና የ OMN ነው። ‘ሥውሩ መንግሥት’ በኦርቶዶክሳውያኑ ላይ የፈፀመውን ወንጀል ለመሸፈን ሲባል በአማርኛ ቋንቋ የተሰራ ዜና ነው። ጣቢያው የአማርኛ ቋንቋ ፕሮግራሞች ቢኖሩትም በ ‘New Media’ ደረጃ ዜና የሰራባቸው ጊዜያት ውስን ናቸው።
ዛሬ ይህን ዜና በማህበራዊ ሚዲያ ሲያሰራጭ ዋና ዓላማው የሥውር መንግሥቱን ወንጀል ለመሸሸግ ነው።
ጣቢያው የኢትዮጵያ ቀን አቆጣጠርን አይጠቀምም። ካሌንደሩ የምዕራባዊያን ሲሆን ዋነኛ ተልዕኮው የኢትዮጵያ ፍሬ ነገር የሆኑትን ምልክቶች መናድ ነው። ለነ ጃዋር የኢትዮጵያ ቀን አቆጣጠር የአማራ ነው የኦሮሞ ቀን አቆጣጠር የምዕራባውያኑ እንዲሆን መርጠዋል። እንግዲህ የዚህ ጣቢያ ባለቤቶች ሥልጣን ላይ ቢወጡ ምን እንደሚያደርጉ አስቡት።
በሚቀጥሉት ጊዜያት ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲጀመር ለተፈለገው ጦርነት ዋነኛ ማቀጣጠያ ሆኖ እያገለገለ ያለው OMN በሕግ የማይጠየቅ ከሆነ ÷ የጦርነት ቅስቀሳ የተከፈተባቸው ኢትዮጵያውያን በዚህ ጣቢያ ላይ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል። ይህ ጣቢያ እንደ ብሔር በአማራ እንደ ሃይማኖት ደግሞ በጥቅሉ ክርስቲያኖች ላይ ዘመቻ ከፍቷል።
ጦርነት የተከፈተባቸው ማህበራዊ ኀይሎች እየመጣ ያለውን አደጋ አስተውለው በጋራ ሊቆሙ ይገባል።
መንግሥት ሚናውን በዘነጋ ቁጥር ÷ ዜጎች ራሳቸውን በማደራጀት ሕግና ፍርድን በእጃቸው ለመጨበጥ ይገደዳሉ።
በዛሬዋ ኢትዮጵያ ሥልጣን መንግሥት የመሆን አንገብጋቢና ቀዳሚ ጥያቄ ሆኖ ቀርቧል! ይህ ሳይሆን ሲቀር አደጋ ውስጥ የገቡ ዜጎች ራሳቸውን ለመከላከል ይገደዳሉ።
OMN ላይ እርምጃ መውሰድ ሀገርን ከእርስ በርስ ጦርነት የመታደግ ሚና ነው! መንግሥት እርምጃ ባይወስድ እንኳ ጦርነት እየተቀሰቀሰባቸው ያሉ ግፉዓን ተደራጅተው ጣቢያው ላይ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል። ከክስ ያለፈ እርምጃ ያስፈልጋል።(
Filed in: Amharic