>
5:13 pm - Tuesday April 19, 9898

የእስራኤል ሳይንቲስቶች ለኮሮና ቫይረስ ፍቱን ያሉትን መድሃኒት ማግኘታቸውን አስታውቁ!!! (ሀብታሙ አያሌው)

የእስራኤል ሳይንቲስቶች ለኮሮና ቫይረስ ፍቱን ያሉትን መድሃኒት ማግኘታቸውን አስታውቁ!!!

ሀብታሙ አያሌው
የእስራኤል የባዮ ሜዲካል ሳይንቲስቶች ለኮሮና ቫይረስ ኮቪድ 19 ፍቱን ነው ያሉትን መድሃኒት ማግኘታቸውን ይፋ ባደረጉበት ዘገባ እንደተመለከተው ለኮቪድ 19 ያገኙት መድሃኒት እጅግ ጽኑ በሆኑ ህሙማን ላይ ተሞክሮ መቶ በመቶ ፍቱንነቱ ተረጋግጧል።
ፕሉሪስተም ቴራፑቲክ በተሰኘው የምርምር ተቋም የተሰራው መድሃኒት እንደ ስኳር የደም ግፊት አስም የልብ ህመም ሌሎች በሽታዎች የሚሰቃዩ ሰባት ታማሚዎች ላይ ተሞክሮ ኮሮናን በስኬታማነት ፈውሶታል።
እንደ ምርምር ቡድኑ ሃላፊ ዶክተር ያኪ ያናይ ገለፃ በሴል ፕሮቲን ውስጥ በሁለት ተልእኮዎች ነው  መድሃኒቱ የተዘጋጀው በሴል ውስጥ በሽታን የመከላከል ብቃትን የማሳደግ ና በተለይም ከሴሉ ውስጥም የኮሮና ቫይረስን በሚያስውገድ ዘዴ ህመምተኞች ከኮቪድ 19 ፈጥነው እንዲያገግሙ ሆኖ ነው መድሃኒቱ የተሰራው።
በእስራኤል ሃይፋ ከተማ የሚገኘው የምርምሩ ተቋም እንዳስታወቀው መድሃኒቱ በህመምተኞቹ ሴል ክፍል ተውስዶ በሽታን በሚቋቋም አካል ቅንጣት እንዲያድግ ሆኖ ነው የተሰራው።
ይህም በሽታን የሚከላከል የፕሮቲን ሴሎች አብቅሎ ሞትን የሚያስከትለውን የኮቪድ 19 ቫይረስ በመርታት ፍውስ እንደሚያስገኝ አረጋግጠናል ነው ያሉት ተመራማሪዎቹ የምርምር ተቋሙ ሃላፊዎች ሙከራው ስኬታማንቱን ተከትሎ ከፈቃድ ሰጪ አካል ይሁንታን እንዳገኘ በፍጥነት በጅምላ ማምረት እንደሚጀምሩ ገልፀዋል።
ዘገባው የ ዴይሊቬንደር ነው
~
የሀኪሞችን ምክር ተግባራዊ ማድረጉ ግን እንዳይረሳ !
Filed in: Amharic