>
5:13 pm - Saturday April 19, 8279

የዐቢይ አሕመድ  የአፓርታይድ አገዛዝ  በታገቱ የአማራ ልጆች ዙሪያ እየሰራው ያለው ነውረኛ ድራማ ሲጋለጥ!!!

የዐቢይ አሕመድ  የአፓርታይድ አገዛዝ  በታገቱ የአማራ ልጆች ዙሪያ እየሰራው ያለው ነውረኛ ድራማ ሲጋለጥ!!!

አቻምየለህ ታምሩ
ከሰሞኑ ስለታገቱ የአማራ ልጆች አንዳንድ ወናፎች ወሬ ሲያሰራጩ ሰንብተዋል። በዛሬ እለት ደግሞ ታግተው ነበር የታባሉ ሁለት ሴት ወጣቶችን ፎቶዎች ተሰራጭቶ አይተናል። እውነቱን ከስር ለማጣራት ባደረግነው ጥረት  የዐቢይ አሕመድ  የአፓርታይድ አገዛዝ  እንደ ጅሃዳዊ ሀረካት› አይነት  ‹ዶክመንተሪ ፊልም› በታጋቾቹ ዙሪያ እያዘጋጀ መሆኑን ደርሰንበታል። ስለ አጠቃላይ ድራማው የውስጥ ምንጫችን የላከልንን ሚስጥራዊ ማስረጃ እንደወረደ እንዲህ አቅርበነዋል! 
_______________
ጤና ይስጥልኝ ወንድሜ! በአማራ ተማሪዎች እገታ ላይ መንግሥታዊ ትዕይንተ ድራማው ቀጥሏል። አሁን እየተደረገ ያለው ነገር እንዲህ ነው። ሁለት አማራ ወጣት ሴቶች ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጎንደር ከተማ ፣ ቀበሌ 18 ተነስተው ወደ ባሕር ዳር አካባቢ ለፀበል ይሄዳሉ። ከፀበል ቦታ ተመልሰው ባሕር ዳር ከተማ እንዳረፉ በአንድ የደኅንነት ሰው እይታ ውስጥ ገቡ። ይህ ሰው ነጋዴ እንደሆነ በመግለፅም ይተዋወቃቸዋል። ይህ ሰውም ሴቶቹን በቅንንነት በመቅረብና በማግባባት ለተለያዬ ቀናት በማግኘት ሲጋብዛቸውና ሲያዝናናቸው ቆይቷል። በመቀጠልም እነዚህን ሴቶች በገንዘብ አታሎ በፍቅር ለመጣል አንዷን ይህ ነጋዴ ተብዬ የደህንነት ሰው፤  ጓደኛዋን ደግሞ ለአንድ በእድሜ ሽማግሌ ለሆነ ሰው ለፆታዊ ግንኙነት ቢጠይቋቸውም፤  ሴቶቹ  ግን አሻፈረኝ ይላሉ።
ከዚያም የልጆቹን የኢኮኖሚ አቅም እንደመጫዎቻ ካርድ አጥብቆ የያዘው የደኅንነቱ ሰው አንድ ስራ ሊያሰራቸው እንደሚፈልግና ለስራውም እስከ ቤተሰቦቻቸው ድረስ ሕይወታቸውን የሚቀይር ጠቀም ያለ ገንዘብ ሊከፍላቸው እንደሚችል ይነግራቸዋል። ሴቶቹም በጉጉት ስራው ምን እንደሆነ ሲጠይቁት ከታጋች ተማሪዎች መካከል እንደነበሩና በውሸት “ታግተናል” እንዳሉ ለሚዲያ እንዲገልፁ ይጠይቃቸዋል። ይህ ሰው የተለያዬ ሀገራት ገንዘቦችን ከመያዝና ከማግባባት ክህሎቱ በተጨማሪ ሽጉጡን በማሳየት የስነ ልቦና ጫና በሴቶቹ ላይ በማሳደር ሀሳቡን እንዲቀበሉ ያደርግ ነበር።
በመቀጠልም «ከታጋች ተማሪዎች መካከል የመጣን ነን በማለት አማራነታችንን ተጠቅመን የአማራ ሕዝብ በመንግሥት ላይ እንዲነሳሳ በፖለቲካ ድርጅቶችና በግለሰቦች ምክርና ድጋፍ ተደርጎልን ታግተናል ብለን ተናግረናል። እኛም መንግሥትንና ሕዝብን አሳስተናል። ስለዚህ መንግሥትንና ሕዝብን ይቅርታ እንጠይቃለን።»  ብለው እንዲናገሩ ለ10 ተከታታይ ቀናት በባሕር ዳር ስልጠና ሲሰጣቸው ቆይቷል። ከስልጠናው በኋላም መንግሥት ወደ አዲስ አበባ በመውሰድ ለደኅንነት ሲባል ለጊዜው ስሙ የማይጠቀስ ትልቅ ሆቴል እንዳያርፉና ለሁለት ቀናት እንዲቆዬ አድርጓል። በሁለት ቀናት የአዲስ አበባ ቆይታቸው ውስጥ ለደኅንነት፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለሴቶች ጉዳይና ለሌሎች የመንግሥት መስሪያ ቤቶች በስልጠና እንዲያጠኑት የተደረገውን የድርሰት ቃል እንዲሰሰጡና ቃላቸው እንዲቀረፅ ተደርጓል።
እነዚህ አማራ ወጣት ሴቶች ስማቸውና ግላዊ ማንነታቸው የሚከተለው ነው።
1. ሸዋዬ ገነት ተዘራ፡ ሸዋዬ ማለት በተለቀቀው ፎቶ ላይ ጥቁር ሰማያዊ የስፖርት ጃኬት የለበሰችው ልጅ ናት። ሸዋዬ ሁለት ልጆች  ያሏት ስትሆን  የዩኒቨርስቲ ተማሪም አይደለችም።
  አድራሻ፦ማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጎንደር ፣ከተማ ፣ቀበሌ 18 ዕድሜ 18 የትምህርት ደረጃ 8ኛ ክፍል
2. ቅድስት ጋሻው አበበ፡ ቅድስት በተለቀቀው ፎቶ ላይ   በአግድም ነጭ ሰንበር ያለበት ቀይ ቲሸርት የለበሰችው ናት።
አድራሻ-:ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ዕድሜ 17 ብትልም የተመዘገበ ግን  18 ተብሎ ሲሆን  የትምህርት ደረጃ፦ 8ኛ ክፍል
ልጆቹ ድርሰታዊ ቃላቸው በተለያዬ የመንግሥት መስሪያ ቤት እንዲቀረፅ ከተደረገ በኋላ መንግሥት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚመልሳቸው ቢጠብቁም   «ማጭበርበር» የሚል የክስ መዝገብ ተከፍቶባቸው፤  ማለትም «ሳይታገቱ  ታግተናል ብለው እንዳጭበረበሩ እንዲሁም መንግሥትና ሕዝብን እንዳሳሳቱ»  ተደርጎ እያለቀሱ ወደ እስር ቤት ተወርውረዋል።
በተጨማሪም ከዚህ ድራማ ጋር በተያያዘ ሁለት ሰዎች በአዲስ አበባ በፖሊስ ተይዘው ወደ እስር ቤት ገብተዋል። እነዚህም፡-
1 ፍቅርተ ቸኮል ተገኝ ስትሆን  አድራሻዋ  አዲስ አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11  ሲሆን ክስ፦ ከአጋች ጋር መመሳጠር ይ የሚል ነው። ይህቺ ሴት የታጋች እኅት ነች።
2 ወንድሜነህ ዋሴ ልመንህ አድራሻ ፦አዲስ አበባ ከተማ ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ፣ አዲስ ሰፈር ስራ፣ የሞሐ ለስላሳ መጠጦች የጥበቃ ሰራተኛ፤  ክስ፦ ሰው እገታ ይህ ሰው ከስራ ቦታው በፖሊስ ተይዞ ወደ ስር ቤት የተወሰደ ነው። ቃሉን ሲሰጥም ምንም የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ገልፆል።
ማስታወሻ፦ ወደ ወለጋ ማለትም ተማሪዎቹ ወደ ታገቱበት ቦታ የተጠናከረ ኃይል ከመላክ ይልቅ ይህን ድራማ ”የተዋጣለት” ለማድረግና የአማራን ሕዝብ ለቅሶ ለመቀማት ከደኅንነትና ከፌደራል ፖሊስ የተውጣጡ አባላትን የያዘ የልዑክ ቡድን ወደ አማራ ክልል የዘመተ ሲሆን የታጋች ቤተሰቦችንም በዛቻና ማስፈራሪያ ድምጻቸውን እያፈነ ይገኛል።  ወደ ጎንደር የተሰማራው የምርመራ ቡድን  ቀደም ብሎ የቀረበውን ድራማ እውነት አድርጎ በማቅረብ  ባለፈው ሰሞን ስለ ታጋችቾች እውነተኛ ማስረጃ የሰጠችውን ከታገተችበት ያመለጠችውን ልጅ « ባልደካሄደ እውነተኛ ጠለፋ በመንግሥትና ሕዝብን በመዋሸት» ክስ  ለመያዝ የፍርድ ቤት ትዛዝ ይዞ ሂዷል።
Filed in: Amharic