እጅግ በጣም አሳዛኝ መልእክት?!?
ሙሉጌታ መልዬ
* ኢትዮጵያ ከትናንት እስከዛሬ መከራዋን የሚያበዙት፣ ስውር አጉራሽ እጆች፣ የናት ጡት ነካሾችን አበዙባት፣ ትንሽ ማር በብዙ መርዝ ለውሰው ሰጧት፣ ሀገሪቱን በሰፊው በከሏት፣ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ረስቶ ፣ በሌሎች አለባሌ ጉዳዮች ተወጥሮ ፣ ከመለወጥ ወደ ጥፋት ፣ በገደል ላይ እንዲጓዝ አደረጉት…
ጆሮዬ_ጭልል_ውውውውው የሚል ነገር ተሰማኝ ጆሮዬን በቀኝ እጄ አሸት አሸት ሳደርገው “hallo halo አቤት አልኩት! ከአሜሪካን ነው የምደውልልህ ሰላም ነህ አቤሴሎም ? ሲለኝ ደህና ነኝ!…Confused.
በጣም የማውቀው የሚመስል ደስ የሚል ድምጽ በጆሮዬ ገባ ፣ ማን እንደሆና ስለራሱ ጠየቁ መለሰልኝ።ወሬ ተጀመረ ስለ አሜሪካን ፣ ስለ አውሮፓ ስልጣኔ ያወራኝ ጀመረ እኔም እጠይቃለሁ እሱም ይመልስልኛል።
ከውጭ ወደ ሀገር ቤት አመጣኝና ስለሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮችም አወራን ፣ ስለ ድሮዋ ኢትዮጵያና ስልጣኔዋ፣ያች ታላቅ ሀገር እንዴት እንደተገነባችና እንዴት ቁልቁል እንደመጣች በሚገርም ሁኔታ ተነተነልኝ!!አንተ ” የስነፍጥረት ሊቅ ነህ ወይስ የታሪክ ምሁር ነህ አልኩት?” ረጅም ሳቅ ሳቀ…….. ደነገጥኩ! የተወሰነ አወራኝ ።
እኔም ስለ ወደ ፊቷ ኢትዮጵያ ጠየኩት!!!
እናንተን የመሠለ ምሁር እያለን ኢትዮጵያን ካለችበት ችግር አውጥተን ታላቋን ኢትዮጵያ ለምን አንመሠረትም አልኩት?
“ዋናው የደወልኩልህ ይህን ላወራህና ለኢትዮጵያ ህዝብ የምታስተላልፍልኝ መልእክት አለኝ።” እኔ ዝም
አቤሴሎም? ሲለኝ
አቤት አልኩት! በእልህም እና በደስታም መሀል ሆኖ ረጅም ታሪክ አውራኝ….! ቀጠለ
የውጭው አለም በተለይ ያደጉ ሀገሮች ያለ ኢትዮጵያ ባዶ መሆናቸውን እንዲህ ሲል በአጭሩ ነገረኝ ።
ፈረንጆቹ ኢትዮጵያ በፈጣሪ የተባረከች የቃል ኪዳን ሀገር መሆኗን ያምናሉ!!!
ፈጣሪ ለኢትዮጵያውያን እውቀትና ሃይለመለኮት ፣ ጥበብና መጎስን ተሰጥቷቸዋል፤ ይህን ጸጋ ይዘው ሀገርና ህዝቡን አንድ አድርገው ይመራሉ፣ ሃያል ሀገር መስርተው አለም ላይ ተጽዕኖ ፈጣሪ ይሆናሉ ብለው ስለሚያምኑ #ኢትዮጲያን በሁለት ነገር ማዳከም፡ ከቻሉም ማጥፋት አጀንዳ አድርገው መስራት ከጀመሩ አምስት መቶ አመት አለፋቸው አለኝ።”
በአምሮዬ ከመቶ አመት በፊትና በሇላ የነበረችውን ኢትዮጵያ ሳስብ እስከ አሁን የነገረኝን ነገር ማመን ጀመርኩ ። ዘመነ መሳፍንት የነሱ ስራ ይሆን? አሰብኩ
እሺ ቀጥል አልኩት………
አንደኛ
“ወዳጅ መስለው ወደ ሀገራችን በመግባት እርስ በእርስ ከፋፍሎ ማጣላትና ሀገሪቱን በታትነው በራሳቸው ቁጥጥር ስር በማድረግ ሞክረዋል ፣ ታላቋን ኢትዮጵያ በታትነው አሳንሰዋታል ነገርግን ማጥፋት አልተቻላቸውም። ይህን ከ5መቶ አመት በፊት የጀመሩት ሴራ ዛሬም ድረስ እንደዘለቀ እያየህ ነው አለኝ ። ” አዎ አልኩት…….
ሁለተኛው
“ኢትዮጵያዊያን የሰሩትን ጥበበኛ ስራ ማጥፋትና ተንቀሳቃሽ ሀብቶችን መስረቅ ፣ የሰረቁትን ተንቀሳቃሽ መጽሀፍትንና ቅርጻቅርጽ ሲወስዱ የእውቀቱ ባሌቤት የሆኑትን ሰዎችን አብሮ በመውሰድ ፣ እነዚህን የተለያዩ መጽሐፍት እንዲያስተምሩ በማድረግ እና ወደ ተግባር በመቀየር ዛሬ ለደረሱበት ስልጣኔ ኢትዮጲያና ሀብቷ አስተዋጽኦ አድርገዋል።” አለኝ
“ኢትዮጵያ ከትናንት እስከዛሬ መከራዋን የሚያበዙት፣ ስውር አጉራሽ እጆች፣ የናት ጡት ነካሾችን አበዙባት፣ ትንሽ ማር በብዙ መርዝ ለውሰው ሰጧት፣ ሀገሪቱን በሰፊው በከሏት፣ ትውልዱ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ረስቶ ፣ በሌሎች አለባሌ ጉዳዮች ተወጥሮ ፣ ከመለወጥ ወደ ጥፋት ፣ በገደል ላይ እንዲጓዝ አደረጉት። ይህን የክፋት ሴራ መሪዎችም መረዳት ተሳናቸው…”
የደዋዩ አሳዛኝ መልእክት
አቤሴሎም …. ” እንግዲህ ኢትዮጵያ መለወጥ ስላለባት ወደፊት እንድትሄድ ከፈጣሪ የተሰጠንን ጸጋ መጠበቅ አለብን እነርሱም ይህን ስለሚያውቁ ከኢትዮጵያ ስር አይወጡም ። ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የተሰጣቸውን ፣ ሀይላቸውንና ሞገሳቸውን አይወስዱም ። ጥበብና እውቀት ዛሬም በኢትዮጵያ አለ። እንድሮው አይሰርቁም አያስገድዱም። ነገር ግን ጥበብን ና እውቀትን በትንሽ ገንዘብ ይወስዳሉ። ኢትዮጵያ በርካታ ጥበብና እውቀት ውጭ ሀገር አላት ለዚህ ደግሞ ሊክሱን ይገባል።
ወደ መልእክቴ ልግባልህ
እኔ ጎበዝ ተማሪ ስለነበርኩ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሆኘ በስኮላርሽፕ ከሀገሬ ወጣሁ። እዚህ ሀገር ተማርኩ አሁን ታላቅ ሳይንትስት ነኝ ነገርግን አያምኑኝም ፣ እውቀቴን ይጠቀማሉ ፤ ከሀገሬ ባህል ውጭ በተደጋጋሚ በወንዶች ተደፍሪያለሁ ። ከስራ ውጭ እጠጣለሁ ኢትዮጵያዊ ሳይ አለቅሳለሁ። ቤተሰቦቸ ጋ እንዳልሄድ ተደርጌያለሁ ። እንደኔ በስኮላርሽፕ የመጡ ታላላቅ ምሁራን እዚህ ሀገር አሉ።ተመሳሳይ ነገር ደርሶባቸው በሞራል ዝቅጠት ውስጥ ይኖራሉ ። ለትምህርት መጥተው ጎበዝ ከሆኑና እነሱ ከፈለጉህ የትም አትሄድም! ብትሄድም ይመልሱሀል ስጋት ከሆንክ ይገሉሀል።
ኢትዮጵያን መለወጥ ካለብን ከ20አመት በታች ለትምህርት ብለው ከሀገራችን ልጆች አይውጡ።ዛሬ የምትፈልገውን ሀገርህ ሆነህ ትማራለህ፣ከሀገሩ የወጣ የሳይንስ ተማሪ ጎበዝ ከሆነ ስለማይመለስ እዚያው ” ናሳን ሆሊውድን “መፍጠር ይችላሉ ። እዚያው በደንብ መስራት አለባቸው ስኮላርሺፕ መሰጠት ያለበትም የመጀሪያ ድግሪ ከተማሩ በሇላ እና የሀገራቸውን ባህልና ወግ አውቀው ቢቻል የግእዝ ትምህርት በየ ገዳማቱ ተምረው ነፍስ አውቀው ከሀገር ቢወጡ ነገሮችን ስለሚረዱና እነሱም በሚስጥራዊ የሚሰሩ ስራዎችን ስለማያሰሯቸው ይመለሳሉ ፤ ሀገራቸውንም ያግዛሉ ፣ ልጆች ከመጥፎ ሀገራዊ ጥላቻ ርቀው ለሀገር እና ለትውልድ የሚያልፍ ስራ እንዲሰሩ ከታች ጀምሮ ይማሩ ።
የጥበብ የእውቀት የሀይልና የግርማሞገስ ስጦታ አለን ይህን ትውልዱ ይጠብቅ። የሆነ ትውልድ ዋጋ ከፍሎ ታላላቅ የምርምር ስራዎች የሚሰሩበት ተቋም እዚያው ይፈጠርላቸው ፣ እውቀትና ብቃት ያለቸውን ልጆች በአንድ ተቋም ሰብስቦ እዚያው ማስተማርና እንዲመራመሩ በማድረግ መንግስት እንዳይሰንፍ ፣ ቤተሰብም ልጆቹ እራሳቸውን ሳይችሉ ከሀገር እንዳይወጡ ያድርጓቸው ።”
ይህን መልእክት አድርስ ብሎኝ ስልኩን ዘጋው ። የነገረኝ ነገር ለማጣራት ሞከርኩ ከኢትዮጵያ የወጡ ባለምጡቅ አእምሮ ለትምህርት ሄደው ተመልሰው ሀገራቸውን ሲያገለግሉ አላዬሁም። እና የደዋዩን መልእክት ለማስተላለፍ ተገደድኩ! ያወራነው በቴሌፓዝ ነበር። የነገረኝ ብዙ ነበር በጥቂቱ አካፈልኳችሁ ።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና እኛ ልጆቹን አብዝቶ ይባርክ! ! አሜን