>

በድህነት አቅም ተቸግረን ያስተማርናት ልጃችን መንግስት ባለበት ሃገር ተነጠቅን``  (የታጋች ተማሪ ስርጉት ጌቴ ቤተሰቦች)

 በድህነት አቅም ተቸግረን ያስተማርናት ልጃችን መንግስት ባለበት ሃገር ተነጠቅን

 የታጋች ተማሪ ስርጉት ጌቴ ቤተሰቦች
መንግስት የታገተች ልጃቸውን እንዲያስመልስላቸው የተማሪ ወላጆች ጠየቁ
ይድነቃቸው ከበደ
በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ፎገራ ወረዳ አባኪሮስ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ቄስ ጌቴ ጥበቡ እና ወ/ሮ የማታ ዋሴ በትዳር 24 ዓመታትን ያሳለፉ ሲሆን 1 ወንድና 5 ሴቶችን በድምሩ 6 ልጆችን ወልደው ለመሳም በቅተዋል ፡፡ ከነዚህ ልጆች መካከል የመጀመሪያ የሆነችውና የደንቢ ዶሎ የዩኒቨርስቲ ተማሪ የ21 ዓመቷ ወጣት ስርጉት ጌቴ ቤተሰቧንና ሀገሯን ለመጥቀም በ2012/ዓ/ም በደንቢ ዶሎ ዩኒቨርስቲ ትምህርቷን ለመከታተል እንደ ሄደች ወላጅ አባቷ ቄስ ጌቴ ገልጸዋል ፡፡
ይሁንና በዩኒቨርስቲው በነበረው ሁከት ህዳር 24/2012 ዓ/ም ትምህርቷን ጥላ ወደ ትውልድ ቀየዋ በመመለስ ላይ እያለች በማይታወቁ ግለሰቦች መታገቷን ለአጎቷ ልጅ በስልክ ነግራዋለች ፡፡ ከኔ ጋርም በስልክ 3 ጊዜ የተገናኘን ሲሆን የመጨረሻ የሥልክ ንግግራቸው ታህሳስ 8/2012 ዓ/ም መሆኑን ገልጸዋል ፡፡
በድህነት አቅም ተቸግረን ያስተማርናት ልጃችን መንግስት ባለበት ሃገር እንደዚህ እንደወጣች መቅረቷ እንዳሳሰባቸው የስርጉት ወላጅ እናት ወ/ሮ የማታ በመግለፅ መንግስት የታገቱ ልጆቻችን በአስቸኳይ እንዲያስመልስላቸው አሳስበዋል ፡፡
ተማሪ ስርጉት ጌቴ በትምህርቷ ታታሪ ትንሽ ትልቁን አክባሪ ለቤተሰቦቿ ታዛዥና ትሁት ልጅ መሆኗን የገለፁት የቅርብ ቤተሰብ የሆኑት አቶ ኪዳን ይትባረክ ልጀ ትልቅ ሰው ትሆናለች በማለት ቤተሰቡ ሳይመቸው የሷን ፍላጎት በማሟላት እንድትማር ያደረጉ ሲሆን በተፈጠረው ችግር ያሳዘናቸው መሆኑን በመግለፅ መንግስት ልጃችን እንዲያስለቅቅ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡
ፎገራ ወረዳ ኮምኒኬሽን
Filed in: Amharic