>
5:16 pm - Tuesday May 24, 6292

ህወሀት በመቐለ ተኩስ ከፍታ የወጣቶችን ደም አፈሰሰች፤ ሙትና ቁስለኛ አድርጋቸዋለች!!! (አሰግድ ገብረስላሴ)

ህወሀት በመቐለ ተኩስ ከፍታ የወጣቶችን ደም አፈሰሰች፤ ሙትና ቁስለኛ አድርጋቸዋለች!!!

አሰግድ ገብረስላሴ
ህወሓት  ” ሰብሰብ ብላችሁ ጠላ ስትጠጡ ነበረ” ብላ በነዚህ ወጣቶች ላይ ተኩስ በመክፈት የግድያና የማቁሰል እርምጃ ወስዳለች። የእናቶቻቸውን አንጀት እርር የአባቶቻቸውን ቆሽት ድብን አድርጋለች። ትህነግ በየምክንያቱ የሰው ደም  ካልገበረች ህይወቷ እንደማይቀጥል ያስጠነቆለች ውቃቢ ቀላቢ ነች የምንለው ዝም ብለን አይደለም
—–
የመቐለ አድማ  ፖሊስ በውጣቶች ላይ ተኩሶ ኣንድ ወጣት በመግደል ሁለት ወጣቶች በከባድ እንዲቆስሉ ኣድርገዋል።
 ትናንት 09/09/2012 ዓ/ም በመቐለ 05 ቀበሌ ኑዋሪ በሆኑት ወጣቶች ተኩስ በመክፈት ሽሻይ የተባለ ኣንድ ወጣት ወድያውኑ ሂወቱ ሲያልፍ ጠዓመ ሓድጉና ሞገስ ሓዱሽ የተባሉት ሁለት ወጣቶች ደግሞ ክፉኛ ቆስለው ዓይደር ሆስፒታል ለህክምና ገብተዋል።
ለግድያው ምክንያት የተባለው “ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የወጣው ስቸኳይ ግዜ ኣዋጅ በመጣስ ተሰብስባቹሃል” የሚል ሲሆን ፖሊስ “ተበተኑ” በማለት ወጣት ሽሻይን ተኩሶ እንደገደለው ተገልፀዋል።
ቶኩሱ ለሰዓታት የቆየ በመሆኑ የ03፣ 05፣ 06 ቀበሌ በርካታ ህዝብ፣ ወጣቶችና ከፍተኛ ቁጣና ተቀስቅሰዋል።
 እንዲሁም መንግስት ችግሩ ለማረጋጋት በርካታ ፖሊስ፣ ምልሻ፣ ኣድማ በታኝ ልዩ ሃይል ፖሊሶች ልኮ ለመረጋጋት ጥረት ኣድርገዋል።
ፖሊስ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በታወጀው ኣስቸኳይ ግዜ ኣዋጅ ምክንያት ሰው በጥይት ሲገድል ለሁለተኛ ግዜው ነው።
ከኣዋጁ በኋላ በጥይት ተኩሶ የኣካል ጉዳት ማድረስ፣ ደብድቦ ኣካል ማጉደል፣ ያለምክንያት ማሰር፣ ሌሎች ጥፋቶች በፖሊስ እየተፈፀሙ ይገኛሉ።
የወንድማችት ሽሻይ ነብስ በገነት ያኑርልን።
 ቤተሰቦቹና  ጓደኞቹ ፅናቱ ይስጣቹ።
* ፍትህ ለመቐለ ወጣቶች !
Filed in: Amharic