>
6:29 am - Wednesday December 7, 2022

የቀድሞው ቀሲስ በላይ አቶ በላይ ኾኗል!!! ክስ እንዲመሰረትባቸው ተወስኗል!!!

የቀድሞው ቀሲስ በላይ አቶ በላይ ኾኗል!!!

 

አባይነህ ካሴ
 

ቅዱስ ሲኖዶስ የእርሱን እና ግብረ አበሮቹን ሥልጣነ ክህነት ይዞባቸዋል!!!

 
ተፀፅተው በይቅርታ እስኪመለሱ ክህነታቸው ተይዞ ይቆያል።
ክስ እንዲመሰረትባቸው ተወስኗል!!!
ጥፊ ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰም አትሰማ እንዲሉ ስንት እና ስንት የበጎነት እና የምሕረት ጥሪ ሲያደርግ የቆየው ቅዱስ ሲኖዶስ ከውግዘት በፊት አንድ የመጨረሻ ዕድል ሰጥቷል። በጊዜ ገደቡ ውስጥ እነዚህ ግለሰቦች ይቅርታ ለመጠየቅ ከተሳናቸው ተወግዘው ይለያሉ።
የኦሮሚያ ቤተ ክህነትን እናደራጃለን የሚለው ሕገወጥ ቡድን አስተባባሪዎች መካከል የዐራቱ ሥልጣነ ክህነት ተይዟል፡፡ ከሕገ ወጡ ቡድን ጋር በተያያዘም ዐራት መሠረታዊ ውሣኔዎችን አስተላልፏል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ከቀትር በኋላ ባደረገው ጉባኤ ይህን መወሠኑን ከሚከተለው የሐራ ዘተዋሕዶ ዘገባ ተረድተናል፡፡
ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን፣ አባ ገብረ ማርያም፣ ዲን. ኀይለ ሚካኤል ታደሰ [ዲቁና የነበረው እንኳን አይመስለኝም አንድም ቀን ራሱን በዲቁና ሲጠራ አላውቅም]፣ ቄስ በዳሳ ከነገ የካቲት 11 ቀን ጀምሮ በጥፋታቸው ተጸጽተው ከተግባራቸው በይቅርታ እስኪመለሱ ድረስ ሥልጣነ ክህነታቸው እንዲያዝ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ልዩነት በሌለው ድምፅ ወስኗል፤
• “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እናዳራጃለን” በማለት በመዋቅር ላይ መዋቅር በመፍጠራቸው እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ማኅተም አስቀርፀው በመንቀሳቀሳቸው፣ በአገሪቱ ሕግ ይጠየቃሉ፤
• ያስቀረፁት ማኅተም ገቢ እንዲደረግ፤ የከፈቷቸው ጽሕፈት ቤቶች፥ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የተከፈቱ እና ሕገ ወጥ በመኾናቸው እንዲዘጉ እንዲደረግ ወስኗል፤
• ኢሬቻ እና ዋቄፈናን ከኦርቶዶክስ ክርስትና ጋራ በማመሳሰል የሚያደናግሩ፤ ቤተ ክርስቲያንን ያለስሟ ስም እየሰጡ የሚተቹ እና በቡድኑ ድጋፍ ለታተሙ መጻሕፍት፥ የሊቃውንት ጉባኤ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ ቋንቋዎች መልስ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶሱ አዟል፡፡
Filed in: Amharic