>
5:13 pm - Wednesday April 18, 3894

የኮሮና ቫይረስ ምንነት እና መከላከያ ዘዴዎቹ!!!  (ሰለሞን ጋዲሴ)

የኮሮና ቫይረስ ምንነት እና መከላከያ ዘዴዎቹ!!! 

ሰለሞን ጋዲሴ
የኮቪድ19 በሽታ  የየቀኑ ምልክቶች 
ጆን ሆፕኪንስ ይኑቨርሲቲ (Johns Hopkins University)  ስለ ኮሮና ቫይረስ የሚከተለውን መረጃ አውጥቷል።
እኔም መረጃው በጣም ጠቃሚ ስለሆነ  የቻልኩትን ያህል ከእንግሊዘኛው ወደ አማርኛ ልመልሰው ሞክሬያለሁ፡፡  እባካችሁ አንብቡት እና ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ለሌሎች አጋሩት።
 ቫይረሱ ህይወት ያለው ፍጡር ሳይሆን እራሱን በሚከላከልበት ስስ ስብ የተሸፈነ የፕሮቲን ሞሎኪዩል( ዲኤን.ኤ) ሲሆን ወደ አይን፣ አፍንጫ እና አፍ በሚገባ ጊዜ በነርሱ ውስጥ በሚገኝ ክፍተት ውስጥ በመግባትና የራሱን ተፈጥሯዊ ማንነት በመቀየር  ወደ ብዙ እና አጥቂ ተውሳክነት ይቀየራል፡፡
 ቫይረሱ ህይወት ያለው ፍጡር ሳይሆን የፕሮቲን ሞሎኪዩል( ዲኤን.ኤ) እስከሆነ ድረስ በራሱ ይበሰብሳል እንጂ አይሞትም፡፡ የሚፈራርስበት ጊዜም በአየሩ የሙቀት መጠን፣ የአየሩ እርጥበት መጠን እና ቫይረሱ በተገኘበት ቁስ ይወሰናል፡፡
 ቫይረሱ በጣም ስስ/ ተሰባሪ ሲሆን ከመሰበር የሚከላከው ነገር ቢኖር በዙሪያው የከበበው በጣም ስስ ስብ ነው፡፡ ለዚህም ነው ማንኛውም ሳሙና ወይም የጽዳት መጠበቂያ ቫይረሱን ለመከላከል ፍቱን መፈትሄ የሆነው፡፡ ምክኒያቱም የሳሙናው አረፋ የቫይረሱን ስብ መሰል መሸፈኛ ይሰባብረዋል፡፡ ለዚህም ነው እጃችንን ከ20 ሰከንድ ለማያንስ ጊዜ በደንብ የምናሸው/ ምንፈትገው፡፡ የስብ መሸፈኛውን በሳሙና ስናሟሟው የቫይረሱ የፕሮቲን ሞሎኪውሉል( ዲኤን.ኤ) እራሱ ይበታተን እና ይሰባበራል፡፡
 ሙቀት ስብ መሰል መሸፈኛውን የቀልጠዋል፡፡ ስለዚህ ከ 25 ዲሴ በላይ በሞቀ ውሃ እጃችሁን፣ ልብሳችሁን፣እና ማንኛወንም ነገር እጠቡ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሙቅ ውሃ ሳሙና ብዙ አረፋ እዲያወጣ ስለሚያደርግ የበለጠ ጠቃሚ ይሆናል፡፡
 አልኮል እና ከ65 እጅ በላይ ከሆነ አልኮል ጋር የተደባለቀ ማኛውም ነገር ማንኛውንም ስብ ያሟሟል በተለይ የቫይረሱን ስስ ስባማ የውጭ ሽፋን ያሟሟዋል፡፡
 ማንኛውም 1 እጅ ቀለም ማስለቀቂያ (Bleach) ( ለምሳሌ በረኪና) ከ 5 እጅ ውሃ ጋር ተደባልቆ የቫይረሱን ስብ ከውስጡ ያሟሟዋል፡፡
 አልኮል ፣ ክሎሪን ወይም ሳሙና ከተጠቀምን በኋላ ሃይድሮጂን ፐርኦክሳይድ  (Hydrogen peroxide)  መጠቀም የቫይረሱን ዲ.ኤን.ኤ ይሰባረዋል፡፡ ነገርግን ነጹህ ሃይድሮጂን ፐርኦክሳይድ መጠቀም አለባችሁ፡፡ ቆዳን ግን ይጎዳል፡፡
 ቫይረሱ እንደ ባክቴሪያ ህይወት ያለው ነገር ስላይደለ በጸረ ባክቴሪያ ልንገለው አንችልም ስለዚህ ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ቶሎቶሎ ልናፈራርሰው ብቻ ነው የምንችለው፡፡
 ማንኛውንም የተጠቀማችሁበትንም ይሁን ያልተጠቀማችሁበትን ልብስ እና አንሶላ በጭራሽ አታራግፉ፡፡ ምክኒያያቱም ክፍተት ባላቸው ነገሮች (አየር እና ውሃ የሚያሳልፉ) ቫየረሱ ሲጣበቅ ምንም መንቀሳቀስ የማይችል ሲሆን በ3 ሰአት ውስጥ እራሱ ይፈራርሳል፡፡ መዳብ በተፈጥሮው ተዋህስያን አምካኝ በመሆኑ እና እንጨት ደግሞ እርጥበትን በሙሉ ስለሚያስወግድ እና አንዴ ቫይረሱ ካረፈበት ስለማይለቀው  ቫይረሱ ለ4 ሰአታት ብቻ ተቀምጦበት ይሰባበራል፡፡ ( cardboard ) ላይ 24 ሰአታት፣ ብረታ ብረት ላይ 42 ሰአታት፣ ፕላስቲክ ላይ 72 ሰአታት ከመፈራረሱ በፊት ሊቆ ይችልል፡፡  ነገርግን ካራገፍን ወይም የአቧራ ማራገፊያ ማሽን ከተጠቀምን ቫይረሱ ለቀጣይ 3 ሰአታት በአየር ውስጥ በመቆየት ወደ አፍና አፍንጫችን የመግባት እድል ያገኛል፡፡
 የቫይረስ ሞሎኪውሎች በሰው ሰራሽ እንደ መኪና እና የቤት አየር ማቀዝቀዣ ላይ ተደላድለው ይቆያሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተደላድሎ ለመቆየት እርጥበት እና  በተለይ ደግሞ ጨለማ ቦታ ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህ የአየር እርጥበታማነትን ማስወገድ፣ ደረቅ፣ ሞቃት እና ብርሃናማ ሁኔታዎችን መፍጠር ቫይረሱ በቶሎ እንዲዳከም ያደረጉታል፡፡
 ማንኛውም ዩቪ ( አልትራቫዮሌት) ብርሃን ያለው ቁስ የቫይረሱን ፕሮቲን ይሰባብረዋል፡፡ ለምሳሌ የአፍንጫ እና አፍ መሸፈኛን አክሞ እንደገና ለመጠቀም ፈጽሞ ውጤታማ ነው፡፡ ነገር ግን ተጠንቀቁ ይህ ብርሃን በቆዳችን ላይ ያሉ የፕሮቲን ክፍሎች በመጉዳት  በቆይታ የቆዳ መሸብሸብ እና የቆዳ ካንሰር ሊያስከትል ይችላል፡
vv
 ቫይረሱ ጤነኛ ቆዳ አልፎ ሊገባ አይችልም፡፡ ( ይህማለት ቁስለት ወይም የተከፈተ ቆዳ ካገኝ በቀላሉ ወደ ስውነታችን ሊገባ ይችላ እና መሸፈን እና መጠንቀቅ አለብን ማለት ነው)
 አቼቶ (Vinegar ) የቫይረሱሱን የውጭ ስባማ አካል ሊያሟሟው ስለማይችል ከቫይረሱ ሊከላከል አይችልም
 ማኛውም የመጠጥ አልኮል ወይም በጣም ጠንካራው ቮድካን ጨምሮ ከ40 ፐርሰንት በላይ አልኮል ስለሌላቸው የሚፈለገው 65 ፐርሰንት አልኮል ስለሆነ ከቫይረሱ ሊከላከሉ አይችሉም፡፡
 የአፍ መጉመጥሞጫው የአሜሪካው LISTERINA መጠቀም ከፈለግን 65 ፐርሰንት አልኮል አለው፡፡ ( ጠቃሚ ነው ማለት ነው)
 በተፋፈጉ  ጠባብ ቦታዎች እና ክፍሎች ውስጥ ቫይረሱ በብዛት ሊኖር የሚችል ሲሆን በተናፈሱ እና በተፈጥሮ ገላጣ ቦታዎች የቫይረሱ መጠን አነስተኛ ነው፡፡
 ተደጋግሞ ተብሏል ነገርግን እጃችሁን ታጠቡ። አፍንጫችሁን፣  ምግብ፣ የበር መዝጊያዎች፣ እጀታዎች፣ ማብሪያ ማጥፊያዎች፣ የርቀት መቆጣጠሪያዎች፣ የእጅ ስልኮች፣ ሰአት፣ ቴሌ ቪዥን፣ እና መታጠቢያ ቤት ከመጠቀማችሁ በፊት እና በኋላ እጃችሁን መታጠብ አለባችሁ፡፡
 የቫይረሱ ሞሎኪዩሎች በጥቅጥቅ እና ጥቃቅን  የእጃችን ሽብሽብ ወይም በተቆረጠ ቆዳችን መሃል ሊቀመጡ ስለሚችሉ በተቻለ መጠን እጃችንን በብዙ ውሃ ማራስ እና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡ እጃችንን ባራስነው መጠን የቫይረሱ መጠን በዛው ልክ ይቀንሳል፡
የኮቪድ19 በሽታ  የየቀኑ ምልክቶች 
• ከ1-3 ቀን
    . በነዚህ የመጀመሪያ ቀናት ቀላል ጉንፋን መሰል ሆኖ ቀለል ያለ ትኩሳት እና የጉሮሮ ህመም ብቻ ሲኖር የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት ጥሩ ነው ።
    . የሰውነት መከላከያ ደከም ያለባቸው ስዎች ቀለል ያለ ተቅማጥ እና ማቅለሽለሽ ሊኖራቸው ይችላል ።
• በ 4 ኛው ቀን
    . የጉሮው ህመም ይጨምራል እንደዚሁም     የድምፅ መወፈር ይኖራል ።
    . ብዙ ጊዜ ትኩሳት  አይኖርም 36.5 degree ብቻ ይሆናል
    . ቀለል ያለ እራስ ምታት እና የምግብ እና መጠጥ ፍላጎት   ሊስተገዋጎል ይችላል ።
• በ 5 ኛው ቀን
    . ስሜቶች የበለጠ ይጨምራሉ  ፦ የጉሮሮ ህመም ይጨምራል ፣ ድምፅ የበለጠ ይጎረንናል ።
    . በእንቅስቃሴ ወቅት የስውነት ህመምና ቁርጥማት ይኖራል ፤ የሰውነት  ድካም ይኖራል ።
• በ 6 ኛው ቀን
    . ትኩሳት ይጀምራል
    . ደረቅ ሳል ከጉሮሮ ህመም ጋር ይበረታል
    . ምግብ በመመገብ  ፣ የሚጠጣ ነገር ሲወስድ እንደዚሁም በንግግር ጊዜ የጉሮሮ ህመም ይኖራል ።
 ተቅማጥና ማቅለሽለሽ የበለጠ ይጨምራል ።
″ በ 7 ኛው ቀን
    . ትኩሳት ከ 38 ድግሪ በላይ ይሆናል
    . ደረቅ ሳል ይኖራል ፣ ይጨምራል
    . የስውነት ቁርጥማት ፣ ራስ ምታት ፣ ተቅማጥና ማቅለሽለሽ ይጨምራል ።
• በ 8 ኛው ቀን
    . መተንፈስ መቸገር
    . የደረት መክበድና ህመም
    . ደረቅ ሳል ይኖራልም ይጨምራልም
    . የስውነት ቁርጥማት ፣ ራስ ምታት ይቀጥላልም  በጣም  ይጨምራል ።
     . ትኩሳት ይቀጥላል ፣ ይጨምራል
• በ 9 ኛው ቀን እና በሚቀጥሉት ቀናት
    . ሁልም ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በጣም ይጨምራሉ ።
ማንኛው ስው የሚከተሉት አደገኛ ምልክቶች ካሉ በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቁአም መሄድ ያስፈልጋል ።
      ፧ የተራዘመ ድረቅ ሳል
      ፧ የትንፋሽ ማጠር
      ፧ የደረት ህመም
      ፧  ከፍተኛ ትኩሳት
ሴማህ እናቶች እና ህፃናት ህክምና ማዕከል
Filed in: Amharic