>
5:13 pm - Tuesday April 19, 2078

የፖሊስ አመራሮች ቶርች እያደረጉት በጨለማ ክፍል ለወራት የታሰረው ፖሊስ አቤቱታ አሰማ!!! (ባልደራስ)

የፖሊስ አመራሮች ቶርች እያደረጉት በጨለማ ክፍል ለወራት የታሰረው ፖሊስ አቤቱታ አሰማ!!!

ባልደራስ
* የፌደራል ፖሊስ አባል ምትኩ ተሾመ በባልደራስ ቢሮ ለአቤቱታ በመምጣቱ ማስፈራሪያ እየደረሰዉ መሆኑን ተናገረ። 
ሰሞኑን በ”ባልደራስ ጽ/ቤት በአካል ቀርቦ ህዝብ ይወቅልኝ በማለት የደረሰበትን አሰቃቂ  የ”ሰብዓዊ መብት ጥሰት ያጋለጠው የፌደራል ፖሊስ አባል ዋና ሳጅን ምትኩ ተሾመ  በውጪ ሀገር ስልክ ከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራራት በሱና በቤተሰቡ ላይ እየደረሰ መሆኑን ገልጿል። ዋና ሳጅን ምትኩ ተሾመ  በታሰረበት ጊዜ የተፈጸመበትን ድብደባና አካላዊ ጉዳት ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልክቶ ደብዳቢዎቹ ለህግ እንዲቀርቡ በወቅቱ ቢጠየቅም ተጠርጣሪውን አናውቅም እኛ ጋር የለም በማለት በእስር ቤት በነበረበት ጊዜ ፖሊስ መጥሪያ አንቀበልም እስከማለት መድረሱን በማስታወስ እስካሁን ፍትህ አጥቷል።
 ዋና ሳጅን ምትኩ ተሾመ  የደረሰበት የአጥንት ስብራት የህክምና  ሰነድ ጨምሮ አቤቱታ ያመለከተበትን ደብዳቤ በመያዝ በባልደራስ ጽህፈት ቤት ቀርቦ ሲያስረዳ በዋናነት የአንድ አካባቢ ተረኛ የፖሊስ አመራሮች ቶርች እዳደረጉት በማዕከላዊ እና በመለስ አካዳሚ  ጨለማ ክፍል ለወራት ታስሮ በስቃይ እንደቆየ መናገሩ ይታወቃል።  ከአራት ወር በላይ የቆየበት ደመወዝ እስካሁን ተቋርጦ በመቆየቱ ከሁለት ልጆቹ  ጋር ቤተሰቦቹ ለከፋ ችግር እንደዳረጉት ተናግሯል።
Filed in: Amharic