>

በህግ አምላክ! ለአንዱ ቦታ እያመቻቹ ሌላውን ከስፍራው መግፋት ማንገላታቱ ይቁም !!! (ዲ/ን  ብርሃኑ አድማስ)

በህግ አምላክ! ለአንዱ ቦታ እያመቻቹ ሌላውን ከስፍራው መግፋት ማንገላታቱ ይቁም !!!

 

ዲ/ን  ብርሃኑ አድማስ 
ይህ ሰው ባስቸኳይ በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ጥፋቱ ይጣራልን!!!
 
መምህር ምሕረተ አብን ለማስደንገጥም ይሁን ጉባኤዎችን ለመረበሽ ትላንት ማታ እንደተደረገ የሰማሁት ነገር ብዙ ነገር የሚጠቁም ነው።
 ሰሞኑን ወንድሞቻችን ሰማዕትነት የተቀበሉበትና አዲስ ቤተ ክርስቲያን የፈረሰበት የ24 ቀበሌው ቦታ ያን ሁሉ መዓት ያመጣው ፓስተር ዮናታን ቦታውን እርሱ እመራዋለሁ ለሚለው የመልካም ወጣት ፕሮጄክት በጠየቀው መሠረት ለማስረከብ በጥድፊያ ላይ ስለነበሩ ነው።
ለረጅም ዘመናት የግለሰቦች የይዞታ ቦታ የነበረውንና ከተማው ለፓርክ ወስኘበታለሁ ብሎ ለግለሰቦቹ ምትክ ሊሰጥ ወስኖበት የነበረውን ቦታ ፓስተር ሲጠይቁ ቦታውን ከፓርክነት ለውጦ ለመስጠት ያን ሁሉ ጥድፊያ ከማድረጉም በላይ ጥፋት እንኳ ቢኖር በቤተ ክህነቱ በኩል መፍታት እየተቻለ በሌሊት ሄዶ ጦርነት ከፍቶ ገድሎና አቁስሎ አስሮ እንዲሁም አፍርሶ እልበቃው ብሎ ነው መሰል በነባር ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ላይ ተገኝቶ ረብሻ ለመፍጠር መሞከሩ በእጅጉ ያስተዛዝባል።
ይህን ሁሉ ጥፋት ለመሸፋፈን ነው መሰል ደግሞ አሁንም የታሠሩት የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰዎች ናቸው። ከዚህም አልፎ ወደ ጉባኤ ብጥበጣ መገባቱ ያስገርማል።
 እንዲያውም ለሰዎች መማር የምታስቡ ከሆነ ሰፋ ያለ ተጨማሪ ቦታ የሚገባው ምሕረተ አብ ነበረ። ቢያንስ ተጨበርብረናል ብለው ጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ድረስ ሄደው የከሰሱት የሉምና። ሁኔታው ግን የተገላቢጦሽ ነው።
ለነገሩ እንጂ ሁኔታውስ ከዚህም ያለፈ ነገር መኖሩን የሚጠቁም ነው። ግድ የለም ይሁን።
ሆኖም ወንድሞቻችን በግፍ ሰማዕትነት የተቀበሉበት ቦታ ለማን እንደምትሰጡት ነገ የምናየው ብቻ ሳይሆን ታሪካዊቷ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ፓስተር ፕሮጄክት ጋር እንዴት እንደምትወዳደርና ለማን እንደምትወስኑ ለመስማት በሁሉም ዐይን እንደምትጠበቁ ከወዲሁ ብታውቁ መልካም ነው።
“ከዐው መዓትከ ላዕለ አሕዛብ እለ ኢየአምሩከ፣
ወላዕለ መንግሥት እንተ ኢጸውዐት ስመከ” (መዝ ፸፰ ፥፮)።
1ኛ.ህዝብ ሰብስቦ በኢየሱስ ስም አጠምቃለሁ ብሎ በአዞ አስበልቶ ከሆነ ይጣራልን
2.የሞተ ሰው አስነሳለሁ ብሎ ሲጮህ ውሎ አድሮ የተከደነ መቃብር አስከፍቶ ሃዘንተኛን የባሰ ሃዘንና መከራ ውስጥ ከጨመረ ይጣራልን
3.ይህ ሰው ህዝብ ሰብስቦ እንደ እንስሳ ሷኢየሱስ ስም ሳር ካስጋጠ ይጣራልን
4.ይህ ሰው በጫማ ጥፊ በኢየሱስ ስም ሠይጣንን አወጣለሁ ብሎ የሰው ፊት ካጣመመ ይጣራልን
5.ይህ ሰው ጸበል ውሃ ነው እያለ የታሸገ ውሃ በኢየሱስ ስም መሸጥ አለመሸጡ ይጣራልን
6.ይህ ሰው በተወወደ የምግብ ዘይት ፎቶውን ለጥፎ በኢየሱስ ስም እየሸጠ መሆኑን ይጣራልን
7.ይህ ሰው በአዳራሽ ውስጥ እየጮኸ አንዲት ወጣት ልጅ ፊቱ ስትመጣ እናትሽ ቀይ ናት  አይደል ሲላት አዎ አጭር ናት አይደል ሲላት አይደለችም ስትለው “የራስ ጉዳይ”ማለቱ ይጣራልን….
ይህ ሰው ጧፍ አስበርቶ ወንጌል እያስተማረ ባልጀራችሁን እንደራሳችሁ አድርጋችሁ ውደዱ እያለ ስለሆነ እንኳን በቆንጨራ አይደለም በጣታችሁ ማንንም እንዳትነኩ እያለ ስለሆነ ይልቁንም የማይሞከረውን “ጠላቶቻችሁን ወደዱ የሚረግሟችሁን መርቁ ክፉዉን በክፉ አትቃወሙ እያለ አብዝቶ በመጮህ እያስተማረ ስለሆነ እባካችሁ ይጣራልን።እሱን ፊትጨለፊት ስላገኛችሁትንጂ እሱን ስትይዙት ሌሎቹ ይመጡላችኋል
ያኔ ዓቢይ ድልቅልቅ ይሆናል።
(የአገልግሎታችን ብርታት ወንድሞቹን አቃፊ የሰው ችንር የሚገባው ቀድሞ የሚያለቅስ የሚደርስ ልቡ ርህሩህ መሆኑን እኔ አውቃለሁ) ለነገሩ እኛ አንሰባሰብ ብለናል እንዲህ ነካኩንና  ስንደራጅ ኢትዮጵያና ተዋህዶ በቅርቡ ትንሣኤያቸው ይሆናል።
Filed in: Amharic