>
5:13 pm - Thursday April 20, 5595

የማንቂያ ደወል!!! (ካሳሁን ደባልቄ)

የማንቂያ ደወል!!!

ካሳሁን ደባልቄ

*:በኢንተርሃምዌ አምሳል በኦሮሞ ፋሺስቶች የተደራጀው ቄሮ እና ተባባሪ የጥፋት ሃይላት እየፈፀሙ ያሉት ተግባር ልክ ኢንተርሃምዌ ከዋናው ጄኖሳይድ በፊት ከሚፈፅማቸው የሙከራ ተግባራት ጋር አንዳይነት ስለሆኑ ነው። የቄሮ የጥፋት ሃይል በአክራሪ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ከመደራጀቱ በተጨማሪ በዓቢይ አሕመድ መንግስት ውስጥ ባሉ የኦሮሞ ባለስልጣኖች እና የጦር መኮንኖች የስልጠና እና የትጥቅ አቅርቦት እየተደረገለት እንደሆነ በቂ ማስረጃዎች አሉን….

—-

በ1994 እ.ኤ.አ. የርዋንዳ ጄኖሳይድ በተካሄደበት ወቅት Interhamwe ኢንተርሃምዌ የሚባል የቄሮ አምሳያ የሁቱ ወጣቶች አደረጃጀት ነበር። ኢንተርሃምዌ በሁቱ አክራሪዎች ተቋቋሞ ሲንቀሳቀስ የትጥቅ እና የስልጠና ድጋፍ ያገኝ የነበረው በወቅቱ በሁቱዎች ይመራ በነበረው የርዋንዳ መንግስት ባለስልጣናት ነበር። በተለይ ኮሎኔል ቴዎኔስት ባጋሶራ የሚባሉት አክራሪ ሁቱ የጦር መኮንን በርዋንዳ መንግስት በነበራቸው ከፍተኛ ስልጣን እና ተሰሚነት በመጠቀም ይህ የወጣቶች ቡድን የተሟላ ትትቅ እና ስልጠና እንዲያገኝ አድርገዋል።

በማርች 1994 በመላዋ ርዋንዳ ሰፈሮች እና ኮረብቶች የኢንተርሃምዌ አደረጃጀት ተስፋፍቶ ከፍተኛ አቅም ያገኘ ሲሆን በርዋንዳ መንግስት እና ፓርላማ ውስጥ የነበሩ የሁቱ አክራሪዎች በስውር አሰራር የመንግስትን ተቋማት ሙሉለሙሉ ወደ መቆጣጠር ደርሰው ነበር።

ኢንተርሃምዌ ቱትሲዎችን ከምድረገፅ ለማጥፋት በነበረው ዕቅድ መሰረት ወደዋናው ተግባር ከመግባቱ በፊት በተለያዩ እንቅስቃሴዎች አቅሙን የመለካት እና የቱትሲዎችን የመከላከል ብቃት የመፈተሽ ስራ ሰርቷል። በተጨማሪም በጊዜው በርዋንዳ ተሰማርቶ የነበረው የተባበሩት መንግስታት ሰለም አስከባሪ ሃይል ቱትሲዎችን ከጥቃት ለመከላከል የነበረውን አቅምም እንዲሁ ይፈትሽ ነበር። ወደዋናው ጭፍጨፋ የገባውም በእነዚህ ፍተሻዎች አማካይነት ሁኔታውን ካጣራ በኋላ ነበር።

በጊዜው በርዋንዳ የተመድ ሰላም አስከባሪ ሃይሉ አዛዥ የነበሩት ጄኔራል ሮሜዎ ደሌር shaking Hands With the Devil በሚል መፅሃፋቸው ይህንን ሁኔታ በዝርዝር ይገልፁታል። በወቅቱ በቂ በተመድ ሃላፊዎች በቂ ድጋፍ ሳይደረግላቸው በመቅረቱ የቱትሲዎችን ዕልቂት ማስቀረት ባለመቻላቸው ባዩት አሰቃቂ ነገር አዕምሯቸውን እስከመታመም ደርሰው ነበር።

ይህንን ያነሳሁት ያለምክንያት አይደለም። በኢንተርሃምዌ አምሳል በኦሮሞ ፋሺስቶች የተደራጀው ቄሮ እና ተባባሪ የጥፋት ሃይላት እየፈፀሙ ያሉት ተግባር ልክ ኢንተርሃምዌ ከዋናው ጄኖሳይድ በፊት ከሚፈፅማቸው የሙከራ ተግባራት ጋር አንዳይነት ስለሆኑ ነው። የቄሮ የጥፋት ሃይል በአክራሪ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ከመደራጀቱ በተጨማሪ በዓቢይ አሕመድ መንግስት ውስጥ ባሉ የኦሮሞ ባለስልጣኖች እና የጦር መኮንኖች የስልጠና እና የትጥቅ አቅርቦት እየተደረገለት እንደሆነ በቂ ማስረጃዎች አሉን። በኦሕዴድ ባሁኑ ብልፅግና ፓርቲ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች በያዙት የፌዴራል እና የክልል መንግስት ስልጣን ተጠቅመው ይህ የቄሮ የጥፋት ሃይል ከገጀራ ጀምሮ የተለያዩ የነፍስ ወከፍ መሳርያዎች እንዲታጠቅ አድርገዋል፥ የማስታጠቁም ሂደት ከሞላ ጎደል ተጠናቋል።

በመከላከያ ሰራዊት እና በፌዴራል ፖሊስ ውስጥ ያሉ የኦሮሞ ፋሺስቶችም ይህንን የቄሮ የጥፋት ሃይል የማሰልጠኑን ስራ ረዥም ጊዜ ወስደው ሲያከናውኑ ቆይተዋል። በተለይ በሐረርጌ እና አርሲ በመንግስት ማሰልጠኛ ካምፖች ገብተው የሰለጠኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ቄሮዎች እንዳሉ ማስረጃዎች ያረጋግጣሉ። የዓቢይ አሕመድ መንግስት ባለስልጣናት በተለይ ለማ መገርሳ እና ደመላሽ ገብረሚካዔል ይህንን የቄሮ ትጥቅና ስልጠና ጉዳይ በትኩረት እየሰሩበት ይገኛሉ። ከዚህ ባሻገር የአማራ ሕዝብ ምንም ዓይነት የመከላከል አቅም እንዳይኖረው ታስቦ በዓቢይ አሕመድ ጠንሳሽነት ጄኔራል አሳምነው ፅጌን የመሰለ የአማራ መከታ እንድናጣ እና በዳዴ እየተነሳ የነበረው የክልሉ ወታደራዊ ሃይል ሙሉ ለሙሉ እንዲሽመደመድ የተደረገውም በዚሁ የኦሮሞ የጥፋት ሃይል ዕቅድ መሰረት ነው።

በዚህ ሁኔታ በተሟላ ትጥቅ እና ስልጠና የተደራጀው የኦሮሞ የጥፋት ሃይል  የጥምቀት ሰሞኑን ሁከት፥ የአዲስ አበባውን የክርስቲያኖች ጭፍጨፋ፥ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን መታፈን የፈፀመው የጥፋት ሃይሉን አቅምና የማጥቃት ጉልበት ለመፈተሽ ነው። በተለይም የኦሮሞ የጥፋት ሃይሎች አማራውና  የተዋሕዶ ክርስቲያኑ ሕዝብ በኦሮሞ የጥፋት ሃይሎች ለሚሰነዘረው የመጨረሻ ምፅዓታዊ  የጥፋት ርምጃ ምን ያህል የመከላከል አቅም ይኖረዋል የሚለውንም የመዘኑበት አሰራር ነው። እነዚህ ጥቃቶች የማንቂያ ደወሎች ናቸው። የዓቢይ አሕመድ መንግስት መዋቅሮች ለዚህ ጥፋት ሙሉ መጠቀሚያ መሆናቸውን መገንዘብ ይገባናል

Filed in: Amharic