>

በአሜሪካ ሜሪላንድ የአድዋ ድል ወር ተሰየመ! ዲያቆን (ዓባይነህ ካሤ)

በአሜሪካ ሜሪላንድ የአድዋ ድል ወር ተሰየመ!

ዲያቆን ዓባይነህ ካሤ
ያን የጥቁር አልማዝ እምዬ ምኒልክን እንኳን ደስ አለህ እንበለውማ። ምክንያት ፡ – ሞቶም ታሪክ ይሠራልና! እንደዚህ ያለ ጀግና የወለድሽ ኢትዮጵያ የማኅፀንሽ ልምላሜ ሲያስገርመን ይኖራል!!!
በችግር ጊዜም ቢኾን ይህች ሀገር ታሪክ ከመሥራት የሚያወርዳት የለም። የኢትዮጵያ መብራቷ ለዓለሙ ፋና ነው።
በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ውስጥ ፶ /50/ ግዛቶች /States/ ይገኛሉ።  ከእነዚህም መካከል አንዱ ሜሪላንድ ይባላል። በዚህ ግዛት ውስጥ ከሚኖሩ የውጭ ሀገር ተወላጆች በቁጥር ኢትዮጵያዊያን ኹለተኛ ደረጃ ይዘዋል።
ይህንን መሠረት አድርጎ የሜሪላንድ ግዛት መንግሥት March 2020 የአድዋ ድል ወር ተብሎ እንዲሰየም ወሥኗል።
#ያን የጥቁር አልማዝ እምዬ ምኒልክን እንኳን ደስ አለህ እንበለውማ። ምክንያት ፡ – ሞቶም ታሪክ ይሠራልና! እንደዚህ ያለ ጀግና የወለድሽ ኢትዮጵያ የማኅፀንሽ ልምላሜ ሲያስገርመን ይኖራል።
ኢትዮጵያ በምዕራባውያን ላይ አሳማኝ ድል / landmark defeat for western forces/ የተቀዳጀችበት ነው ይላል።
Filed in: Amharic