>

"የኢትዮጵያ ሕዝብ በአልባሌዎች እየታወከ ነው!" (ብ/ጄ/ል ካሳዬ ጨመዳ )

“የኢትዮጵያ ሕዝብ በአልባሌዎች እየታወከ ነው!”

                  ብ/ጄ/ል ካሳዬ ጨመዳ 
 
* ለምሳሌ በእኔ ደም ውስጥ ሦስት አራት የብሔር ዳራ አለ። የሌሎቻችሁም እንዲሁ ይመስለኛል። ኢትዮጵያችን የዛሬውን ቅርጿን የያዘችው በአባቶቻችን ተጋድሎና በዚህ ተፈጥሯዊ ትስስር የተነሳ ነው።
–‘-
   “ለሰላም ዋጋ መስጠት አለብን። ዛሬ ለኢትዮጵያ አንድነት የቆሙ እንዳሉ ሁሉ አፍራሽ ሆነው ሕዝቡን የሚያውኩ ፓርቲዎችና ግለሰቦች አሉ። እነዚህ አካላት በሕዝብ ስም ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደሚሰበስቡ ይታወቃል። ከዚያ ገንዘብ ላይ ግን አንዲት የውሃ ቦኖ ማሠራት አይፈልጉም። ጥላቻና መለያየት እየዘሩ ግን እንታገልልሃለን የሚሉትን ያንኑ የሕዝብ ክፍል በመከራ ውስጥ እንዲኖር ያስገድዱታል።
   ተለያይተንና ተነጣጥለን ልንኖር አንችልም። የማሕበረሰብ፣ ከፍ ሲልም የሕዝብና የአገር መዋቅር  አስፈላጊነት ተደጋግፎ መኖር ነው። በክርስትናም በእስልምናም እንደሚታመነው አዳም መጀመርያ ብቻውን ነበር። በኋላ ሔዋን ከጎን አጥንቱ ተፈጠረችለት። ተደጋግፈው እንዲኖሩ ነው።
   እኛም እንዲሁ ነን። በሥራ ከአከባቢ አከባቢ ስንንቀሳቀስ በጋብቻ፣ በሁለንተናዊ የማሕበረሰብ ትስስርና በሌሎችም ተዋልደንና ተጋምደን የምንኖር ነን። ለምሳሌ በእኔ ደም ውስጥ ሦስት አራት የብሔር ዳራ አለ። የሌሎቻችሁም እንዲሁ ይመስለኛል። ኢትዮጵያችን የዛሬውን ቅርጿን የያዘችው በአባቶቻችን ተጋድሎና በዚህ ተፈጥሯዊ ትስስር የተነሳ ነው።
   የአገራችን ጠላቶች በመሣሪያ ሞክረውን አልቻሉም። ዛሬ በትልቋ የኢትዮጵያ ጣርያ ስር በጋራ ተደጋግፎ ከማደግ ይልቅ ለገንዘብ ተንበርክከውና ለስልጣን ሲሉ ልዩነትንና መበተንን የሚያቀነቅኑ የሰላም ጸሮች ተፈጥረዋል።
   የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅና ጨዋ ሕዝብ ነው። ይህ ጨዋ ሕዝብ በአልባሌዎች እየታወከ እየተበጠበጠ ነው። መንግሥት ሥርዓት የማስያዝ ሃላፊነት አለበት። …”
       ጀግናው ብ/ጄ/ል ካሳዬ ጨመዳ 
(በዛሬው ዕለት ረፋድ ላይ ‘እናት ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት’ ባዘጋጀው የሰላም ኮንፈረንስ ላይ ካደረጉት የመግቢያ ንግግር የተወሰደ)
Filed in: Amharic