>

የጥላቻ ህጉ ለኦ.ኤም.ኤን ሲሆን ሁሌም አቅም የሚያጣው ለምን ይሆን?!? (ሙክታሮቪች)

የጥላቻ ህጉ ለኦ.ኤም.ኤን ሲሆን ሁሌም አቅም የሚያጣው ለምን ይሆን?!?

ሙክታሮቪች
 
* “ነፍጠኛ ባሎቻችሁን ሚስቶቻችሁን ፈታችሁ እኛን አግቡ… “
የአዳማዋ ቄሪት
* የፕሮፍ መራራ እና የዚህች ልጅ ነገር…???
ፕሮፍ መረራ በመፅሃፉ አንዴ አሜሪካ ሳለሁ ዲያስፖራ የኦነግ አባል በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሰበሰብንበት ለጥያቄ እጁን አነሳ እና በኦሮሚኛ መናገር ጀመረ እያሉ ገጠመኛቸውን ይናገራሉ …..
ሁላችን በምንሰማው አማርኛ ወይ በእንግሊዝኛ እንዲናገር ብንማፀነውም አሻፈረኝ አለ። ከዚያ እሱ በኦሮምኛ ሲናገር ወደ አማርኛ የሚመልስ ሰው ተፈልጎ ተገኘና ጥያቄውን አቀረበ።
ዝግጅቱ ካለቀ ከቀናት በኋላ ይህን ልጅ በእኔ የሽኝት ፕሮግራም ላይ በአማርኛ እየቀለደ ቆንጆ ቆንጆ ሴቶችን ሲያሽኮረምም ሲያሳስቅ ጉንጫቸውን ሲቆነጥጥ አብሯቸው ሲስቅ አየሁትና አጠገቤ ያለውን ልጅ ጠርቼ:
“ይሄ ልጅ በቀደም አማርኛ አልችልም ብሎ በአስተርጓሚ የተናገረው አይደል?” ብዬ ስጠይቀው፣ ልጁ ከት ብሎ ስቆ ሲያበቃ እንዲህ አለ:
“ይሄ ልጅ እኮ ፖለቲካ ሲሆን አማርኛ ይጠፋበታል። የአማራ ሴቶችን ለማሽኮርመምና ለመጀንጀን ለፖለቲካ የጠፋበት አማርኛው ከች ይልለታል” 😀 ብሎ አሳቀኝ ይላሉ በመፅሃፋቸው።
ትናንትና ይህች ልጅ የአዳማ ልጅ ነኝ ብላ
እኛ የአዳማ ቀሬዎች የትግል እስትራቴጂ የኦሮሞ ወንድ የሀበሻ ሴቶችን እንዳያገባ ማድረግ ነው። ትግላችን ከዚህ ቀደም ያገቡትን ማፋታት ይጨምራል። ያላገባችሁ ቆንጆ ቆንጆ የኦሮሞ ሴቶች ተዘጋጅተዋል። ለምሳሌ እኔ እዚህ ፊታችሁ የቆምኩት አላገባሁም። ትግላችን ሁለገብ ነው። ከአዳማ የሴቶች ትግል ሌሎች የኦሮሚያ አካባቢ ልምድ መውሰድ አለባቸው። ትግሉ የማይሳካበት ምክንያት ስለህዝባችን አውርተን ቃል ተጋብተን ወደ ቤታችሁ ስትመለሱ ቤት ያለችው ነፍጠኛ ሀሳባችሁን ትበትነዋለች” 😀 😀 
እያለች ስታብራራ እና ስትበጠረቅ ፕሮፍ መራራ ከበቀለ ገርባ ጋር ሆኖ በዚሁ መድረክ በልጅቷ የትግል ስልት አፍሮ ተሸማቆ አንገቱን መድፋት አልያም ማስቆም ሲገባው ትርጉም የማይሰጥ  ሳቅ አይሉት መገልፈጥ ሲንተከተክ ነበር።
ለነገሩ ምን ታድርግ ልጅቱ? አቅም የሌላቸው መሪዎች በብሄራቸው ታዝለው ወደስልጣን ሲመጡ አየች። ከዚያም እሴም በብሄሯ ታዝላ ወደ ትዳር ለመምጣት ሞከርች :: ይኸው ነው የብሄር ፖለቲካ ግብ። አለቀ
በዚህ  አሳፋሪ ፕሮግራም ኦኤም ኤን እራሱን እየሰደበ ነው። የቲቪው ባለቤት ጃዋር እራሱ በእናቱ የመንዝ አማራ ነው። ከአማራ ያልተጋባ ኦፒዲዮ/ኦዲፒ ማግኘት ከባድ ነው። ፕሮፍ መረራ (የዛሬን አያድርገውና 😀 )  ከአማራ ሚስታቸው ጋር እያደሩ ለእኛ የማይመስል ፖለቲካ ይነግሩናል ብሎናል ካድሬው ነፍጠኛ ብላ ብላ ማለቱ አናዷቸው።
 እኔ ይህን የማነሳው ኦሜን እንዲህ ህዝብ ለ ህዝብ መቃቃር የሚፈጥር ፕሮግራም መስራት የለበትም ለማለት ነው። የጥላቻና ሀሰተኛ መረጃ አዋጁ ይህን ተግባር ከግምት በማስገባት ነው የፀደቀው።
ምነው ኦሜን ግን የኢኮኖሚ ትንተና፣ የፖለቲካ ትንትና፣ የስነጥበብ፣ የታሪክ፣ የስኬት ተምሳሌት ታሪኮች፣ የአውደሰብ፣ የቴክኖሎጂ፣ የታሪክ፣ የስነክዋክብት፣ የፈጠራ እና የስራ አፈላለግ፣ የውይይትና ቶክሾው፣ የፋሺን፣ የዝክረባህልና ትውፊት፣ የትምህርት፣ የልጆችና ወጣቶች ፕሮግራም፣ የአለማቀፍ ዜናና ሁነት ትንታኔ፣ የሳቅና ወዘበሬታ፣ የምግብ አሰራር እና ወዘተ (ሌላውን በክፍያ ነው የምናገረው 😀 ) እንደማቅረብ የዘርና የጎጥ ነገር ላይ አኝኝኝ ማለት ምን ይረባል? ኧረ ታረሙ!? ምነው እቴ! አለች እትዬ ከበቡሽ 😀
የብሄር ፖለቲካ ሀገር ያፈርሳል ስንል የምታሾፍ ሁላ እንግዲህ ምን ይዋጥህ? ሀገር ማፍረስ የሚጀመረው ቤተሰብን በማፍረስ ነው።
ትግሉ ተወሳስቧል ወገን! ሆ! አለች እሜት ከበቡሽ?
Filed in: Amharic