>

የተንቤን ማፈሪያ ስየ አብርሀ!!! (አዳነ አጣነው)

የተንቤን ማፈሪያ ስየ አብርሀ!!!

 

አዳነ አጣነው
ስየ አብርሀ በተንቤን ታሪክ ውስጥ ተውልዶ ያልታየ የጉደ ማፈሪያ ነው፡፡ ስየ  ሀወሀትን ተቀላቅሎ ሲሸፍት የአድዋ መንደርተኞች ገብረጻድቃን በሚባል አዝማሪ ተንቤን፣አጋሜን፣እንደርታን እና 2 አውላሎን ንጹህ ትግሬ አይደሉም በሚል ሲያዘፍኑ ስየ አብርሀ አብሮ ከአድዋ መንደርተኞች ጋር ከበሮ ይመታ ነበር፡፡
በአጭሩ በሺ የሚቆጠሩ የተንቤን ተወልጆች በአድዋ ህወህት እንዲገደሉ ስየ አብርሀ ሙሉ ትብብር አድርጓል፡፡ለወደፊትም ይጠየቃል፡፡
ስየ አብርሀ፣ የሌለ ህግ በ24 ሰአት ታውጆ እስር ቤት በጉቦ ተከሶ ሲወረወር ፈሪ ስለሆነ ተው ይሰሩኝ ብሎ ያሰሩትን ያዋረዱትን የወያኔ አመራሮች ሳያወግዝ፣ የሰሩትን አውራጃዊ ወንጀል እንዃ ከተፈታም በኻላ ሳያጋልጥ ሳይሞግታቸው ቀረ፡፡
ስየ አብርሀ ወህኒ በጉቦ ተከሶ ሲወርድ፣ ባለቤቱን በ24 ሰአት ከመንግስት ቤት እንድትወጣ ስትታዘዝ የቤት እቃን እንኳ ማስቀመጫ አጥታ የቤት እቃዎች እንዳሉ መንገድ ላይ ተወረወሩ፡፡ ባለቤቱ ቤት እንኳ ለመከራየት በወያኔ አለቆች ተከልክላ በየዘመዱ ቤት ነበር እየዞረች ያሳልፈችው፡፡
ስየ በኻላ ወያኔዎች የውሸት ፊታቸውን ፈገግ ሲያደርጉለት ተስፋ አድርጎ በወያኔ ምክርቤት ተንቤንን ወክሎ ተስፋ ሳይቆርጥ ለመወዳደር  ተንቤን ሲገባ ዘመዶቹ እና የባለቤቱ አባት አናስገባህም አነተ ፈሪ አናውቅህም ሲሉ ፊት ነስተውታል፡፡
ስየ አብርሀ በቅርቡ እነ ስብሀት አዲስ ቤት ሰርተው ተበድለሃል በሚል ቧልት ወጭውን ሸፍነው “አወ ባለፈው ተበድለሀል” በሚል አዲስ ሰበካ ሆዱ ራርቶ ሰሞኑን በትግራይ ህዝብ ላይ የተደገነ አደጋ በሚል የለየለት ውሸት ከወያኔ ወንጀለኞች ጋር አብሮ ደረቱን መደለቅ ጀምሯል፡፡ እረ ለመሆኑ የፍርሀት መልኩ ስንት ነው? ቀለሙስ ምን ይመስላል?
ስየ አብርሀ እባክህ አንተ እንደተዋረድክ እራስህን ችለህ ተዋረድ ግን ተንቤንን አታዋርድ፡፡
ወያኔ በራሱ ክብደት በወደቀበት በአሁኑ ስአት የወያኔን ወንጀል ለመካፈል መሮጥህ የጤንነት ሳይሆን የፍረሀት መንገድ ነው፡፡ ትግራይ ከነስብሀት ነጋ ቤተሰቦች ውጭ ጠላት የለውም፡፡ አንተም ሲበሉ ያልጠሩህ አሁን የወንጀላቸው ተካፋይ መሆንህ ከቶ ለምን ይሆን?
Via ተሻገር ገብሩ 
የተንቤን ህዝብ እንባ ጠባቂ ንቅናቄ
Filed in: Amharic